የእንግሊዝ ኤምባሲ በኦስሎ (UK Embassy in Oslo, Norway )
በጉዳያችን
በሰልፉ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች መሃከል '' ዩኬ ዜጋሽ የት ነው? የመን አቶ አንዳርጋቸውን ልቀቂ! አቶ አንዳርጋቸው የዲሞክራሲ ተሟጋች እንጂ አሸባሪ አይደለም!'' የሚሉ ይገኙባቸዋል።ሰልፉ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተሞላበት እና የእንግሊዝ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንድትሰጥ የማድረግ ዓላማ የያዘ ነበር።
በመቀጠልም በሰልፉ አስተባባሪ ''የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ'' አማካይነት ለእንግሊዝ ኤምባሲ የተዘጋጀውን ደብዳቤ የእንግሊዝ አምባሳደር በኖርዌይ ተወካይ ወደ ሰልፈኞቹ መጥተው ከመረከባቸውም በላይ ለተሰላፊዎቹ ባደርጉት ንግግር ''ጉዳዩን የእንግሊዝ መንግስት በአንክሮ እየተከታተለ ነው እኛም ከየመን መንግስት ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን ለማከናወን ጥረት ላይ ነን'' በማለት ተናግረዋል።
በመጨረሻም ሁኔታዎች ለውጥ ካላሳዩ ቀጣይ ሰልፎች እንደሚኖሩ በተለይ በመጪው ማክሰኞ በመላው ዓለም በሚገኙ የየመን ኤምባሲ እንደሚደረግ እና የመን በኦስሎ ኤምባሲ ስለሌላት በሌሎች የአውሮፓ ከተሞች የሚደረጉ ሰልፎች ላይ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦ የሰልፉ ፍፃሜ ሆኗል።
ጉዳያችን
ሰኔ 26/2006 ዓም (ጁላይ 3/2014)
No comments:
Post a Comment