ፍኖት ታትማ ወጥታለች
ኢቲቪ (ወይም አዲሱ ስማችውው ኢቢሢ)፣ የኢትዮጵያ ሬድዮ፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ በመንግስት ገንዘብ የሚተዳደሩ የመገናኛ ብዙሃን ናቸው። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29 ንኡስ አንቀጽ 5 “በመንግስት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናግገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል።” እንደሚለው የተለያዩ አስትያየቶችን ፣ በአገሪቷም ያሉ በሕግ የተመዘገቡ ሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶችን ከኢሕአዴግ ባልተናነሰ ማስተናገድ እንዳለባቸው ነው ሕጉ የሚያዘው።
ዳሩ ግን ቅሉ፣ እነዚህ ሜዲያዎች እንኳን ሌሎች አስተያየቶችችን ሊያስተናገድ ቀርቶ ጭራሹኑ የአገዛዙ የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ሆነው ከኢሕአዴግ ዉጭ ያሉ ድርጅቶችን እና ማህበሮችን ፣ በተለይም የአንድነት ፓርቲን ማጥቃት ነው የተያያዙት።
ዳሩ ግን ቅሉ፣ እነዚህ ሜዲያዎች እንኳን ሌሎች አስተያየቶችችን ሊያስተናገድ ቀርቶ ጭራሹኑ የአገዛዙ የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ሆነው ከኢሕአዴግ ዉጭ ያሉ ድርጅቶችን እና ማህበሮችን ፣ በተለይም የአንድነት ፓርቲን ማጥቃት ነው የተያያዙት።
አገር ዉስጥጥ ትልቅ መዋቅር ያለዉና በአገዛዙ ከፍተኛ ዱላ እየደረሰበት፣ የሕዝብን ጥያቄ ይዞ እየተንቀስቀስ ያለው የአንድነት ፓርቲ፣ እነ አዲስ ዘመን ዝግ በመሆናቸው፣ ፍኖተ ነጻነት የሚባል ተወዳጅ ጋዜጣ በማሳተም፣ አማራጭ ሐሳቦችን ለህዝቡ ማስተማር ጀመረ።
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ በሕወሃት/ኢሕአዴግ መሪዎች ትእዛዝ፣ ማታሚያ ቤቱ የሚታተሙ ጋዜጦችን ከማተማቸው በፊት ሳንሱር እንደሚያደርግ (ይዘቱ ጥሩ ካልመስላቸው እንደማያታተም፣ ወይም እንዲስተካከል እንደሚጠየቅ ) የሚገልጽ ወረቀት ካስፈረሙ በኋላ ብቻ እንደሚያትሙ ገለጹ። ይመስለኛል ሪፖርተር፣ ሰንደቅና አዲስ አድማስ ሳንሱር ለመደረግ ተስማምተው ይሄን ወረቀት በመፈረማቸው ሳይሆንን አይቀርም ጋዜጦቻቸው የሚታተሙላቸው።
በመሆኑም ሕወሃት/ኢሕአዴግ “የቅድሚያ ምርመራ በማንኛዉም መልኩ የተከለከለ ነው” የሚለውንን የሕገ መንግስትቱን አንቀፅ 29 ፣ ንኡስ አንቀፅ 3 ፣ እዝባር ሀ/ የተቀመጠው ሕግ፣ ባፈጠጠመልኩ እንደናደው እናያለን።
በዚህ ምክንያት የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነችው የፍኖት ጋዜጣ ለሁለት አመታት ሳትታተም ቀረች። ሆኖም የአንድነት ፓርቲ አገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ያሉ ደጋፊዎቹን በማስተባበር የሕትመት ማሽን ገዛ። አንዱን በር አገዛዙ ሲዘጋ ሌላ በር አስከፍተ።
ለሕትምቱ ሥራ በቂ የመብራት ኃይል እንዲለቀቅ ፓርቲው ጠየቀ። ሆኖም ለጅቡቲ ተርፎት መብራት የሚሽጠው መብራት ኃይል ፍቃደኛ አልሆነም። ብዙ መሰናክሎችን ፓርቲው ካሰለፈ በኋላ ጀነሬተር በመከራየት ከሁለት አመታት በኋላ የመጀመሪያዉ የፍኖት ሕትመት ለሕዝብ ቀረበ። እነ አዲስ ዘመን በየሱቁና በየመስሪይያ ቤቱ በነጻ የሚወስዳቸውና የሚያነባቸው ጠፍቶ፣ የታተሙት በሺህ የሚቆጠሩ የፍኖት ጋዜጦችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕዝቡ ሲረባረብባቸው ማየት የሕዝቡ ልብ የት እንዳለ በግልጽ የሚያሳይ ነው። ብዙ ሰው ጋዜጣው የታል ቢልም፣ ወዲያው በማለቁ ጋዜጣው ሊገኝ አልቻለም። የፍኖት አዘጋጆች በሚቀጥለው ጊዜ ቁጥሩን ቢያንስ በእጥፍ ይጨምሩታል ተብሎ ይጠበቃል።
እንግዲህ እንዲህ አይነት የፖለቲካ ድርጅት ነው የሚያስፈልገው። ገዢው ፓርቲ መሰናክል ባስቀመጠ ቁጥር ተስፋ ቆርጦ የሚቀመጥ ሳይሆን፣ መሰናክሉን አልፎ የሚሄድ። ለትንሹም ለትልቁም አገዛዙን የሚከስ ሳይሆን፣ ወደ ራሱ ተመልክከቶ የአገዛዙን አፈና ተቋቁሞ ትግሉ ወደፊት የሚመራ። የገዢዎችን ዱላ የሚያጎዝፍ ሳይሆን ትልቅ መስሎ የሚታየውን አጠና ሊሰባብር በሚችለው የሕዝብ ጉልበት የሚተማመን። የአንድ ጎሳ፣ ወይም በአንድ አካባቢ ያሉትን ብቻ የሚያቅፍ ሳይሆን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ድንኳን የሚሆን።
አንድነት ጋዜጦችን፣ ፓምፍሌቶችን ፣ መጽሄቶችን ፣ በተለያዩ ቋንቋዎች ሁሉ ሳይቀር እያተመ፣ መልእክቶቹን ለሕዝብ ለማድረስ ትልቅ እቅድ ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው። የፍኖት ጋዜጣም ሕትመት የዚህ እንቅስቅሴ አንዱ አካል ነው:፡ ፍኖት ልትታተም የቻልቸው በሕዝብ፣ በአባላትና በደጋፊዎች ጥረት ነው። ፍኖት በቀጣይነት በብዛት እንድትታተም፣ አንድነት በአስተምአማኝ ሁኔታ ጀነሬተር ለመግዛት ገንዘብ ማስባሰብ ጀምሯል። አንድነት ያለ ሕዝቡ፣ ያለ አባላቱና ደጋፊዎች ድጋፍ ምንም ማድረግ ስለማይቻል፣ በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን፣ መረጃዎች ለሕዝብ እንዲደርሱ የሚደረገዉን ትግል እንድትቀላቅሉ ጥሪ ያቀርባል።መረጃ ኃይል ነውና።
ለአንድነት ወቅታዊ ጥሪ፣ ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት፣ አንድነትን በገንዘብ ለመርዳት
http://www.andinet.org/ በመሄድ በስተቀኝ በኩል ከላይ «Donate» የሚለውን ይጫኑ ።
በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ለመከታተልም የሚከተለውን የፌስ ቡክ ገጽ ላይክ ያደርጉ፡
በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በስፋት ለመከታተልም የሚከተለውን የፌስ ቡክ ገጽ ላይክ ያደርጉ፡
ፓርቲዉን በጽሁፍ፣ ጠቃሚና ፕሮፌሽናል አስተያየቶች በመስጠት ሆነ በማንኛዉም ገንዝበ ነክ ባልሆኑ ጉዳዮችም ለመርዳት ፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ ግብረ ኃይል ወይንም የአንድነት ድጋፍ ድርጅት አካል ሆናችሁ መስራት ለምትፈልጉ በሚከተለው አድራሻ ኢሜል ይላኩልን።
millionsforethiopia@gmail.com
No comments:
Post a Comment