Thursday, December 18, 2014

መድረክ የሰላማዊ ሰልፉን አካሄደ

ከ ጎልጉል 

medrek8

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እሁድ ዕለት ያቀደውን ሰላማዊ ሠልፍ በ37 መፈክሮች በማጀብ አካሂዶዋል፡፡
medrek3አብዛኛዎቹ መፈክሮች ምርጫን፣ ምርጫ ቦርድን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁኔታን፣ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመሠረታዊ አገልግሎቶች መቆራረጥና መንግሥትን ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲወጣ የሚጠይቁ ነበር፡፡
ከመፈክሮቹ መካከልም “ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንጂ በአስመሳይ ፕሮፖጋንዳ፣ በኃይልና በተፅዕኖ አይገነባም”፣ “የአገራችን ችግሮች በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሚገለጽ የሕዝብ ውሳኔ እንጂ በኃይል ዕርምጃ አይፈቱም”፣ “ከምርጫ በፊት የምርጫ ውድድር ሜዳው የሚስተካከልበት ውይይትና ድርድር ይካሄድ”፣ ወዘተ የሚሉ መፈክሮች ተካተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሕዝቡ በ1ለ5 መረብ አፈናና ቁጥጥር ከሚካሄድ የምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ነፃ እንዲሆን የሚጠይቁና ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ እንዲቋቋም የሚጠይቁ መፈክሮችም ተካተዋል፡፡
በሰላማዊ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ የሚካሄደው እስራትና ወከባmedrek7እንዲቆም፣ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ለገዥው ፓርቲ የሚያሳዩትን ወገንተኝነት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፣ በልማት ስም በሕገወጥና ግብታዊ በሆነ መንገድ ሕዝብን ማፈናቀል እንዲቆም፣ የውኃ፣ የመብራት፣ የትራንስፖርትና የስልክ አገልግሎቶች ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ መፈክሮችም የሠልፉ አካል እንደሆነ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡
ሰላማዊ ሠልፉ ከአራት ኪሎ በስተምሥራቅ ከሚገኘው የግንፍሌ ድልድይ በመነሳት በቀበና ወንዝ ድልድይና በባልደራስ በኩል አድርጐ ወረዳ 8 ኳስ ሜዳ (ድንበሯ ክሊኒክ ፊት ለፊት) ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ ጀምሮ ከቀኑ በሰባት ሰዓት እንደተጠናቀቀ ተገምቶዋል፡፡ (ከሪፖርተር የተወሰደው ተሻሽሎ እንደቀረበ)

No comments:

Post a Comment