Thursday, April 3, 2014

“የእሪታ ቀን” እንዲሰረዝ የኢህአዴግ መንግስት ጠየቀ

በአንድነት ፓርቲ አማካኝነት – መጋቢት 28 ቀን፣ 2006 ሊደረግ የነበረው የ እሪታ ቀን በአዲስ አበባ መስተዳድር ተቃውሞ ገጥሞታል። ከአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የወጣው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ከሆነ፡ ሰልፈኞቹ የሚሄዱበት ስፍራ የተከለከለ በመሆኑ የሰላማዊ ሰልፉን ጥያቄ እውቅና አንሰጠውም ብሏል። ቀበና መድሃኔአለም ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ተነስቶ በፒያሳ እና ቸርችል ጎዳና አድርጎ፤ ጥቁር አንበሳ ድላችን ሃውልት ጋር ይጠናቀቅ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት… መንገዱ የባቡር መስመር የሚዘረጋበት፣ ትራፊክ የሚበዛበት እና ሆስፒታል የሚገኝበት መሆኑን በመግለጽ ነው፤ ለሰልፉ እውቅና የነፈገው። ይህ በ’ንዲህ እንዳለ የአንድነት ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰልፉን የሚያካሂድ መሆኑን ገልጿል። ሆኖም በፓርቲው በኩል የተሰጠ ዝርዝር ማብራሪያ ወይም ኦፊሴላዊ መግለጫ የለም። ምናልባት ፓርቲው ተለዋጭ ቀን እና ቦታ ይጠይቅ ይሆናል… እውቅና ከተነፈገና ለሌላ ጊዜ የሚያስተላልፈው ከሆነ ጉዳዩን በቴሌቪዥን እና በሬድዮ ማሳወቅ ሳይኖርበት አይቀርም። ለማንኛውም ከአንድነት ፓርቲ የሚሰጥ ኦፊሴላዊ መግለጫ ካለ ይዘንላቹህ እንቀርባለን።


No comments:

Post a Comment