To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Friday, September 6, 2013
የህወሃት ክፍፍል ከሙስና እስከ ፖለቲካ አመለካከት ውጥረት…..ህወሃት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶአል ..... በአዜብ ዳፋ አቦይ ስብሃት ሊዳፋ ???
የህወሃት ክፍፍል ከሙስና እስከ ፖለቲካ አመለካከት ውጥረት…..ህወሃት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶአል
September 6 2013
ምንሊክ ሳልሳዊ
በአዜብ ዳፋ አቦይ ስብሃት ሊዳፋ ???
ሕወሓት አዲስ አበባ ላይ በግምገማዊ ውጥረት ተከሽኖ አባላቱ እርስ በእርስ እያባላ አጣብቂኛዊ ስብሰባ ተቀምጧል:: ስብሰባው ታዲያ በነአዜብ የታለመው አሉ በእባባዊ መርዛቸው ሾልከው እስካሎጡ ድረስ አቦይ ስብሀትን ነው ::አቦይ ስብሃት ቤተሰቦቻቸውን በተደላደለ ኑሮ አውሮፓ ውስጥ አንፈላሰው እያኖሩ ጣሊያን በሚገኙ ሁለት ልጆቻቸው ስም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር እያሸሹ ይገኛሉ አንደናው ይገኛሉ አንደናው ልጃቸው የሕወሓት ተተኪ ለመሆን ኮሚኒስታዊ ስልጠና በቻይና ሲወስድ የተመደበለት ባጀት ለሶስት ተማሪዎች የሚመደብ ስለሆነ የሚሉ ስሞታዎች መቅረብ ጀምረዋል ሽማግለው ደሞዙ በሺዎች የሚቆጠር ብር የሚኖረው ግን በሚሊዮኖች የሚሉ ትንኮሳዎች በነበረከት ቡድን እየተለጠፉበት ነው::
,አብዛኛው የሕወሓት ካድሬ በደብረጺሆን ጉያ የተሸሸገ ሲሆን የውሳነ ሰጪነት መሉ ስልጣኑን የተቆጣጠረው ደብረጺዮንን መከታ አድርጎ በሙስና የሚተየቁ ካሉ የጠየቁ ዘንድ ግፊት እያደረጉ ነው::የብኣዴኑ በረከት ስምኦን በሞተ የስልጣን እርከን ላይ በመሆን እየተንደፋደፈ በመለስ ራእይ ውስጥ ተሸሽጎ ለማምለጥ ቢሞክርም በፍርሃት እና በስጋት ራሱ አስሮ ውርደቱን እየጠበቀ ነው:ሲሉ ካድሬዎቹ ይተቹታል::የደህንነት ባለስልጣኑን ወልደስላሴን መያዝ ተከትሎ በስብሰባ የተወጠረው ሕወሓት ማን ወደ ሙስናው ዘብጥያ ይውረድ የሚለውን ወይንም የረጋጋ የሚለውን ለመናገር በአጣብቂኝ ውስጥ ነው::
በሁለት ሃይሎች መካከል የተነሱ ፍትጊያዎች ማብቂያቸው በሰረ ሙስና እና በመለስ ራእይ ስም ውስጥ እየተሹለከለከ ነው::የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም የመለስን ራእይ ሽፋን አድርጎ የሚውረገረገው የበረከት ቡድን በአቦይ ስብሃት እና አባይ ጸሃዬ በኩል በትችት ፍልጥ የተመታ ሲሆን መለስ ዜናዊን በተመለከተ በሚደረጉ የፖለቲካ ፍጆታዎች ላይ የላቸውን አቋም አቶ በረከት በፍጥነት እንዲያጡ ሲደረግ ከሚዲያው ጎራም ተጠልዘው ወተዋል::
ሕወሓት ሰላሙን አጥቷል::በቀጭን ገመድ ታንቆ ለመሞት እያጣጣረ ያለበት ሰአት ላይ ካድረው ስብሰባ ተቀምጦ ድርጅታችንን እናድን እያለ ሲሆን የመለስ ድርጅታዊ የማፊያዊ አመራር በሞት ከተኮላሸ በኋላ ድርጅቱ እና አባላቱ በተለይ አመራሩ ተከፋፍሎ እየተባላ እየተናከሰ ነው::
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment