ዛሬ (May 6/2014) በኦሮሚያ ክልል በደምቢዶሎ ከተማ ሕዝብ ላነሳው ጥያቄ የመንግስት ምላሽ ጥይት ሆነ፤ ውጥረቱ ቀጥሏል የአንዲት ሴት ልጅ ሕይወት እንደጠፋ ተነግሯል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ትምህርት ተቋሞች ውስጥ የተነሳው ተቃውሞ እየተቀጣጠለ በተለያዩ ከተሞች እየተዛመተ ሲሆን በዛሬው ዕለት በደምቢዶሎ ከተማ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የመንግስት ወታደሮች የሃይል እርምጃ መውሰዳቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከስፍራው ዘገቡ።
እንደምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ ደምቢዶሎ ከተማ የመንግስት ወታደሮች በሰልፈኞች ላይ የጥይት እሩምታ ያወረዱ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወገኖች መጎዳታቸውንና የህክምና መስጫ ጣቢያዎችም በቁስለኞች መጨናነቃቸውን እንደምንጮቻችን ዘገባ ከሆነ ደምቢዶሎ ከተማ የመንግስት ወታደሮች በሰልፈኞች ላይ የጥይት እሩምታ ያወረዱ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ወገኖች መጎዳታቸውንና የህክምና መስጫ ጣቢያዎችም በቁስለኞች መጨናነቃቸውን
ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል። በዛሬው ተቃውሞ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ ባይኖርም ከሌሎች ወገኖች
ባገኘነው መረጃ የአንዲት ለጊዜው ስሟና ማንነቷ ያልታወቀ ሴት ልጅ ሕይወት ጠፍቷል።
ባገኘነው መረጃ የአንዲት ለጊዜው ስሟና ማንነቷ ያልታወቀ ሴት ልጅ ሕይወት ጠፍቷል።
ከአዲስ አበባ 650 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደምቢዶሎ ከተማ ያለው ውጥረት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ
አልበረደም።
አልበረደም።
ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሷት ትመለሳለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት “አዲስ አበባን እና የኦሮሚያ ልዩ ዞንን በልማት ለማስተሳሰር የተዘጋጀው የጋራ ማስተር ፕላን ልዩ
ዞኑን ብሎም አጠቃላይ የኦሮሚያን ክልል የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው” ሲል ገለጸ። መንግስት በምእራብ ሸዋ ዞን የዞኑ
ነዋሪዎችና የመንግስት ተወካዮች ጋር አካሄድኩት ባለው ውይይት “በውይይቱ በዞኑ የተወሰኑ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን
ሁከትና ብጥብጥ ተከትሎ በጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመትን አውግዘዋል” ሲል በሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች በኩል
ዜናውን አሰምቷል። ይህን ውይይት የመሩት ውይይቱን የመሩት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር
ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ወይዘሮ አስቴር ማሞ “ማስተር ፕላኑ
የኦሮሚያን ልዩ ዞንና የክልሉን ተጠቃሚነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው” ሲሉ መናገራቸውን የመንግስት ሚድያዎች ዘግበዋል።

No comments:
Post a Comment