To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Monday, September 23, 2013
ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብሰበው ስዊድን ገቡ
ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብሰበው ስዊድን ገቡ
(ዘ-ሐበሻ) የጦር ሃይሎች የሎጂስቲክስ ዋና ሐላፊ የነበሩት ሌ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ቤተሰቦቻቸውን ሰብስበው ስዊድን መግባታቸውን አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ባስተላለፈው መረጃ አመለከተ። አብርሃም ገዛኢ ከሃገር የወጡት በጡረታ ለተገለሉ በኋላ ነው በማላት ”የህወሓት ሃላፊዎችማ የያዙትን ይዘው ከሀገር እየወጡ ነው። የተቸገሩ ታችኞቹ ካድሬዎች ናቸው። እንደ አለቆቻቸው ወደ ዉጭ በመኮብለል የግል ደህንነታቸው መጠበቅ አይችሉም።” ሲል ትችቱን አስፍሯል።
ጄነራል ገዛኢ አበራ በሱዳን አቢ ግዛት ሰፍሮ የነበረውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል የመሩ ናቸው።
ከአንድ ዓመት በፊት የግንቦት 7 የኢትዮጵያ የጥናት ቡድን ባሰራጨው ምስጢራዊ መረጃ ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን የጦር አለቆች ከፍተኛ የሆነ ሃብት እንዲያካብቱና ዘረፋ እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ለተለያዩት የጦር መኮንኖች ሟቹ ጠ/ሚ/ር በ1989 ለአ/አበባ አስተዳደርና ለመከላከያ ሚ/ር መ/ቤት ለ25 የወያኔ የጦር መኮንኖች፣ ለእያንዳንዳቸው በሽልማት በአዲስ አበባ ውስጥ 500 ካሬ ሜትር 1ኛ ደረጃ መሬት እንዲሰጣቸው ትእዛዝ በሰጡት መሰረት ይህን መሬት የተቀበሉት ሌ/ጄነራል ገዛኢ አበራ በወር 170 ሺህ ብር የሚከራይ ቤት ቦሌ አካባቢ ሠርተው እንደሚያከራዩ ተጋልጦ ነበር።
ግንቦት 7 በአንድ ዓመት በፊት እንዳጋለጠው፦
የወያኔ የጦር መኮንኖች የአዲስ አበባን ከተማ በመዝረፍ ያከማቹት ሃብት
ተራ/ቁ ማእረግ ስም ቦታው የሚገኝበት ወርሃዊ ኪራይ በብር የዘውግ መግለጫ
1 ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ቦሌ 25,000 ከ4 ዓመት በፊት ትግሬ
2 ጄኔ ሳሞራ የኑስ ቦሌ 28,000 ትግሬ
3 ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ ቦሌ 38,000 ትግሬ
4 ሌ/ጄ ገዛኢ Aበራ ቦሌ 170.000 ትግሬ
5 ሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ ቦሌ 38,000 ትግሬ
6 ሌ/ጄ ሳእረ መኮንን ቦሌ 35,000 ትግሬ
7 ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ቦሌ 1,2 ሚሊየን መሬቱን የሽጠ አገው
8 ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት ቦሌ 2.5 ሚሊዮን መሬቱን የሽጠ ትግሬ
9 ሜ/ጄ አብርሃ ው/ገብርኤል ቦሌ 34,000 ትግሬ
10 ሜ/ጄ ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ 28,000 ትግሬ
11 ሜ/ጄ አባ ዱላ ገመዳ ቦሌ 45,000 ትግሬ/ኦርሞ
12 ሜ/ጄ አለሙ አየለ ቦሌ መሬቱን በ1.7 ሚሊዮን የሸጠ አገው
13 ሜ/ጄ ስዮም ሃጎስ ቦሌ 28,000 ትግሬ
14 ሜ/ጄ ሃየሎም አርAያ ቦሌ ? ትግሬ
15 ሜ/ጄ ገ/እግዚአብሄር መብራቱ ቦሌ 40,000 ትግሬ
16 ሜ/ጄ ባጫ ደበሌ ቦሌ 20,000 ኦሮሞ
17 ብ/ጄ ታደሰ ጋውና ቦሌ መሬቱን 1.2 ሚሊዮን ብር የሽጠ ትግሬ
18 ብ/ጄ ተክላይ አሽብር ቦሌ 60,000 ትግሬ
19 ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳነ ቦሌ 30,000 ትግሬ
20 ብ/ጄ ፓትሪስ ቦሌ 34,000 ትግሬ
21 ብ/ጄ መስፍን አማረ ቦሌ 23,000 ትግሬ
22 ብ/ጄ ምግበ ሃይለ ቦሌ 20,000 ትግሬ
23 ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ ቦሌ 22,000 ትግሬ
24 ኮ/ል ታደስ ንጉሴ ቦሌ 48,000 ትግሬ
25 ኮ/ል ጸሃየ መንጁስ ቦሌ መሬቱን 1.2 ሚሊዮን የሽጠ ትግሬ
ከእነዚህ የጦር አለቆች ውስጥ ባሁኑ ሰዓት በተራ ቁጥር 1, 8, እና 17 ከስርአቱ ውጭ ሲሆኑ፣ በተራ ቁጥር 14 እና 24 ያሉት ደግሞ በህይወት የሌሉ ናቸው።
ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ ወያኔ ለጦር አለቆቹ የሚሰጠው ጥቅማ ጥቅም የሚከተለውን ይመስላል።
እነዚህ የጦር አለቆች በነጻ መሬት ወስደው ቤት በዘረፋ ከሰሩ በህዋላም በከተማው ውስጥ በመንግስት እጅ ከሚገኙ ምርጥ ቪላዎች መሃል ተመርጦ በተሰጣቸው ቤቶች ውስጥ በነጻ መኖር ቀጥለዋል።
የውሃ የመብራት የስልክ ወጭዎችን ሙሉ በሙሉ የወያኔ መንግስት ይከፍላል። እነዚህ ሞልቃቃና ቅምጥል የጦር አለቆች በሚኖሩበት ቪላ ውስጥ ብርዱን አልቻልንም በማለት ቤታችውን ሙሉ በሙሉ በውድ ምንጣፍ ማሽፈናቸው አልበቃ ብሉዋቸው ከፍተኛ የኤሌትሪክ ሃይል ፍጆታ የሚያስፈልጋችው የኤሌትሪክ የቤት ማሞቂያ መሳሪያዎች በየክፍሉ አስገጥመዋል። ምንጣፍ ለሚጠርገው የኤሌትሪክ መጥረጊያ ሆነ ለኤሌትሪክ ማሞቂያዎቹ የሚወጣው ክፍተኛ ወጪ፣ እንዲሁም እንዳሻቸው ለሚያፈሱት ውሃ በነጻ ተገልጋዮች እንዲሆኑ ተደርገዋል። በእዚህ ላይ ነጻ የሆነውን የሞባይልና የቤት ስልክ አገልገሎት ስንጨምርው በነጻ የሚያገኙት አገልግሎት በሽዎች የሚቆጠር ብር ይደርሳል።
የጦር አለቆቹ ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው፣ ከእዚህም አልፎ አባትና እናቶቻቸው ሳይቀሩ እሰከ ውጭ ሃገር ድረስ በመሄድ የሚሰጥ ነጻ ህክምና ያገኛሉ።
ሁሉም የጦር አለቆች ተጨማሪ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በመቀሌ በባህር ዳር፣ አንዳንዶቹም በአ/አበባ ከተማ፣ በድጋሚ መሬት እንዲወስዱና እንዲገነቡ ተደርገዋል። ከእዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ በዱከም በናዝሬትና በሌሎች ቦታዎች ለንግድና ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ ቦታዎች በመውሰድ ይህን መሬት በቀላሉ ለማያገኙ ሌላ የሃገሪቱ ዜጎች በከፍተኛ ዋጋ በመቸብቸብ ያካበቱት ሃብት ገደብ የሌለው ሆንዋል። ታደስ ወረደ፣ ወዲ እምቤቲ፣ ፍስሃ ኪዳነ፣ ገዛኢ አበራ የተባሉት የጦር አለቆች በዚህ ድርጊት በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መሃል ናችው።
ይህ አልብቃ ብሎ እነዚህ የጦር አለቆች በመከላከያ ሚኒስትር በተያዘ ከፍተኛ የመስተንገዶ በጀት በመጠቀም የሚኖሩትን የቅንጦት ኑሮ ለተመለከተ ሃገራችን በምን አይነት የቀን ጅቦች እንደተወረረች ለማየት የሚያስችል ይሆናል። በ1992 ዓ/ም መከላከያ ሚኒስቴረ ለመስተንግዶ ብቻ የመደበው በጀት 280,000,000 (280 ሚሊዮን) ብር ነበር። በእዚሁ በ1992 ዓ/ም የሶማሊያ ክልል አመታዊ በጀት በተመሳሳይ 280 ሚሊዮን ብር እንደነበር ስናስታውስ፣ ይህ ለጦር አለቆቹ የተመደበው በጀት ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ መረዳት ይችላል የሚል እምነት አለን። በእዚህ የመስተንግዶ በጀት በመጠቀም የጦር አለቆቹ በየቀኑ ብፌ እያዘጋጁ ራሳቸውን ሲቀልቡ ከእዚህም አልፈው እንደጥንቶቹ መሳፍንት ግብር እንዲያበሉ፣ ውድ የሆኑ የውስኪ አይነቶች እንደ ውሃ እያፈሰሱ የሚኖሩበትን ሁኔታ አመቻችቶላቸዋል።
በእዚህ የመስተንግዶ በጀት አማካይነት የወያኔ የጦር አለቆች ከትንሹ ሹካና ማንኪያ ጀምሮ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ሶፋዎች የምግብ ጠረጴዛዎች አልጋዎችና ሌሎችም በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ታዋቂ ሃብታም ዘፋኞችና የፊልም ተዋንያኖች የሚገልገሉባቸውን የቤት ቁሳቁሶች መግዛት ችለዋል። የጦር አለቆቹ እነዚህን የቤት ቁስቁሶች በየአመቱ የመቀየር መብት ስለተሰጣችው በእዚህ መብት ስም የሚያባክኑት የህዝብ ሃብት እጅግ በርካታ ነው።
እያንዳንዱ የወያኔ የጦር አለቃ ከሁለት በላይ ውድና ዘመናዊ መኪናዎች ተሰጥቶታል። እነዚህ መኪናዎች በየአመቱ በአዲስ ሞዴል መኪናዎች ይተካሉ። የወያኔ ጄኔራል አንድ መኪና ለራሱ ሌላ መኪና ለሚስቱና ለልጆቹ በመውሰድ፣ እነዚህን መኪናዎች በግላቸው ያለምንም ወጪ እንዳሻቸው ከመገልገል አልፎ የኮንትሮባንድ እቃዎች ማመላለሻ አድርገው ይገለገሉባቸዋል። የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከድሬደዋ፣ ሃረር፣ ጅጅጋ አርቲሸክና ሞያሌ በማመላለሱ ስራ ተሰማርተው ከሚገኙት መሃል ጎልተው የሚታወቁት ሌ/ጄ ታደስ ወረደ፣ ሌ/ጄ ሳረ መኮንን፣ ሌ/ጄ አበባው ታደሰ፣ ሜ/ጄ ሙሉጌታ በርሀ፣ ሜ/ጄ አለሙ አየለና ሌሎችም በርካታዎች ናቸው። በሌላ መንገድም የተሰጣቸውን መኪና፣ ከመንግስት ያለምንም ገደብ ከሚወስዱት ነጻ ነዳጅ ጋር እያከራዩ የሚጠቀሙ ጄነራሎች ብዙ ናቸው። በዚህ ተግባር ከተሰማሩት በርካታዎች መሃል ሌ/ጄ ገዛኢ አበራ ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ፣ ብ/ጄ ተክላይ አሽብርን መጥቀስ ይቻላል። የመከላከያ ሚኒስቴር በ1993 አ/ም ብቻ በአንድ ግዜ ለመለስ የጦር አለቆች መገልገያ የሚሆኑ 300 ኮብራ ቶዮታ ላንድ ክሩዘር አስገብተዋል። ኢትዮጵያን በመሰለ ደሃ ሃገር ውስጥ በአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በአንድ ግዜ ብቻ ይህንን ያህል የውጭ ምንዛሪ ሲባክን አይቶ የማይደነግጥ ሃገር ወዳድ ዜጋ ይኖራል የሚል እምነት የለንም።
ከእዚህ በተጨማሪ በመከላከያ ስር ያሉ ወታደራዊ መደቦችና ክበቦች የወያኔ የጦር አለቆች የግል ንብረቶችና መገልገያዎች እንዲሆኑ ተደርገዋል። የጎልፍ ክበብ፣ መኮንኖች ክበብ፣ ደብረዘይት የአየር ሃይል ክበብና በየክልሉ የሚገኙ ትላልቅ ክበቦችን ጨምሮ እነዚህ የጦር መኮንኖች እንዳሻችው ያለምንም ወጪ የሚሰክሩባቸውና የሚዝናኑባቸው ናቸው። ወታደራዊ መደብሮቹ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲያስግቡ የተፈቀደላቸው በመሆናቸው ማንኛውም የውስጥ እቃዎቻቸውና ድርጅታቸው በልዩ በጀት የተሙዋሉላቸው በመሆናቸው ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አትራፊዎች ናቸው። ይህ ትርፍ፣ በየጦር ሰፈሩ የሚሸጠው ሳር፣ ዛፍ፣ አትክልት፣ ውዳቂ ብረታ ብረትና አላቂ እቃዎች፣ የሚረቡ የወተት ከብቶችና የሚደልቡ የስጋ በሬዎች በሙሉ የውያኔ የጦር አለቆች ተጨማሪ የግል ገቢዎች ምንጮች ናቸው።
http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/09/General-Gezae.jpg
http://www.zehabesha.com/amharic/?p=7622
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment