Saturday, August 10, 2013

እርስ በእርስ ሲያናቁረን ዝም ብለን ከተመለከትን

እርስ በእርስ ሲያናቁረን ዝም ብለን ከተመለከትን የመሪዎች ሥልጣን በምድር ከጠመንጃ አፈሙዝ የሚመጣ፣በሰማይ ደግሞ ፈጣሪ ይሁንታ እንዳለበት የምናመን ይመስለኛል፡፡ መሪዎቻችን አሁንም ሥልጣናቸውን የሚያገኙት ከመለኮታዊ ኃይል ንደሆነ አድርገው ይወስዱታል፡፡ ዘመናዊ ለመምሰል የዴሞክራሲ ጭምብል ያጠልቃሉ፤በይዘት ግን ፈላጭ ቆራጭ አምባገነኖች ናቸው፡፡ በዚህ መልክ፣የኢህአዴግ ሥርዓት ቁንጮ ነጥረው ወጥተዋል፡፡ ምድረ-ኢትዮጵያ በሙሉ የእሳቸው ሆናለች፡፡ መሬቱን ከሕዝቡ ነጥቀው ወስደዋል፤መላ የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢህአዴግ ጭሰኛ ሆኗል፡፡ የአፄው ሥርዓት እንኳን ይህን አላደረገም፡፡ ኢህአዴግ የሕዝቡ “የዓይን ቀለም ስላላማረው” ሕዝቡን ከመሬቱ ነቅሎ፣“የሚያምር የዓይን ቀለም ባላቸው ፈረንጆች ለመተካት እየሞከረ ነው! የሀገሪቱን የወርቅ ማዕድናት ለፈረንጆች ወይም“ፈረንጅ ለሚመስሉ ሰዎች” ሰጥቶ የትርፍ ተካፋይ ሆኖአል ኢህአዴግ እኛ ኢትዮጵያውያንን በመጣለት ሁሉ እየከፋፈለ እርስ በእርስ ቢያናቁረን ዝም ብለን ከተመለከትን፣መጥፎ ነገር ተገዢ ሆነናል ማለት ነው፡፡ ኢህአዴግ የሰዎች ስብስብ ነው፤እናም ኢህአዴግ “በስሜ ማሉ፣አምልኩኝ፣ስገዱልኝ” ሲል አሜን ብለን ከተቀበልን፣የፈጣሪ ፀጋ ሁሉ ከእኛ ይርቃል፡፡ ስለዚህ፣ፆምና ፀሎታችንን አጥብቀን እንቀጥላለን፤በንፁሕ ልቦና፡፡ ኃጢያት እየሠሩ ቤተክርስቲያንም ሆነ መስጊድ መሄድ ፈጣሪን እንደ ማታለል ይቆጠራል፡፡ እየሰከሩ፣ጫት እየቃሙ፣ሲጋራና ሀሺሽ እያጨሱ ፍቅር የለም፤ጥላቻና ሞት ነው! የኢትዮጵያ! ወጣቶችን ወደ “የወሲብ ቁስ አካልነት” ለማውረድ የሚሞክረውን ኢህአዴግ በፆም በፀሎት ብቻ ሳይሆን፣በሰላማዊ ትግል ስልቶች መፋለም ይገባናል፡፡ ታሪካዊ ዋጋ የተከፈለበትን ታሪካዊ ውርስ የሆነ መሬት ለባዕዳን አንሰጥም ብለን እንጩህ! “ከእናት ሀገራችን ቅድስት ኢትዮጵያ ማህፀን የተገኘውን ወርቅ ኢህአዴግና ባዕዳን እንዲዘርፉት አንፈቅድም” እያልን ድምፃችንን እናሰማ! ከኢኮኖሚ ልማት አኳያ፣እንዴት አንድ ሀገር የወርቅ ማዕድኑን ለባዕዳን ይሸጣል በሌላ በኩል፣በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵየ ሕዝብ ፀጥ ለጥ ብሎ በኢህአዴግ “በጊንጥ እየተገረፈ ነው፡፡ እየተራበና ከአፉ እየነጠቀ ለኢህአዴግ መንግሥት ግብር /ቫት/ እየከፈለ ነው፡፡ አፅመ ርስቱን በአዋጅ ሲነጠቅ ዝም ብሎ እየተገዛ ነው፡፡ መከራው የበዛበት ሀገር ጥሎ በአራቱም ማዕዘናት እየተሰደደ ነው፡፡በሀገራችን በኢትዮጵያ ደሞክራሲያዊ ሥርዓት በትግል ሊገነባ ይችላል ብሎ ሕዝቡ የሚያምን አይመስለኝም፤ ከባሕላዊና ጥንታዊ አስተሳሰቡ ገና ሙሉ በሙሉ አልተላቀቀም፡፡ እንዲያውም ኢህአዴግ “ኑ ውጡና አወድሱኝ፣ስገዱልኝ፣አደግድጉልኝ” እያለ ሲሰራ፣ በነቂስ እየወጣ ኢህአዴግን ያኑርልን” እያለ ውዳሴ-ኢህአዴግ ያስተጋባል፡፡ እርግጥ፣በልቡ ሌላ ነገር ይሆናል የሚያስበው፤ “ፈጣሪ ከዚህ ጭራቅ መንግሥት ገላግለን” የሚል ሊሆን ይችላል፤ግን አሁንም እግዚአብሔር ካልፈቀደ በስተቀር በሀገራችን ለውጥ ይመጣል ብሎ የሚያስብ አይመስለኝም፡፡ ኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚቃወም በኢትዮጵያ መሬት እንዲኖር አልፍቅድም በማለት ላለፉት ዓመታት በትጋት ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ገዢው ፓርቲ የሃይማኖት ተቋሞችን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚሰብኩ ካድሬዎች የሚርመሰመሱበት ከማድረግ ጀምሮ የመንግስት ሠራተኛውን፣ መምህሩን፣ ተማሪውን፣ አርሶአደሩን (አርብቶ አደሩን) ነጋዴውን በአጠቃላይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፀበል በግድ በዘመቻ ሲያጠምቅ የከረመው ኢህአድግ አስርቱን የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ትዕዛዛትን አውጥቶ በማስፈፀም ላይ ይገኛል፡፡

No comments:

Post a Comment