Saturday, January 3, 2015

ገርጂ ኮንዶሚኒየም አንድ ብሎክ ህንፃ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ… // በጋምቤላ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት 79 ሰዎች መገላቸውን መንግስት ገለጸ


 በቦሌ ክፍለከተማ ገርጂ ቁጥር አንድ ኮንደሚንየም ተብሎ በሚጠራው በብሎክ ሃያ አንድ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች የኮንደሚንየም ቤቱ በላያችን ላይ ሊፈርስ ነው ሲሉ ፍርሃታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ሳይት የሚገኘው ብሎክ ሃያ አንድ ቤት ግርግዳው ከመሰረቱ እስከጣራው ድረስ እየተሰነጣጠቀ መሆኑን የዘገበው ሰንደቅ ነዋሪዎቹም የግርግዳው የስንጥቆቹ ክፍተቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መሄዱን ተናግረዋል። ድሬ ትዩብ 
ከዚህም በተጨማሪ ህንፃው ከቁመናው የመዛባት ባህሪ እየታየበት ስለሄደ ነዋሪዎቹ የቤቶቻቸው መዝጊያዎች ሳይቀሩ እየተዛነፉ ለመክፈትና ለመዝጋት በመቸገራቸው በየጊዜው እያሰቆረጡ ቁመታቸውን ለማስተካከል መገደዳቸውን ተጠቅሷል።
የብሎኩ ነዋሪዎች ቤት ከውስጥም ከውጪም በከፍተኛ ደረጃ የመሰንጠቅ ችግር የገጠመው ሲሆን ስንጥቆቸም በሁሉም የብሎኩ ነዋሪዎች ቤቶች የመስፋት ሁኔታ ይታይባቸዋል።
ነዋሪዎቹ የህንፃው ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመሄዱ በላያቸው ላይ ሳይፈርስ የሚመለከተው የመንግስት አካል መፍትሄ እዲሰጣቸውም ጠይቀዋል። የችግሩ መንስዔ በብሎኩ አቅራቢያ እጅግ በርካታ የኮንስትራክሽን ግዙፍ መኪናዎች በየቀኑ ማለፋቸው ነው ተብሎ ቢጠቀስም የአፈር ችግር፣ እንዲሁም የህንፃው መሰረትም የችግሩ መነሾ ነው ተብሏል..
በጋምቤላ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት 79 ሰዎች መገላቸውን መንግስት ገለጸ
ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በጋምቤላ ክልል በጎደሬ ወረዳ ከመጋቢት እስከ ጳጉሜ በነበሩት ግጭቶች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ12 አይበልጥም በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቢቆይም፣ አቃቢ ህግ የክልሉን ባለስልጣናት ለመክሰስ ባቀረበው የክስ ቻርጅ ላይ 79 ሰዎች መገደላቸውን ፣ 273 ቤቶች መቃጠላቸውን ከ13 ሺ በላይ ዜጎች እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸውን ገልጿል።
አንዳንድ ወገኖች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር በመቶዎች እንደሚቆጠሩ ሲገልጹ፣ ኢሳት 60 ሰዎች መገደላቸውን የሞአቾችን ስም ዝርዝር ይፋ በማድረግ ዘገባ አቅርቦ ነበር።
አቃቢ ህግ መንግስት አምኖ የሾማቸው የክልሉ ባለስልጣናት ግድያውን እንዳስፈጸሙና ግጭት እንዲነሳ እንዳደረጉ በክስ ቻርጁ ላይ አምልክቷል። የክልሉ ልዩ ሃይል አዛዥ አቶ ያእቆብ ሸራተንና የመዠንገር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትንሳኤ ራጃን ጨምሮ 35 የክልሉ ባለስልጣናት ክስ ተመስርቶባቸዋል።
የክልሉ ባለስልጣኖች በሚጤ ህዝቡን ሰብስበው ከተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች የመጡ ሰዎች የእርሻ ቦታቸውንና የቡና ተክላቸውን ለክልሉ ተወላጆች እንዲያካፍሉ፣ ይህን የማያደርጉ ከሆነ ግን ከክልሉ እንዲወጡ ቅስቀሳ ማድረጋቸው በክሱ ላይ ተመልክቷል።
የግጭቱ መነሻ በአካባቢው የሚታየው መሬት ወረራ መሆኑ በተደጋጋሚ ቢገለጽም፣ በዚህ በኩል ተጠያቂ የሆኑ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ለፍርድ አለመቅረባቸው የፍርድ ሂደቱ ተአማኒነት እንዲያጣ አድርጎታል። የቀድሞ የህወሃት አዛዦች የአካባቢው መሬት በስፋት እየቀሙና ነዋሪውን እያፈናቀሉ መሆናቸው በተጨባጭ ማስረጃ ቢረጋገጥም እስካሁን ምንም አይነት እርምጃ ሳይሰወድባቸው መቅረቱ በዜጎች መካከል ያለውን ልዩነት የሚያሳይ መሆኑን አዲስ አበባው ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በመጪው ጥር አጋማሽ የክሱን ዝርዝር ለማዳመጥ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ ‪


ታኀሳስ 23/04/2007 ዓ ም


የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ታጋዮች ከወልቃይት ጠገዴና አርማጭሆ ህዝብ ጎን በመሰለፍ በዘረኛውን ናዚ ወያኔ መከላከያና ከትግራይ ተስፋፊ ታጣቂዎች ጋር ከባድ ውጊያ አያካሄደ ይገኛል።አዴሃን ከኤርትራ/ሻቢያ/ ምድር ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለውጤት የሚያበቃውን የአደረጃጀት ስልት በመንደፍ /በመቀየስ/ ወደ ተጨባጭ ስራ መግባቱን ይፋ ማድረጋችን ይታወሳል።
አዴሃን በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም የወያኔ ስርአት አረመኔያዊ አገዛዝ ግፊት ቀማሽ ለሆነው ከወልቃይት ጠገዴና አርማጭሆ አካባቢ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም ህውሃት በወረራ የያዛቸውን የወልቃይት ጠገዴና የአርማጭሆ ሰፋፊ ለም መሬቶችን አስተማማኝ ለማድረግ እና አዳዲስ መሬቶችን ለመያዝ የነደፈውን እስትራቴጂ ተግባራዊ ሊያደርግ እየተዘጋጀ መሆኑንና ታላቋን ትግራይ ለማስፋት ባለው ህልም መሰረት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን August 19 – 2014 ” ህወሃት በወልቃይትና ጠገዴ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የዘር /ማጽዳት/ፍጅት ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው።” በሚል ርዕስ መረጃዎችን ይፋ አድርገን ነበር።
በሌላ በኩልም November 19- 2014” የጠገዴ ወረዳ ህዝብ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም በማለት እራሱን ለመከላከል እየተዘጋጀ ነው።” በሚል ርዕስ ለህዝብ የተበተነውን የትግል ጥሪ ፓምፕሌት ጨምረን ይፋ አድርገን እነደነበር ይታወሳል። በመሆኑም ወያኔ የትግራይን የመስፋፋትና አማራውን የማጥፋት አባዜውን እውን ለማድረግ፦ ህዝቡም እራሱን ለመከላከልና ማንነቱን ለማስከበር በጀግንነት ዱር ቤቴ ብሎ የራሱን የጎበዝ አለቃ መርጦ በከባድ መሳርያ የሚታገዘውን የወያኔ ሰራዊት በከፍተኛ ደረጃ እየመከተ ይገኛል። በመሆኑም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በቅርብ የሚገኘው አማራውና እንዲሁም በተለያየ መንገድ ወያኔን ለማሰወገድ በትግል ላይ ያሉ ድርጅቶች ከህዝብ ትግል ጎን እንዲቆሙ አሳስበንም ነበር። ይኸው ዛሬ የወያኔ የጸጥታ መከላከያና፡ የትግራይ ታጣቂዎች እንዲሁም ስውር ነብስ ገዳይ ደህንነቶች በማን አለብኝነት በሰላማዊ ህዝብ ላይ ከታህሳስ 17- 2007 ጀምሮ ግልጽ ጦርነት ከፍተዋል። ህዝቡም እራሱን ለመከላከል ሲል በሚቻለው ሁሉ ራሱንና ሀገሩን ከባዳዎች ስብስብ ለመከላከል ዘረኛውን አባገነን ስርአት እየተፋለመው ይገኛል።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ታጋዮችም ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተልን ከህዝቡ ጎን በመሰለፍ ታረካዊ ግዳጃችንን እየተወጣን እንገኛለን። በአሁኑ ጊዜ አረመኔው የወያኔ ስርአት በርካታ የመከላከያ ሃይሉን ከትግራይ ግንባሮችና ከመሃል ሀገር ሳይቀር ወደ ስፍራው በማንቀሳቀስ የሚያካሄደውን የማንነት ትግል በሃይል ለመጨፍለቅ እርብርብ እያደረገ ይገኛል ። በተለይ የናዚው ወያኔ የግፍ አገዛዝ ሰለባ ላለመሆን እራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን ህጻናት፣ ሽማግሌዎችንና ሴቶች ላይ አረመኔያዊ የሆነ ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።አሁን ባለንበት ሰአት የወልቃየት ጸገዴና አርማጭሆ ህዝብ በከፍተኛ ወኔ እየተጠራራ እየተደራጀ የጀመረውን የነጻነት ትግል ለማጠናከር ዱር ቤተ ብሎ ከያለበት የእከተተ ይገኛል ።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄም የቻለውን ሁሉ በማድረግ ከህዝቡ ጎን ተሰልፎ የራሱን ታሪካዊ አስተዋፆ በማበርከት ህዝቡን የድል ባለቤት ለማድረግ ተግቶ በሰራት ላይነው ። ሁኔታው የሚመለከታችሁና የሚያሳስባችሁ ወገኖች ሁሉ የተቀጣጠለውን ካለው ህዝባዊ ትግል ጎን እንድትሰለፉ አዴሃን ወቅታዊ ጥሪ ያቀርባል።በሁሉም መስክ ትግሉን ለማጠናከር በየቀኑ ሁኔታውን በመከታተል፣ እንድትሳተፉ በድጋሜ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
፠ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ፠
ሞት ለወያኔ
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ስ\አስፈፃሚ

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ #Ethiopia               
ታኀሳስ 23/04/2007 ዓ ም
                  
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ታጋዮች ከወልቃይት ጠገዴና አርማጭሆ ህዝብ ጎን በመሰለፍ  በዘረኛውን ናዚ ወያኔ መከላከያና ከትግራይ ተስፋፊ ታጣቂዎች ጋር ከባድ ውጊያ አያካሄደ ይገኛል።አዴሃን ከኤርትራ/ሻቢያ/ ምድር ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ለውጤት የሚያበቃውን የአደረጃጀት ስልት በመንደፍ /በመቀየስ/ ወደ ተጨባጭ ስራ መግባቱን ይፋ ማድረጋችን ይታወሳል።

አዴሃን በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም የወያኔ ስርአት አረመኔያዊ አገዛዝ ግፊት ቀማሽ ለሆነው ከወልቃይት ጠገዴና አርማጭሆ አካባቢ ልዩ  ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰን እንገኛለን።  ከዚህ ቀደም ህውሃት በወረራ የያዛቸውን የወልቃይት ጠገዴና የአርማጭሆ ሰፋፊ ለም መሬቶችን አስተማማኝ ለማድረግ እና አዳዲስ መሬቶችን ለመያዝ የነደፈውን እስትራቴጂ ተግባራዊ ሊያደርግ  እየተዘጋጀ መሆኑንና ታላቋን ትግራይ ለማስፋት ባለው ህልም መሰረት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን August 19 – 2014 ” ህወሃት በወልቃይትና ጠገዴ ህዝብ ላይ ተጨማሪ  የዘር  /ማጽዳት/ፍጅት ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው።” በሚል ርዕስ መረጃዎችን ይፋ አድርገን ነበር። 

በሌላ በኩልም November 19- 2014” የጠገዴ ወረዳ ህዝብ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም በማለት እራሱን ለመከላከል እየተዘጋጀ ነው።” በሚል ርዕስ ለህዝብ የተበተነውን የትግል ጥሪ ፓምፕሌት ጨምረን ይፋ አድርገን እነደነበር ይታወሳል። በመሆኑም ወያኔ የትግራይን የመስፋፋትና አማራውን የማጥፋት አባዜውን እውን ለማድረግ፦  ህዝቡም እራሱን ለመከላከልና ማንነቱን ለማስከበር በጀግንነት ዱር ቤቴ ብሎ የራሱን የጎበዝ አለቃ መርጦ በከባድ መሳርያ የሚታገዘውን የወያኔ ሰራዊት በከፍተኛ ደረጃ እየመከተ ይገኛል። በመሆኑም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በቅርብ የሚገኘው አማራውና እንዲሁም በተለያየ መንገድ ወያኔን ለማሰወገድ በትግል ላይ ያሉ ድርጅቶች ከህዝብ ትግል ጎን እንዲቆሙ አሳስበንም ነበር። ይኸው ዛሬ የወያኔ የጸጥታ መከላከያና፡ የትግራይ ታጣቂዎች እንዲሁም ስውር ነብስ ገዳይ ደህንነቶች በማን አለብኝነት በሰላማዊ ህዝብ ላይ  ከታህሳስ 17- 2007 ጀምሮ  ግልጽ ጦርነት ከፍተዋል። ህዝቡም እራሱን ለመከላከል ሲል በሚቻለው ሁሉ ራሱንና ሀገሩን ከባዳዎች ስብስብ ለመከላከል ዘረኛውን አባገነን ስርአት እየተፋለመው ይገኛል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ታጋዮችም  ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተልን ከህዝቡ ጎን በመሰለፍ ታረካዊ ግዳጃችንን እየተወጣን እንገኛለን። በአሁኑ ጊዜ አረመኔው የወያኔ ስርአት በርካታ የመከላከያ ሃይሉን ከትግራይ ግንባሮችና ከመሃል  ሀገር ሳይቀር ወደ ስፍራው በማንቀሳቀስ  የሚያካሄደውን የማንነት ትግል በሃይል ለመጨፍለቅ እርብርብ እያደረገ ይገኛል ።  በተለይ የናዚው ወያኔ የግፍ አገዛዝ ሰለባ ላለመሆን እራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን  ህጻናት፣ ሽማግሌዎችንና ሴቶች ላይ አረመኔያዊ  የሆነ ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።አሁን ባለንበት ሰአት የወልቃየት ጸገዴና አርማጭሆ ህዝብ በከፍተኛ ወኔ እየተጠራራ እየተደራጀ የጀመረውን የነጻነት ትግል ለማጠናከር ዱር ቤተ ብሎ ከያለበት የእከተተ ይገኛል ።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄም የቻለውን ሁሉ በማድረግ ከህዝቡ ጎን ተሰልፎ የራሱን ታሪካዊ አስተዋፆ በማበርከት ህዝቡን የድል ባለቤት ለማድረግ ተግቶ በሰራት ላይነው ።  ሁኔታው የሚመለከታችሁና የሚያሳስባችሁ ወገኖች ሁሉ የተቀጣጠለውን ካለው ህዝባዊ ትግል ጎን እንድትሰለፉ አዴሃን  ወቅታዊ ጥሪ ያቀርባል።በሁሉም መስክ ትግሉን ለማጠናከር በየቀኑ ሁኔታውን በመከታተል፣ እንድትሳተፉ በድጋሜ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
        
፠ድል  ለኢትዮጵያ ህዝብ፠
                                            
ሞት ለወያኔ
                               
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ስ\አስፈፃሚ

Thursday, January 1, 2015

“በሐውዜን ድብደባ፤ የእሥራኤል እጅ አለበት” አቦይ ስብሃት ነጋ

 "Israel played role in Hawzen bombing in Ethiopia" Sebhat Nega

በ  

ከ26 ዓመታት በፊት የደርግ መንግሥት በትግራይ ክልል በሐውዜን ሕዝብ ላይ ያካሄደው የአውሮፕላን ድብደባ በስተጀርባ የእሥራኤል መንግሥት እጅ እንዳለበት የቀድሞ የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ስብሃት ነጋ ይፋ አደረጉ። 
አቶ ስብሃት ይህን የገለፁት በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የደርግ 604 ኮር የተደመሰሰበትን የወታደራዊ ሳይንስ ጥበብ አስመልክቶ ሰሞኑን በሽሬ ከተማ በተሰናዳ የውይይት መድረክ ላይ ነው።
     አቦይ ስብሃት ሲያስረዱ፣ “የቀዝቃዛው ጦርነት ማክተምን ተከትሎ ታላቋ ሶቪየት ሕብረት መፈራረስ ጀመረች። ይህን ክስተት ተከትሎ ሶቪየት ሕብረት ከኢትዮጵያ እየወጣች መጣች። በእሷ እግር የተተካውም የሩሲያ ፌዴሬሽን ለደርግ አገዛዝ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረውን ወታደራዊ እርዳታ አቋረጠ። ይህን ዓለም ዓቀፍ የፖለቲካ ዳይናሚዝም ተከትሎ አሜሪካ መራሹ የምዕራብ ዓለም እና የእሥራኤል መንግስት ከደርግ ጋር ወዳጅ ሆኑ። የደርግ አገዛዝን መውደቅን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የጂኦ-ፖለቲካል ኃይል አሰላለፍ በመፍራት የምዕራቡ ዓለምና እሥራኤል  ደርግን ወዳጅ አድርገው በእኛ የትግል እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ እርምጃዎች መውሰድ ጀመሩ” ብለዋል።
     አያይዘውም፣ “በወቅቱ ሕወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅሙ እየጠነከረ እየመጣ በመሆኑ አሜሪካና እሥራኤል ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል። የአዲስ አበባው መንግስት ወዳጅ ስለሆኑ እንዴት ከተጀመረው የትጥቅ ትግል ሊያድኑት እንደሚችሉ ብዙ መንገዶችን ሞክረዋል። በጊዜው ደርግን ለማትረፍ ያልሞከረ የምዕራብ ሀገር አልነበረም። ሁሉም የሚችለውን አድርጓል። አሜሪካ ለማደራደር ስትሞክር እሥራኤል ግን የተለየ ሚና ወሰደች” ሲሉ ወንጅለዋል።
     “አሜሪካ አንዴ ወደ ሮማ ሌላ ጊዜ ወደ ለንደን እንድንመጣ ጠራችን።  ሮማ ላይ ጂሚ ካርተር አስጠርቶን የነበረ ቢሆንም፣ የደርግ ልዑካን ቡድን እናንተ ስለኢትዮጵያ ምን ያገባችኋል አሉን። ወደ ለንደን ተጠርተን ስንሄድ ግን ሁሉን ነገር ስለጨረስን ደርግን ጥለን ነበር” ብለዋል።
     እስራኤል ግን ወደ ሮማ ከመሄዳችን በፊት፣ ደርግን በጦር መሳሪያ በማስታጠቅ ጀምራለች። ደርግ የታጠቀውን የክላስተር ቦምብ እ.ኤ.አ ጁን 22 ቀን 1988 ሐውዜን በገበያ ቀን ህዝቡ ላይ አዘነበው። በጥቃቱም ከ2ሺ 500 በላይ ህዝብ ማለቁን ተናግረዋል። አያይዘውም፤ “ይህ ሁሉ የህዝብ ዕልቂት በእሥራኤል አስታጣቂነት የተፈጸመ ነበር” ሲሉ አቦይ ስብሃት ለተሰብሳቢው በሃዘን ተውጠው አስረድተዋል።
     የቀድሞ የደርግ መንግሥት ርዕሰ ብሔር የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም ወደ ዙምባቡዌ የሸሹት በምዕራብ ሀገሮች ድጋፍ መሆኑ ሲነገር ነበር። ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማሪያም በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል የሞት ፍርድ ቢተላለፍባቸውም አንዳቸውም የምዕራቡ ሀገራት የዙምባቡዌ መንግስት አሳልፎ እንዲሰጥ ግፊት አድርገው አያውቁም።

ፖሊስ የደብረማርቆስ ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ ነው



ነገረ ኢትዮጵያ // ኢካዴፍ  
Protest in Bahirdar, Ethiopia


ፖሊስ የደብረ ማርቆስ ተማሪዎችን እየደበደበ ነው፡፡ የትናንትናው ተቃውሞ በኢሳትና በሌሎች ሚዲያዎች መተላለፉን ተከትሎ ‹‹ማን ነው ከኢሳትና ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር እየተደዋወለ መረጃ የሚሰጠው?›› እንዲሁም ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ካለ ተናገሩ››  በሚል ተማሪዎቹን አሳልፈው እንዲሰጡ ከፍተኛ ደብደባ እየፈጸመ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡
 ፖሊስ አሁንም ተማሪዎችን እየፈለገ እያሰረ መሆኑም ተገልጾአል።
——————

• ‹‹ኢህአዴግ አይገዛንም!›› ተማሪዎቹ
 ፖሊስ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን የተቃወሙ የደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎችን እያፈሰ እያሰረ እንደሚገኝ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ በትናንትናው ዕለት ኢህአዴግን የሚተቹ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳታቸው ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ ከመደረጉም ባሻገር ጥያቄ የሚያነሱት ላይ ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ጠዋት ጥያቄ ያነሳሉ የተባሉት ተማሪዎች ስልጠና ወደሚሰጡባቸው ትምህርት ቤቶች ግቢ እንዳይገቡ ከመደረጉም ባሻገር የድብዛ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስልጠናውን መቃወማቸውን ተከትሎ ፖሊስ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሰሙ የተክለሀይማኖት መልስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እርምጃውን በመቃወም ለድብዛ ተማሪዎች ድጋፍ መስጠታቸው ተገልጾአል፡፡
የሁለቱም ትምህርት ቤት ተማሪዎች በጋር በመሆን ከተማው አደባባይ ላይ በመውጣት ‹‹አህአዴግ አይገዛንም፣ ኢህአዴግ ሌባ፣…›› የመሳሰሉ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለጻቸውን ተከትሎም ፖሊስ ተማሪዎቹን እያፈሰ ወዳልታወቀ ቦታ መውሰዱ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጥያቄ የሚጠይቁና ፖሊስ ተቃውሞውን አደራጅተዋል ብሎ የሚጠረጥራቸውን ተማሪዎች እየፈለገ እያሰረ መሆኑን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን በ17ቱም ወረዳዎች የሚገኙ ተማሪዎች ስልጠናውን ካልወሰዱ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩና ፈተና ላይ እንደማይቀመጡ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ስልጠናውን መቃወማቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ከገንዘብ ክፍፍል ቀመሩ በፊት ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን መወያየት እንደሚያስፈልግ አሳሰበ

• ተወካዩ ስብሰባውን ረግጦ ወጥቷል
(ነገረ ኢትዮጵያ)
ምርጫ ቦርድ ዛሬ ታህሳስ 22/2007 ዓ.ም ለመጭው 2007 ዓ.ም ምርጫ የገንዘብ ክፍፍል ቀመር ላይ ለመወያየት በጠራው ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ ከገንዘብ ክፍፍል ቀመሩ በፊት ምርጫው ፍትሓዊና ነጻ ለማድረግ መወያየት እንደሚቀድም ማሳሰቡን ፓርቲውን ወክሎ በስብሰባው የተገኘው አቶ ጌታነህ ባልቻ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡
ሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ ትብብሩን የመሰረቱት ፓርቲዎች ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን የበኩላቸውን ትግል እያደረጉ እንደሆነ ያስታወሰው አቶ ጌታነህ፤ ታህሳስ 12/2007 ዓ.ም የህዝብ ታዛቢዎችን ለመምረጥ በተደገው ሂደት የተመረጡት የኢህአዴግ አባላት መሆናቸው፣ ከተመረጡት መካከል የሞቱ ሰዎች ስምም መካተቱ፤ እንዲሁም በህመምና በተለያዩ ምክንያቶች ለመታዘብ የማይችሉ የሚገኙበት መሆኑ፣ የአውሮፓ ህብረትና ሌሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመታዘብ ልምድ ያላቸው ተቋማት ራሳቸውን ማግለላቸው ምርጫው ከአሁኑ ፍትሓዊ እንዳልሆነ እንደሚያሳይና ከገንዘብ ክፍፍሉ በፊት ምርጫውን ፍትሓዊ ለማድረግ መወያየት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ምርጫ ቦርድ ባቀረበው የገንዘብ ክፍፍል ቀመር መሰረት 10 በመቶ ለሴቶች፣ 10 በመቶ ለሁሉም ፓርቲዎች እኩል፣ 25 በመቶ ፓርቲዎች በሚያቀርቡት እጩ፣ 55 በፓርላማና በክልል ምክርት ቤት ባላቸው መቀመጫ እንደሚያከፋፍል የተቀመጠ ሲሆን ይህም 99.6 በመቶ ፓርላማ እንዲሁም የክልል ምክርቤትን የተቆጣጠረው፣ ከዚህም በተጨማሪ 547 ተወዳዳሪዎችን ለሚያቀርበው ኢህአዴግ የሚጠቅም ነው በሚል ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲን ወክሎ በምርጫ ቦርድ ስብሰባ የተገኘው የፓርቲው እቅድና ስትራቴጅ ኃላፊ የሆነው አቶ ጌታነህ ባልቻ ‹‹ከገንዘብ ክፍፍሉ በፊት ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን መወያየት አለብን›› በሚል ያቀረበው ሀሳብ በምርጫ ቦርድ ተወካዮች ተቀባይነት ባለማግኘቱ ስብሰባውን ረግጦ መውጣቱን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

አንድነትና መኢአድ በምርጫ ዋዜማ ከምርጫ ቦርድ ጋር የጀመሩት ውዝግብ

-- ምርጫ ቦርድ ምን ይላል? 
 ልጅ  ግሩም (ከ ሪፖርተር ጋዜጣ)  
ከእነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ጋር የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ ምርጫ ቦርድ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
‹‹እነኚህ ሁለት ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ለጊዜው በሆደ ሰፊነት እንዲያስገቡ የተደረገ ቢሆንም፣ በየፓርቲዎቹ የውስጥ ጉዳይ ምክንያት በአመራሮች መካከል መከፋፈል በመፈጠሩ የፓርቲዎቹ ሕጋዊና ትክክለኛ አመራሮች ያለመታወቅ ችግር ነበር፤›› በማለት ይገልጻል፡፡
በመኢአድ በኩል በቦርዱ ከተጠቀሱት ችግሮች መካከል በፓርቲው ውስጥ በተፈጠረ የውስጥ ዴሞክራሲ እጦት ምክንያት ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ የምርጫ አዋጁንና የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ ባላከበረ መንገድ ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዶ ለቦርዱ ሪፖርት በማድረግ ማፅደቅ ያለመቻል፣ በየጊዜው ደንብ በማሻሻል አመራር በመቀየር ተመርጠናል የሚሉ አካላት መከሰታቸው ይጠቀሳል፡፡ ይህ እንደ ትልቅ ችግር ከመቅረቡም በላይ፣ ቦርዱ ትክክለኛው የመኢአድ አመራር ማን መሆኑን ለመለየት ግራ ተጋብቻለሁ ይላል፡፡
‹‹የመኢአድ ፕሬዚዳንት ማን ነው? አቶ አበባው መሀሪ? ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል? ወይስ አቶ ማሙሸት አማረ?›› በማለት ምርጫ ቦርድ ይጠይቃል፡፡ አንድነት ፓርቲን በተመለከተ ደግሞ፣ ‹‹ቦርዱ በማያውቀውና ዕውቅና ባልሰጠው የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻሉን፣ አሻሻልኩ የሚለውን ደንብም ለሰባት ወራት ለቦርዱ ሪፖርት ሳያደርግ ሚስጥር አድርጎ አስቀምጧል፤›› የሚል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ ‹‹ይኼንኑ ደንብ በመጠቀም ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን (የፓርቲውን ፕሬዚዳንት) ከሥልጣን አሰናብተዋል፡፡ በምትካቸውም በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብም ሆነ በምርጫ አዋጁ በጠቅላላ ጉባዔ መመረጥ ያለበትን ወደጎን በመተው በብሔራዊ ምክር ቤት እንዲመረጥ አድርገዋል፤›› ይላል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ አሥራት ጣሴ:-
‹‹ምርጫ ቦርድ ያወጣው መግለጫ በጣም የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ነው ታኅሳስ 19 እና 20 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔ አካሂደን በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የፕሬዚዳንት ምርጫና የብሔራዊ ምክር ቤት ምርጫ ተከናውኗል፤›› ምርጫ ቦርድ ባወጣው መግለጫ መሠረትም እርግጥ ነው ሐምሌ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. ነው ለምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባዔ የቃለ ጉባዔ ሰነድ ያስገነባው፤›› በማለት ለሰባት ወራት ያህል መዘግየቱን አምነዋል፡፡
መኢአድ :-
የመኢአድ አመራር ማን እንደሆነ መለየት መቸገሩን ለሚገልጸው የቦርዱ ጥያቄ የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ፣ ‹‹ምርጫ ቦርድ ያውቀናል፡፡ እንደሚያውቀንም ማረጋገጫው ጠቅላላ ጉባዔአችንን በሁለት ታዛቢዎቹ አማካይነት መታዘቡንና ከዚህም በላይ የምርጫ ምልክታችሁን በአስቸኳይ እንድታስገቡ የሚል ደብዳቤ መላኩ ነው፤›› በማለት ቦርዱ ያወጣው መግለጫ እውነታን መሠረት ያላደረገና መራጩን ኅብረተሰብ ውዥንብር ውስጥ የሚከት ነው፤›› በማለት ይከራከራሉ፡፡

ለምን ወለድናቸው?። – ዳዊት ዳባ።

ze-habesha

  • 248
     
    Share
ፖሊስ የደብረ ማርቆስ ተማሪዎችን እየደበደበ ነው፡፡ የትናንትናው ተቃውሞ በኢሳትና በሌሎች ሚዲያዎች መተላለፉን ተከትሎ ‹‹ማን ነው ከኢሳትና ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር እየተደዋወለ መረጃ የሚሰጠው?›› እንዲሁም ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ካለ ተናገሩ›› በሚል ተማሪዎቹን አሳልፈው እንዲሰጡ ከፍተኛ ደብደባ እየፈጸመ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡ ፖሊስ አሁንም ተማሪዎችን እየፈለገ እያሰረ መሆኑም ተገልጾአል ይላል የዛሬ ዋና ዜና።
deberemarcos-7ለምን ለሚልና ላልሰማ። ወያኔዎች አንድ ቀን ቀደም ብሎ ‹‹የአብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና በደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎች መስጠት ጀመሩ። ክርክሩን በኢሳት ራዲዬ የሰማን በሙሉ ምስክር ልንሆን በምንችልበት  ህፃናቱ  በሀሳብ  ሞግተው ግልፅ ሆኖ በሚታይ ሁኔታ የስርአቱን ካድሬዎች አሸነፏቸው። ያነሷቸው ጥያቄዎችና መከራከሪያዎች ፍፁም እውነትነት ያላቸው፤ ብስለት የተሞላባቸውና ስክን ባለ ሁኔታ የሚቀርቡ ነበሩ። አይደለም ተራ ካድሬዎች አውራዎቹም ቢመጡም የሚቋቋሟቸው እንዳልሆነ ላዳመጠው ሁሉ ግልፅ ነበረ።  ካድሬዎቹ  ለጊዜው   እንደ መፍትሄ አድርገው በተለመደው የመከፋፈል ዘይቤ ህፃናቱ ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ በማድረግና ጥያቄ የሚያነሱትን በማስፈራራት ሊወጡት ሞከሩ። ህፃናቱ  በዚህም የሚሸነፉ አልሆኑም ማለት ነው። ይህው በሚቀጥለው ቀን ወያኔዎች ወደሀይል እርምጃ መግባታቸውን የሚያሳይ ከላይ የተቀመጠውን አሳፈሪም አሳፋሪም ዜና ሰማን።
እነዚህ ልጆች ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ታዳጊ ህጻናት ናቸው። ወዲያም አደረግነው ወዲህ ደህንነታቸው በዋናነት በቤተሰብና በማህበረሰቡ ሀላፊነት ላይ ነው ገና ያለው። ጥቃት እየፈፀመባቸው ያለው አካል ስራው ደህንነታቸውን መጠበቅ ይገባቸው ከነበሩት አንዱ  “መንግስት” ተብዬው ነው። ይህ አካል ሁላችንንም እየቀጠቀጠ እየገዛ ያለና አሁንም ቤተሰብ ለምን ቢል ጥቃት ከመሰንዘር የማይመለስ መሆኑ ቢታወቅም።  በአጠቃላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ ባላንጣ  ቢሆንም። እነዚህ ልጆች ለብቻቸው መተው ግን በጭራሽ የለባቸውም።ቤተሰብም ማህበረሰቡም ዝም ብሎ ይህንን ህፃናት ልጆቹ ላይ የሚፈፀም ወንጀል መመልከት የለበትም።  እጅጉኑ  ዝም ልንለው ከሚገባው በላይ ያለፈም ነው።
ህፃናቱን ምን አድርጉ ነው የሚላቸው። 90%የሚሆኑት ለመምረጥ ገና እድሜያቸው አልደረሰም። ምረጡኝን ምን አመጣው። በጣም ከጥቂቶች በቀር አስራ ስምንት አመት ገና ያልሞላቸው አማካኝ እድሜያቸው አስራ ስድስት አመት አካባቢ የሆኑ ታዳጊ ህፃናት ናቸው። የትኛውንስ ርእዬት አለም  ለማጥመቅም ሆነ ተከታዬ ሁኑ ለማለት ቤተሰቦቻቸውን አስፈቅዷል ወይ?። ተጠይቀንስ ፈቅደናል ወይ?። ይህም ሆኖ መታወቅ ያለበት ለአቅመ አዳም ለደረስነውም   ማስገደድ ከባድ  ወንጀል ነው።  ህፃናትን አስገድዶ ተከታዬ ሁኑ፤ አስገድዶ ምረጡኝ ማለት አስገድዶ ከመድፈር በምንድን ነው የሚለየው?። ይህ አላንስ ብሎ መደብደብ፤ ማሰር፤ ትምህርታቸውን ማስተጓጎል፤ ማሸበርንስ ምን የሚሉት?፤ ማን አለብኝነትስ ነው?። እንዴትስ ነው ይህ ዝም ተብሎ የሚታየው?። ለልጆቹስ ይወጡት ተብሎ የሚተወው።
ልጅ እያለው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲለቀቁ እየጠበቅን ቾክ እንለምን ነበር። ልጅ ስለነበርኩም ይሆናል ተማሪዎቹ ጠብደል ጠብደል ያሉ፤ በስርአቱ የለበሱና ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚሄዱ ጎልማሶች ነበሩ።  እኔ ሁለተኛ ደረጃ ስደርስ እንደጠበኩት አልነበረም። ገና ፔፕሲ፤ ሱዚና ሌባና ፖሊስ እረፍት ላይ ቅልጥ አድርገው የሚጫወቱ ነበሩ። አሁን ደግሞ ልጆቼ ናቸው። አውቃለው በእርግጠኛነት በጣም በለጋ እድሜ ያሉ ታዳጊ ህፃናት ናቸው። በዛ ላይ ገና አስረኛ ክፍል ያልደረሱ።