በ46 አመቱ የህወሃት አገልጋይ እና የኢምባሲ ጠባቂ በሆነው ሰለሞን ገ/ስላሴ ላይ የአሜሪካን መንግስት ክስ መሰረተበት
Oct 04, 2014
ቢል ሚለር የአሜሪካ ፍትህ አካል ቃላ አቃባይ የሆኑት ባለፈው ሰኞ በሰላማዊ ሰልፈኞች እና በኢትዮጵያ ኢምባሲ ዋሽንግተን ጽ/ቤት መካከል በነበረው ሂደት ላይ የኢምባሲ ጠባቂ በሆነው ሰለሞን ገ/ስላሴ ሽጉጥ ተኩሶ የመግደል ሙከራ ማደርጉ ወንጀል መሆኑን አምነው ይህም የዲፕሎማቲክ ፈቃዱ ከክስ እንደማያድነው ተናገረዋል። በዚህ መሰረት የአሜሪካን መንግስት ፍትህ ጸ/ቤት ክሱን አዘጋጅቶል። ሰውየው ከሀገር ቢባረርም በሌለበት ሂደቱ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ሰለሞን ገ/ስላሴ ከዚህ በሆላ ጥፋተኛ ከተባለ ከ15 እስከ 20 አመት በሚደርስ የእስራት ቅጣት እንደሚጠብቀው የህግ ባለሙያዎች የተነተኑ ሲሆን ይሁን እንጂ ሰለሞን ወይም የኢትዮጵያ ኢምባሲ ይህን ሂደት ስለሚያውቁ ተጠርጣሪው ወደ አሜሪካ የመመለስ አጋጣሚን እንደማያደርግ ይታመናል።
ለህግ ባለሙያው; ከክስ ሂደቱ ማጠናቀቂያ በሆላ ውሳኔዉን ለማስፈጸም የአሜሪካን ሀገር ወንጀለኛውን ለመያዝ የማደኛ ትእዛዝ ሊያስተላልፍ ይችላል ወይ ብለን ላቀርብንላቸው ጥያቄ አሁን የሚወሰን ሳይሆን ወደፊት እንደወንጀሉ ክብደትና ቅለት የሚለካ ነው ሲሉ የህግ ባለሙያው ለአባይ ሚዲያ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በእንደዚህ አይነት የቀለለ ወንጀል ሲገባ የመጀመሪያ ባይሆንም ይህ ለየት የሚያደርገው አምባሳደር ግርማ ብሩም የጉዳዩ ተዋናያን መሆናቸው እንዲሁም በርካታ የአለም ሚዲያዎች የዘገቡት መሆኑ ነው።
አምባሳደር ግርማ ሰሙኑን ከሬዲዮ ፋና ጋርና ከሌሎች የወያኔ ሚዲያዎች ጋር ባደረጉት ንግግራቸው ምንም አይነት ስለ ጠባቂው ሰለሞን የሰጡት ማስተባባያ የለም። በደፈናው የተቃዋሚ ቡድኖች በኤርትራ ተደግፈው ያደረጉት ነው ሲሉም ተደምጠዋል።
ዘጋቢያችን በማጠቃለያው የኤርትራ መንግስት አሜሪካ ውስጥ ገብቶ ወያኔን ያስጭንቃል እንዴ? ምን አይነት አምባሳደር ይሁን ሀገሪቱ ይዛ ፕሮፖጋንዳ የምትሰራው ሲል ትዝብቱን በማከል ሪፖርቱን ለአባይ ሚዲያ ልኮልናል ።
No comments:
Post a Comment