Saturday, October 18, 2014

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ላይ ሳለ ያስተላለፈው መል ዕክት + (የክሱን ዶሴ ይዘናል)


(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶ፤ በአምስተኛ ፖሊስ ጣብያ ከቆየ በኋላ ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት ሊወሰድ በዝግጅት ላይ እንደነበረ፤ ትላንት በስፍራው ሄደው የጠየቁት ጋዜጠኞች ገልጸዋል። ከነዚህ ጋዜጠኞች መካከል ኤልያስ ገብሩ ስለሁኔታው በአጭሩ እንዲህ ብሏል።
ጋዜጠኛ ተመስገን በፌዴራል ፖሊሶች ታጅቦ ሲወሰድ
‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው››
‹‹የእስክንድር ሃሳብ ትክክል ነው›› ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከነገረን የተወሰደ
*******************************
‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ በተስተናገዱ ሶስት ጽሑፎች ተከስሶ ለሁለት ዓመት ያህል የክስ ሂደቱ ሲታይ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ጥፋተኛ›› ከተባለ በኋላ ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጥዋት ላይ ከእስከዳር አለሙ፣ ይድነቃቸው ከበደ እና ስለሺ ሀጎስ ጋር ሄደን ጠይቀነው ነበር፡፡
ከተሜ ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦችን ተወያይተናል፣ በተወሰኑ ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በየግል እምነቶታችንን በማንሳት ሃሳቦችን ተለዋውጠናል፡፡ ጥያቄዎችን አንስተን ምላሾችን ተደማምንም ነበር፡፡ …

ተመስገን፣ በመጨረሻ ካነሳቸው ሀሳቦች መካከል ጥቂቱን እንዲህ ላስነብባችሁ፡-
‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ ‹‹በአሁን ወቅት የእስር፣ የስደት፣ …ወዘተ ነገሮች መብዛት ሰላማዊ ትግል ሥራውን እየሰራ መሆኑን ማሳያ ነው›› ያለው ትክክል ነው፡፡ እኔም ይህንን የእስክንድርን ሃሳብ እጋራለሁ፡፡ የእስር መብዛት ወደፊት፣ ነገ ላይ በሀገራችን የሚያመጣው ለውጥ አለ፡፡››
ተመስገን፣ እስከግማሽ ቀን ድረስ በዚሁ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረ ሲሆን፣ ከሰዓት በኋላ ወደቂሊንጦ እስር ቤት እንደሚሄድ ነግሮናል፡፡
ተሜ፣ የሚመጣውን ነገር ሁሉ በሀገሬ ሆኜ እቀበላለሁ ላልከው ጽናትህ ትልቅ ክብር እሰጥሀለሁ!
ብርታትና ጥንካሬውንም ይበልጥ ፈጣሪ ይስጥህ! (የጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ዘገባ እዚህ ላይ አብቅቷል)
ጋዜጠኛ ተመስገን በፌዴራል ፖሊሶች ታጅቦ ሲወሰድ
ጋዜጠኛ ተመስገን በተለያዩ ጊዜያት ወደ ውጭ እንዲወጣ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በአገሩ ውስጥ ቆይቶ የሚሰጠውን ፍርድ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል።
ሰለኝ ለአመታት ፍርድ ቤት ሲመላለስበት በነበረው ክስ ጥፋተኛ ተብሎ ወደ እስር ቤት ወረደ ከ20-25 ዓመት ሊፈረድበት እንደሚችል ይገመታል
ተመስገን የፍህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት በጻፋቸው
“ሞት የማይፈሩ ወጣቶች”፣ “የፈራ ይመለስ” “የብሔር ነፃነት እስከመጨፈር” እንዲሁም ባለፉት 20 አመታት የኢህአዴግ መንግስት በበደኖ፣ በአርሲ፣ በአምቦ እና በጅማ የፈጸማቸን የጅምላ ጭፍጨፋ እና የአ.አ ዩኒቨርስቲ ተማሪች በኤርትራ እና በአሰብ ጉዳይ አስመልክቶ መንግስት የወሰደውን እርምጃ ጠቅሶ በመጻፉ ፡ የሚከተሉት ክሶች ቀርበውበት ነበር
1 ህገመንግስቱን በሀይል ለማፍረስ እና የሰሜን አፍሪካው አብዮት በኢትዮጵያም እንዲደገም ወጣቶችን በማነሳሳት
2. የህዝብን ሰላም በማናወጥ እና
3. የመንግስትን ስም በማጥፋት
ጋዜጠኛ ተመስገን ወደ እስር ቤት ከመወሰዱ በፊት በጊዜያዊ ማረፊያ ውስጥጋዜጠኛ ተመስገን ወደ እስር ቤት ከመወሰዱ በፊት በጊዜያዊ ማረፊያ ውስጥ
የክሱን ሙሉ ቅጂ ከዚህ ቀጥሎ ለህትመት አብቅተነዋል።
page 1page 2page 3page 4page 5
ጋዜጠኛ ተመስገን ከ2 ሳምንት በኋላ፤ ኦክቶበር 27 – 2014 ወደ ፍርድ ቤት ተመልሶ መጥቶ ዳኞቹ የፍርድ ውሳኔ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment