To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Saturday, October 5, 2013
በአንድነት እና በተደራጀ ሃይል ጠላትን ዳግም እንዳይነሳ አድርጓ መቅበር ይቻላል ::
Oktober 5/2013
ከገዛኸኝ አበበ
በአሁኑ ሰአት አገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደመትገኝ በበዙዎች ዘንድ እየተነገረ ይገኛል:: በሀገሪቷ ውስጥ የሚኖሩ የሀገሪቷ ዜጎች እንደ ዜጋ መብታቸው ሳይከበር አገሪቱን እየመራው ነው በሚለው ሀይል ጨቋኝ አገዛዝ የተነሳ መብታቸው ታፍኖ እና ተረግጦ በተወለዱበት እና በተፈጠሩበት ሀገር በነፃነት መኖር በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ እና ወያኔ ኢሕአዲግ በየባታው በየሰፈሩ በየመስሪያ ቤቱ አሉኝ የሚለውን የራሱን ካድሬዎችን በማሰልጠን እና በማሰማራት በህዝባችን ላይ አደገኛ የስለላ መረቡን በመዘርጋት ህዝባችንን በማሸበር እና በማወክ ላይ እንደሚገኝ ካለኝ መረጃ ለማወቅ ችያለው ::
ይህም ሊሆን የቻለበት ዋንኛው ምክንያት በሀገር ቤትም እና ከሀገር ውጪ ያሉት የመንግስት ተቀዋሚዎች እያሳዩት ያለው ወኔ እና ቆራጥነት የተሞላበት ትግል ለወያኔ ኢሕአዲግ አመራሮች የራስ ምታት ሳይሆን እንዳልቀረ ይገመታል::
በአሁኑ ሰአት በሀገር ውስጥ የሚገኙት የተቀዋሚ ድርጅቷች እንደ ሰማያዊ ፓርቲ እና እንደ እንድነት ፓርቲ ያሉ ሀገር በቀል ድርጅቷች ትግሉን በሙሉ ሀይል በመግፋት ላይ ሲሆኑ እነዚህ ድርጅቶች እያደረጉ ያለውን የሀገር ወኔ የተሞላበት ሰላማዊ ትግል ሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሊያበረታታው እና ሊደግፈው ከጓናቸውም ሊቆም ይገባል ባይ ነኝ :: እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች የወያኔን መንግስት ምን ያህል እያሰደነበሩት እና እያስደነገጡት እንዳለ ወያኔ እያደረገ ካለው ነገር መረዳት እንችላለን::
እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶቸ ባለፈው ሳምንታት አዘጋጅተውት በነበረው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰልፉን ለማሰናከል የወያኔ መንግስት ዘውትር እንደሚያደርገው ሁሉ አባሎችን ሲያስር ሲገርፍ እና ሲያሰቃይ እንደነበር በአደባባይ የታየ ሀቅ ነበር::ይህም ሀገርን በነጻነት እየመራው ነው ከሚል ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ እና እንዲሁም የወያኔ መንግስት ምን ያህል የዱርዬ እና የወሮበላ መንግስት መሆኑን ለሀገራችን እና ለአለም ህዝብ በተግባር ያሳየበት ነበር :: የወያኔ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ህዝቡን ይሰር ይግረፍ ያሳቃይ እንጂ ነገሩ ግን ሌላ ነው :: አፈናው ወከባው እስራቶ እና ስቃዩ ያልበገረው ህዝብ ግን ለወያኔ ዛቻ እና አሰልቺ ፕሮፖጋንዳ የሚገዛ እና የሚንበረከክ አይመስልም:: በፓርቲዎቹ የጠነከረ እና የበሰለ አመራር እና በአባላቱ ወኔን የተሞላበት ተነሳሽነት የወያኔ መንግስት የተደናገጠ ይመስላል::
ሰሞኑን ሀገር ቤት ከሚኖር አንድ በጣም ከምቀርበው እና የወያኔን ሚስጥር ያውቃል ከምለው ሰው ጋር ተገናኝቺ ነበር :: በአገር ቤት እየተደረገ ባለው ትግል የህዝቦች ልብ ምን ያክል እንደራቀው የተረዳው የወያኔ መንግስት በየቦታው የሚገኙትን ካድሬዎቹን በየስፍራው ሰብስቦ ውይይት ከካድሪዎቹ ጋር እንዳደረገ እና በውይይቱም ወቅት አባላቶቹ የተፈለገውን ያክል እየተንቀሳቀሱ እንዳይደለ እና ምንም ነገር እየሰሩ እንዳልሆነ ከዚህ በሆላ ግን በትጋት መስራት እንዳለባቸው ቁጣን የተሞላበት ትህዛዝ ለካድሬዎቹ እንዳስተላለፈ እና ለስለላ ካድሬዎችን በስፋት እንዳሰማራ እና ወያኔ ያሰለጠናቸው የወያኔ ካድሬዎች ከስለላው ጉን ለጉን በየመስሪያ ቤቱ፣ በየዪንቨርስቲዎች ፣ በየኮሌጆች እና በእየትምህርት ቤቱች፣ በየቀበሌው እና በየሰፈሩ ወያኔን የብርሃን መላአክ አስመስለው በህዝባችን ዘንድ ለመቅረብ በስፋት እየሰሩበት እንዳለ ለማወቅ ችያለው:: ወያኔ ይሳካልኛል ብሎ ይህን ያድርግ እንጂ ሀቁ ግን ሌላ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ማን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል:: የወያኔን ጭራቅነት እና አረመኔነተ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መንገረም አያስፈልግም:: ይህ ሕዝብ በሃያ ሁለት ዓመታት የወያኔ አገዛዝ ዘመን ውስጥ የመኖር ህልውናው ጥያቄ ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ ውስጥ እየተገኛ ወያኔ ኢሕአዲግ በሕዝብ ዘንድ እራሱን የብርሃን መላአክት አስመስሎ ለማድረግ የሚያደርገው ሮጫ የሚያዋጣው አካሄድ አይመስለኝም ::
በሀገር ውስጥ እየተደረገ ያለው ተቃውሞ እና ትግል ብቻ አይደለም ለወያኔ መንግስት የራስ ምታት እየሆነበት ያለው በውጭ ሀገር የሚገኙትም የፖለቲካ ድርጅቶች እና ሀይሎችም በውጪ ሀገር የሚኖረውም የኢተዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በተለየ መንገድ በሀገራዊ ስሜት እየተሰባሰቡ፣ እየተደራጁ እና ሀይላቸውን እያጠናከሩ የወያኔንን መንግስት አከርካሪውን ለመስበር በዝግጅት ላይ መሆናቸው እና ወያኔ የግሌ የእራሴ ናቸው ብሎ የሚመካባቸው ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ሳይቀሩ ይሄን ትግል በመቀላቀል የወገን አጋርነት እያሳዪ መሆናቸው እና በተለይም ሰሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ጸሀፊ አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ግንቦት ሰባት በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ መስመሩን እየዘረጋ እንደሆነ መናገራቸው በወያኔ መንግስት ላይ የጭለማ ዘመን እየመጣ እንዳለ አመሳካሪ ሲሆን ወያኔን በሀይል ለመፋለም የተነሱት ድርጅቶች ደግሞ በርቷ የሚያሰኝ ታላቅ ስራ እየሰሩ እንዳለ እና በውጭ ሀገር የሚኖረው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊም በታላቅ ሀገራዊ ስሜት በማንኛውም መንገድ ከጓናቸው እንደሚገኝ እያስመሰከረ ይገኛል:: ለዚህም ምስክር የሚሆነው በ 28/9/2013 በኖርዌይ ኦስሎ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያን ዜጎች ወያኔን በሃይል ለመፋለም ቋርጧ የተነሳውን የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሀይልን ለመደገፍ በራሳቸው ተነሳሽነት ባዘጋጁት የገንዘብ ማሠባሠቢያ ፕሮግራም ላይ ምን ያክል ወያኔንን ለማዳከም ቆርጠው መነሳታቸውን እና ከሕዝባዊ ሀይል ጓን መሰለፋቸውን ያስመሰከሩበት እና በፕሮግራሙም ላይ ሕዝባዊ ሀይሉን ለማጠናከር ከፍተኛ ገንዘብ ከሕዝብ እንደተሰበሰበ እና በሁሉም በኩል የተሳካ ዝግጅት እንደነበር ለማየት ችለናል :: ፕሮግራሙን ለመታደም ከተለያዩ አውሮፓ ሀገሮች ሰዎች እንደተገኙ እና በነበረው ዝግጅት በጣም መደሰታቸውን ለማወቅ ችለናል ::
በተቃራኔው ወያኔ ያሰማራቸው የወያኔ ካድሬዎች ከመጀመሪያው አንስቶ ፕሮግራሞ እንዳይሳካ ከፍተኛ መሯሯጥ ሲያደርጉ እንደነበር እና ዝግጅቱ እንዲቋረጥ ክፉኛ እንደሮጡ ነገር ግን የገቢ ማሰባሰቢያውን ባዘጋጁት ኮሚቴዎች የበሰለለ አመራር ሳይሳካላቸው እንደቀረ እና በፕሮግራሙ መጨረሻ የፕሮግራሙን በጥሩ ሁኔታ መሳካት ሲያውቁ እርስ በእርስ መደባደባቸውን ከፕሮግሙ በኋላ በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል ::
ከፕሮግራሙ መጠናቀቅ በኍላም ባሉት ቀናት ውስጥም የወያኔ መንግስት ክፉኛ እንደተደናገጠ የሚያሳዩ ነገሮች እየታየ ሲሆን በኦስሎ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ውስጥ የወያኔ ዲፕሎማት እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዲፕሎማቲክ የሚስጥር ውይይት ያደረጉ ሲሆን የወያኔው እኝው የወያኔ ዲፕሎማት ኢሕአዲግን የብርሃን መላእክት አስመስሎ በማቅረብ በኖርዌይ የሚኖሩት ተቀዋሚ ኢትዮጵያኖች የተለያየ ቃላትን ሲከሱ እንደነበር ማወቅ ችለናል ::
የወያኔ መንግስት የግንቦት ሰባት አካሄድ ክፉኛ ያስደነገጠው ይመስላል በዚህም በተለያዩ አውሮፓ አገሮች በመዞር በግንቦት ሰባት ላይ ያለውን ፍርሃት የወለደውን ፕሮፖጋንዳውን ለመዝራት እየሞከረ ሲሆን ይህ አካሄዱ ደግሞ በየትኛውም አገራት ተቀባይነትን እያገኘ አይደለም:: በአሁኑ በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ እየጠነከረ ባለው ትግል በታላቅ ፍርሃት ውስጥ እና መደናገጥ ውስጥ የገባውን ይሄን ዘረኛ እና አረመኔ መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጌዜ ዳግም እንዳይነሳ ለመቅበር በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉት በተለያየ አቅጣጫ እየታገሉ ሀይሎች አንድነት ሀይል ነው እና በአንድነት እና በተደራጀ ሃይል መነሳት ይጠበቅባቸዋል ::
አንድነት ሃይል ነው!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment