To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Monday, September 23, 2013
Police Block Blue Party Rally Near Office
Police Block Blue Party Rally Near Office
September 22, 2013
Police blocked thousands of Blue Party demonstrators from rallying to the City’s biggest square, Meskel Square. They were blocked after they walked 100 meters from their Head office in Ginfele,near 4Kilo. The leaders of Blue Party have ordered demonstrators to return back to the Party’s Head Office and to peacefully continue the demo there. The demonstrators are voicing slogans like ” We Need Freedom, Police belongs to the people, we are one, Free Eskinder Nega, Free Reeyot Alemu and others”, sitting near their Head Office.
Blue Party’s earlier demo called on September 2, 2o13 had been forcefully crushed by police. Police last week warned the Party that it could not only hold the rally in Meskel square but in Jan Meda.
Blue Party Demo
Saturday, September 21, 2013
ወጣቱ የግብርና ኤክስፐርት በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ መገደሉ ተገለጸ
ወጣቱ የግብርና ኤክስፐርት በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ መገደሉ ተገለጸ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎጃም ዞን በጐንጅ ቆለላ ወረዳ በሸበሌ ቀበሌ ዘመናዊ የግብርና አሠራር ለአካባቢው ነዋሪዎች በማሠልጠንና አብሮ በመሥራት ላይ የነበረ ወጣት የግብርና ኤክስፐርት፣ ፖሊስ በጥይት ደብድቦ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደለው ዘመዶቹና የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
በአካባቢው ለፖሊሲ ኮሙዩኒቲንግ ሥራ ከወረዳው በተላከ ፖሊስ በጥይት ተደብድቦ ሕይወቱ አልፏል የተባለው የግብርና ኤክስፐርት ዘለዓለም ፀሐይ የሚባል የ29 ዓመት ወጣት መሆኑን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በ2002 ዓ.ም. ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግብርና የትምህርት ዘርፍ ከተመረቀ በኋላ፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት ‹‹ያሳደገኝን አርሶ አደር መርዳት አለብኝ›› በማለት ከከተማ ሥራ ይልቅ ገጠሩን መርጦ ሲያገለግልና ሲያሠለጥን እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከክልሉ፣ ከዞኑና ከወረዳው ሳይቀር ልዩ ምሥጋናና አድናቆት ሲቸረው የቆየ ኤክስፐርት እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፣ ለቀበሌው ተመድቦ የነበረው ረዳት ሳጅን ታከለ በላይ የተባለ ፖሊስ፣ ከቤቱ ጠርቶ ለሕጋዊ ሥራ በተሰጠው መሣሪያ በጥይት ደብድቦ እንደገደለው ተናግረዋል፡፡ በጥይት ከመግደሉ በፊት በድንጋይ መትቶ ጥሎት እንደነበረም ጠቁመዋል፡፡
ፖሊሱ ግድያውን ሊፈጽም የተነሳበት መሠረታዊ ምክንያት ይኑረው ወይም አይኑረው ለጊዜው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ግድያውን በፈጸመበት ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ግን፣ ገዳይ ሟችን ከተኛበት ቀስቅሶ ‹‹ኳስ እንጫወት›› በማለት ወደ ሜዳ ወስዶት ሲጫወቱ ቆይተው ለማንም ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ከተጨቃጨቁ በኋላ፣ ተጠርጣሪው ገዳይ በድንጋይ ጭንቅላቱን መትቶ ከጣለው በኋላ፣ ወደ ቤቱ በመግባት መሣሪያ አምጥቶ እንደገደለውና እጁን ለፖሊስ እንደሰጠ አስረድተዋል፡፡
የገደለበትን ምክንያት ምን እንደሆነ ወደፊት በምርመራ የሚታወቅ ቢሆንም፣ መግደሉን አምኖ እጅ ሲሰጥ የክልሉ ፖሊስ ኃላፊነቱን በመውሰድ ቤተሰቦቹንና የአካባቢውን ነዋሪዎች ማፅናናትና እንዲረጋጉ ማድረግ ሲገባው፣ ይህንን ሳያደርግ በመቅረቱ ቤተሰቦቹንና ነዋሪውን እንዳስቆጣ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ለዜጎች ደኅንነት በማሰብ የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊትን ሲመለምል ከአቋም መለኪያ በተጨማሪ ያለውን ሥነ ምግባር፣ አስተዋይነትና የትምህርት ደረጃውን መሠረት አድርጎ ይሆናል የሚል ግምት እንዳላቸው የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ አሁን አሁን ግን በክልሉ ከባህር ዳር ጀምሮ፣ በአንዳንድ ዞንና ወረዳዎች በታጣቂ ፖሊሶች እየደረሰ ያለው የግድያ ወንጀል ሥጋት ውስጥ እንደከተታቸው አስረድተዋል፡፡ የፌዴራልም ሆነ የክልሉ መንግሥት በፖሊስ አመላመልና ሠልጥነው በሥራ ላይ ያሉትን ፖሊሶች ሥነ ምግባር፣ ከተሰጣቸው ተልዕኮና ሕዝብን ከማገልገል አንፃር እየተገበሩት ስለመሆኑ መፈተሽ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የአገሪቱ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነውን ግብርናን በተሻለና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ለማስቀጠል ከተማ ትቶ ከአርሶ አደሩ ጋር ደፋ ቀና ሲል በአሰቃቂ ሁኔታ በፖሊስ ስለተገደለው ወጣት የግብርና ባለሙያ፣ ትኩረት ሰጥቶ ለቤተሰቦቹና ለነዋሪናዎች ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡
ወጣቱ የግብርና ኤክስፐርት በፖሊስ ስለመገደሉና ስለተወሰደው ዕርምጃ ማብራሪያ እንዲሰጥ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንን ተጠይቆ አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የፖሊስ ሹም ድርጊቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል፡፡ ግድያው የተፈጸመው ታስቦበትና ሆን ተብሎ ሳይሆን፣ በጨዋታ ላይ እያሉ ሲበሻሸቁ በድንገት ገዳይ ተበሳጭቶ በደም ፍላት ያደረገው ሳይሆን እንደማይቀር የፖሊስ ሹሙ ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ውሎ ፍርድ ቤት መቅረቡንና በጊዜ ቀጠሮ ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ነሐሴ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. የተገደለው ወጣት ዘለዓለም ፀሐይ፣ ከሁለት ዓመት በፊት ቀለበት ካደረገላት ዕጮኛው ጋር በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም. ጋብቻ ለመፈጸም ፕሮግራም እንደነበረው ቤተሰቦቹ ገልጸዋል፡፡ ሟቹ በተወለደበትና ወላጆቹ በሚኖሩበት በምዕራብ ጐጃም ዞን በአዴት ወረዳ በዴንሳ ቀበሌ ውስጥ በበዓታ ቤተ ክርስቲያን ጳጉሜን 1 ቀን 2005 ዓ.ም. የቀብር ሥርዓቱ መፈጸሙን ቤተሰቦቹ አስረድተዋል፡፡
lets fight together for freedom
I am proude you dears ... we are together for common goal
to make free our land from domestic colonization of weyane ,whatever the strangle is biter and rough we will go through it ......!!!!!
God bless Ethiopia ,
ቀጣዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማን ሊሆን ይችላል?
ቀጣዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማን ሊሆን ይችላል?
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔር በመሆን በሁለት ዙር ለ12 ዓመታት ያገለገሉት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ የስልጣን ዘመናቸው ሊያበቃ የቀራቸው ጥቂት ቀናት ብቻ ነው። ይሄም ሆኖ ግን ቀጣዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ማን ሊሆን እንደሚችል አሁንም ድረስ ፍንጭ አልተገኘም። የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ በፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የስልጣን ዘመን የስራ ክንውኖች ዙሪያ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ባለስልጣናትንና ምሁራንን አስተያየቶች አሰባስባለች፡፡ የ90 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ ፕሬዚዳንት ግርማ ምን ተሳካላቸው፣ ምንስ ከሸፈባቸው? እሳቸውን የሚተካው አዲሱ ፕሬዚዳንትስ ማን ይሆን? አስተያየቶቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
=============
“የመምረጥ እድል ቢሰጠኝ ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞንን እመርጣለሁ” ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም ፕሬዚዳንት ግርማ እስካሁን በስልጣን ላይ ሲቆዩ ይህን ሰሩ፣ ይህን አደረጉ የምለው አንድም ወደ አዕምሮዬ የሚመጣ ነገር የለም። አንድም ጊዜ አቋም ወስደው በአገር ፖሊሲ ላይ ጫና ሲፈጥሩ አይቼም ሰምቼም አላውቅም። እንደውም እውነቱን ለመናገር ከነመኖራቸውም ትዝ አይሉኝም፡፡ አንድ ጊዜ እንደውም “አሰብ የኤርትራ አንጡራ ሀብትና ግዛት ናት” ሲሉ በጆሮዬ ሰምቼ እጅግ አዝኜባቸዋለሁ፡፡ ይህን በቴሌቪዥን ነው የተናገሩት፡፡ ቦታው ለምልክትነት ካልሆነ ብዙ የሚሰራበት አይደለም በሚለውም አልስማማም፡፡ ፕሬዚዳንቱ
ሊያከናውኗቸው የሚችሏቸው የተለያዩ ተግባራት አሉ፡፡ በግልፅ የተቀመጡትን እንግዳ መቀበል፣ ፓርላማ መክፈት እና የመሳሰሉትን ትተን፣ በርካታ ስራዎችን መከወን ይችሉ ነበር፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ የበጐ አድራጐት ስራዎችን መምራት፣ የተለያዩ ማህበራትን ማጠናከር፣ ህዝቡን ለስራ ማደፋፈር፣እስረኞችንና ህሙማንንን መጐብኘትና ያሉበትን ሁኔታ መከታተልና የመሳሰሉትን ሊሰሩ ይችሉ ነበር፡፡
ከዚህም ባለፈ የውጭ ግንኙነት ላይ የዲፕሎማሲ ስራዎች ሞልተዋል፡፡ ነገር ግን እኔ አንዱም ላይ ሲንቀሳቀሱ አላየሁም፡፡ ስለዚህ በዚህች አገር ፕሬዚዳንትነት ላይ ብዙም የሚታወሱ አይደሉም ማለት እችላለሁ፡፡ የተለያዩ የአለምና የአፍሪካ ፕሬዚዳንቶች በርካታ ስራዎችን ይሰራሉ፣ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግን እንቅስቃሴያቸው በጣም ደካማ ነው፡፡ በቀጣይ ማን ፕሬዚዳንት ይሁን በሚለው ላይ የመምረጥ እድል ቢሰጠኝ አንድ ዕጩ አለኝ በውስጤ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ይህ በተለይ ለኢትዮጵያ ሴቶች ትልቅ አቅም ይፈጥራል። አሁን ባሉበትም ብዙ እየሰሩ ነው፣ ወደፊትም ብዙ ለመስራት አቅም እንዳላቸው ይሰማኛል፡፡ በመሆኑም እጩ ምረጥ ብባል ለወ/ሮ ሙሉ ሰላምን ቅድሚያ እሰጣለሁ፡፡ “ፕሬዚዳንቱ ለሁለተኛ ጊዜ መመረጣቸው ፈፅሞ ስህተት ነበር” አቶ ሙሼ ሰሙ (የኢዴፓ ሊቀመንበር) እኔ እስካሁን በኖሩበት የፕሬዚዳንት ዘመናቸው አንድም የማስታውሰው ስኬት የላቸውም፡፡
ይህን የምልበት ምክንያት አንደኛ፣ ጤነኛ ሆነው አመቱን ሙሉ የሰሩበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ ሁለተኛ፣ የሰውነት አቋማቸው በንቃት እንዲንቀሳቀሱ የሚያደርጋቸው አልነበረም፡፡ በሶስተኛ ደረጃ፣ ባሉበትም ሁኔታ ይህን ሰሩ ብዬ በግልፅ የምጠቅሰው ነገር የለኝም፡፡ በዚህች አገር ጉዳይ ላይ፣ ይህችን አገር ወደፊት ያራመደ ጠንካራም ሆነ ደካማ የማስታውሰውም የማውቀውም ነገር የለም። እኔ ፕሬዚዳንት ግርማን የማውቃቸው በአገር ምልክትነታቸውና መገለጫነታቸው ብቻ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ህገ-መንግስቱ ሰፍሮ ከሰጣቸው ስልጣን ባለፈ በፕሬዚዳንትነታቸው ሊሰሯቸው የሚችሏቸው ሥራዎች ሞልተዋል፡፡ ለምሳሌ የፕሬዚዳንቱ ቦታ የዲፕሎማቲክ ስራዎችን እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ብዙ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችም አሉ፡፡ ምናልባት አንድ ወቅት ላይ በእርሳቸው ተጀምሮ የከሸፈ ወይም የት እንደደረሰ የማላውቀው የአገሪቷ የደንና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ነበር።
አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ሊሰራባቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ከጤና፣ ከአረጋዊያን፣ ከህፃናትና ከሴቶች፣ ከህፃናት ጥቃትና መሰል ጉዳዮች ጋር የተገናኙ ሥራዎች ሞልተዋል፡፡ በፖለቲካውም ማህበራትን በማቋቋምና በማጠናከር፣ እንዲሁም በት/ቤቶች ዙሪያ ሊሰሩ የሚችሉ እጅግ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ይህቺ አገር የሚያስፈልጓት ስራዎች ማለቴ ነው፡፡ እናም እርሳቸው የሀገሪቱ ምልክት እንደመሆናቸው ከተለያዩ አገራት መንግስታት ጋር እየተገናኙ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ፋውንዴሽኖችን ማቋቋምና ማጠናከር ይችሉ ነበር፡፡ የሌሎች አገሮች ፕሬዚዳንቶች ይህንን ያደርጋሉ። በሴቶችና በህፃናት ጥቃት ጉዳይ፣ በህፃናት የትምህርት ጉዳይ፣ በጤናና በበርካታ ሚሊዮን ጉዳዮች ዙሪያ ሊንቀሳቀሱና ሊሰሩ ይችሉ ነበር፡፡ ይህቺ አገር ያለባት ማህበራዊ ችግር ሠፊና ጥልቅ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
ይህ ከማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በፖለቲካው ረገድ ብትወስጂው እዚህ አገር እጅግ በርካታ ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ በፖለቲካ፣ በወንጀል እና በተያያዥ ጉዳዮች ወህኒ ቤት የሚገኙ እስረኞች አሉ፡፡ የእነዚህ እስረኞች ጉዳይ መፍትሄ አግኝቶ በቀላሉ የሚፈቱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሠፊው መስራት ነበረባቸው፡፡ አንዳንዱ ሰው እኮ እስር ቤት የቆየበትን ምክንያት እንኳን አያውቀውም፡፡ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ከኦነግ ጋር፣ ከኦብነግ ጋርና ከተለያዩ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ እስር ቤት ገብተው እስካሁን ያልተፈቱ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ጉዳይ አንድ ማህበራዊ ተቋም ተመስርቶ፣ ተጣርቶና መፍትሄ አግኝቶ መስተካከል ነበረበት፡፡ ይህን መስራት ያልቻሉት በጤናና በአቅም ሁኔታ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በፊት በነበረው መንግስት በርካታ ተጠቃሽ ስራዎችን ሰርተዋል፡፡ ቀላል የማይባሉ ተቋማትን በማጠናከር ረገድም ብዙ ስራዎችን አከናውነዋል፡፡ ሰውየው የብቃት ችግር አለባቸው ብዬ አላምንም፡፡ አሁን ግን የእድሜ፣ የጤናና የሰውነት አቋም ችግሮች ተደማምረው በፕሬዚዳንትነታቸው መስራት የሚገባቸውን እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል፡፡ ይህ መቼም ግልፅና ብዙም የማያወዛግብ ጉዳይ ነው፡፡
በተለይ ሁለተኛው ተርማቸው ፈፅሞ መደረግ ያልነበረበት ነው። አሁን ኢትዮጵያ ወደፊት ለመራመድ ከምትፈልገው አቅጣጫ አኳያ ጠቃሚ ያልሆነ ውሳኔ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ልማት፣ እድገትና ብልፅግና ማምጣት የምትፈልግ አገር ነች፡፡ የዚያ መገለጫ የሚሆን ፕሬዚዳንት ነው የሚያስፈልጋት፡፡ ለእኔ ያንን መገለጫ የሚያሳዩ ፕሬዚዳንት አልነበሩም፡፡ እንዳልኩሽ ኢትዮጵያ ራዕይ አላት፡፡ ራዕይ ስልሽ የኢህአዴግ ራዕይ አይደለም፣ የዜጐች ራዕይ ማለቴ ነው፡፡ ያ ራዕይ ደግሞ ዜጐች ከድህነት ወጥተው፣ የተረጋጋ የኢኮኖሚና በተረጋጋ አገር ውስጥ የመኖር ራዕይ አላቸው፡፡ ይህንን ለማምጣት ደግሞ አቅምና ብቃት ያለው ገለልተኛ ፕሬዚዳንት ያስፈልጋል፡፡ ገለልተኛ ሲሆን የፖለቲካ ተቃርኖዎችን በማስታረቅና መፍትሄ በመስጠት እንዲሁም አቅጣጫ በማሳየት፣ እነዚህን ሁሉ ስራዎች ወደ ውጤት መቀየር የሚችል መሪ ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን የዜጐች ራዕይ ማን ያሳካል ለሚለው፣ እከሌ ማለት ምኞት ብቻ ነው የሚሆነው። አንደኛ፣ ኢህአዴግ ይህን እድል ለማንም አይሰጥም። ሁለተኛ የራሱን ሰው መርጧል፡፡ ሲመርጥ ደግሞ በራሱ መስፈርት ነው፡፡ ከብሄር፣ ከሀይማኖትና ከመሰል ጉዳዮች አኳያ እንደሚመርጥ ነው የሚገመተው፡፡ ከዚህ በፊት በውስጤ ያሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ አሁን ግን ከኢህአዴግ አኳያ አቅጣጫውን ሳየው፣ እከሌ ወይም እንትና ማለት ጥቅም የለውም፡፡
ስለዚህ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም ኢህአዴግ እንዲህ አይነት እድል የሚሰጥ ባህሪ የለውም፡፡ የሰዎችን ባህሪና ስነ-ልቦና አዳምጦ፣ ጠቃሚ የሆነን ሰው ወደዚያ ቦታ ለማምጣት ተነሳሽነት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ስለዚህ አሁን አስተያየት መስጠት ዝም ብሎ ምኞት ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ እኔ ደግሞ የምኞት ሰው ሳልሆን የተግባር ሰው ነኝ፡፡ “እንኳን አቶ ግርማ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳስ ምን ሰራና ነው” ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ለመሆኑ አቶ ግርማ ምን ሰርቶ ነው ስኬት ነበረው ውድቀት ነበረው የምትይው? አሁን ይሄን ጥያቄ ብለሽ ነው የምትጠይቂው ወይስ ጠፍቶሽ ነው? በመጀመሪያ ደረጃ ምን ሀላፊነት ተሰጠውና ነው ስኬት ውድቀት የምትለኪበት? የፕሬዚዳንቱ ስራ ዝም ብሎ ቁጭ ማለት ነው፡፡ ወደ 12 ዓመት ገደማ ቁጭ ብሏል ይወጣል፣ በቃ አለቀ፡፡ የምን ስኬት ነው? ምንስ ስራ ተብሎ ነው ስኬቱ የሚለካው? በመሰረቱ ህጉ ራሱ ምንም ሀላፊነት እና ሥራ አይሰጠውም፡፡ በህጉ ላይ የተወሰኑ ነገሮች አሉ፡፡ ሰዎችን መቀበል፣ እንግዶችን ማስተናገድ፣ አምባሳደሮችን መቀበልና መሸኘት፣ ይቅርታ መስጠት፣ “ይሙት በቃ” የተፈረደባቸውን ሰዎች ፈርሞ ማፅደቅ የመሳሰሉትን ያከናውናል፡፡ ይህንንም ቢሆን የሚፈፅመው ግን ከላይ ያሉት ሲፈቅዱለት ነው፡፡ ይህን ጉዳይ እናንተ ጋዜጠኞቹም ታውቁታላችሁ፣ ዝም ብላችሁ ነው የምታደርቁን፡፡
እኔ የምለው--- ከእርሱ በፊት የነበረው ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳስ ምን ሰራ? እንኳን አቶ ግርማ? ዝም ብሎ ተቀምጦ ኖሮ ጊዜው ሲደርስ ወጣ፣ በቃ ይሄው ነው፡፡ አንድ ሰው ስኬቱና ውድቀቱ የሚለካው ይህን ይህን ይሰራል ተብሎ በጉልህ የተቀመጠ እና ሊያሰራ የሚችል ሁኔታ ላይ ሲሆን ነው፡፡ ይሄ በሌለበት ስኬት ውድቀት የሚባለው ነገር አይገባኝም፡፡ አዲሱ ፕሬዚዳንት ማን ይሁን? ምን ይስራ? ለሚባለው የማውቀው ነገር የለኝም፡፡ እኔን ተይኝማ ጐሽ! “ፕሬዚዳንት የሚሆኑ ሰዎች ጤናማና ቀልጣፋ ቢሆኑ እመርጣለሁ” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር) ፕሬዚዳንቱ ስኬታቸው ውድቀታቸው ምንድነው የሚለው ጥያቄ ከባድና የሚገርም ጥያቄ ነው፡፡ እኔ እንደውም ባልናገር ይሻለኛል፡፡ እንዴ! እርሳቸው ቤተ-መንግስት ገብተው ሲጦሩና ሲታከሙ ኖሩ እንጂ ምን የሰሩት ስራ አለና ነው እንደ ጥያቄ የሚነሳውስ፡፡ እናንተም ቢሆን እንዴት አንድ ነገር ሳንፅፍ ይሰናበታሉ በሚል ለወጉ ነው እንጂ ያነሳችሁት ምንም አለመስራታቸውን ሳታውቁት ቀርታችሁ አይደለም፡፡ በግላቸው በተፈጥሮ ሳይንሱና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ፍላጐት እንዳላቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ እሰማለሁ፡፡ ነገር ግን ያ ጉዳይ ወደ ተግባር ተለውጦ ማየት ነበረብን፡፡
እኔ በበኩሌ ይሄ ነው የሚባል ነገር አላየሁም፡፡ እርሳቸው ርዕሰ መንግስት ሳይሆኑ ርዕሰ ብሄር ናቸው፣ ስለዚህ እሳቸው ሊሰሩ ይገባ የነበረው ይቅርታን የመስበክ፣ ሁሉንም ፓርቲዎች እኩል የማየት፣ በሀይማኖት ጉዳይ ችግር ሲከሰት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ማድረግ ነበር፡፡ ነገር ግን እርሳቸው ጤናቸውም፣ እድሜያቸውም ምክንያት ሆኖ የስራ እንቅስቃሴያቸው ትክክለኛ ፕሬዚዳንት ሊያደርገው የሚችለው አይነት አልነበረም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ፣ እርሳቸው ኢህአዴግን ከማመን ውጭ በራሳቸው ተንቀሳቅሰው ይህን አደረጉ የሚባልላቸው ነገር የለም፡፡ በሶስተኛ ደረጃ፣ ቦታውም ሆን ተብሎ በህገ-መንግስቱ ሲፀድቅ ባዶ ከመሆን የማይሻል ተደርጐ ስለሆነ እኔ እንደ አንድ የፖለቲካ ቁምነገር ለማየት እቸገራለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ህገ-መንግስቱ ላይ ባይቀመጥም ፕሬዚዳንቱ ብዙ ሊሰሯቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ እርሳቸው ግን ምንም አላደረጉም፡፡ ለምሳሌ በሀይማኖቶች አካባቢ ያለውን እንመልከት፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለሁለት ተከፍሎ ችግር ላይ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት እነዛም ከውጭ ይምጡና ይወዳደሩ የሚል ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ፣ ፖለቲከኞቹ ሲቆጧቸው ሀሳቡን አንስቻለሁ አሉ። በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ይህ ሁሉ ችግር ሲፈጠር፣ እንደ ርዕሰ-ብሄርነታቸው መንግስት ከዚህ ጨዋታ እንዲወጣና ችግሮቹ መልክ እንዲይዙ ማድረግ ይችሉ ነበር፡፡ በምርጫው ጊዜ በፓርቲዎች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ወደ እርቅ፣ ወደ መቻቻልና ወደ ሰላም እንዲመጡ የራሳቸውን አስተያየትና ሀሳብ መስጠት ይችላሉ፡፡
እንደርዕሰ ብሄርነታቸው ጐላ ባለ መልኩ ሊሰሯቸው የሚችሏቸው በርካታ ነገሮች ነበሩ፣ ነገር ግን እንደነገርኩሽ ዕድሜያቸውም ሆነ ጤናቸው እንዲሁም አጠቃላይ ሁኔታቸው ያንን እንዲከውኑ አላደረጋቸውም። በዘመኑ ቋንቋ “ከደረጃ በታች ተጫውተዋል” ነው የእኔ አስተያየት፡፡ በትምህርት ዝግጅት፣ በዲፕሎማሲ በአጠቃላይ ሁኔታዎች እከሌ ቢመረጥ የምትለው አለ ወይ ለተባልኩት እኔ በእውነቱ ምንም እከሌ የምለው ሰው የለኝም፡፡ አንደኛ የሚመረጠው ሰው በኢህአዴግ ኮረጆ ውስጥ ገብቶ ነው የሚሰራው፡፡ ሁለተኛ ቦታውም እዚህ ግባ የሚባል ስልጣን በህገ-መንግስቱ አልተሰጠውም፡፡ የሚወዳደሩትም ሰዎች በብዛት እዚያ ሲስተም ውስጥ የሚገቡት በዚህ ታሪክ ውስጥ ስማችን ተመዝግቦ እናልፋለን ብለው እንጂ ቦታውን አሁን ባለው ሁኔታ ቁም ነገር እንሰራበታለን ብለው አይደለም፡፡ ስለዚህ ለእኔ ማንም ተመረጠ ማን ለውጥ አያመጣም፡፡ ነገር ግን ጨቋኞች ቢሆኑም የአገር ምልክት ናቸውና ጤነኛ፣ የተማረ፣ ተነጋግሮ በቋንቋ የሚግባባ ሰው፣ በተቀላጠፈ ሁኔታ የሚንቀሳቀስና ያሉትንም ውስን ስራዎች የሚያከናውን ቢሆንና አገር ባይዋረድ እመርጣለሁ፡፡
ከዚህ ባለፈ በስራ ደረጃ ፕሬዚዳንቱ ይህን ሰርቶ፣ ይህን አድርጐ ለውጥ ያመጣል በሚል የምጠብቀው ምንም ነገር የለም፡፡ “ፕሬዚዳንት በህገ-መንግስቱ የተቀመጠላቸውን ሀላፊነት በአግባቡ ተወጥተዋል” ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ፕሬዚዳንቱ ይህን ሰሩ ወይም አልሰሩም ለማለትም በህገ-መንግስቱ የተቀመጠላቸውን አቅጣጫ ማየት ግድ ይላል፡፡ በህገ-መንግስቱ የተቀመጠና የተሰጣቸው የስራ ሀላፊነት አለ፣ ያንን ከመወጣት አኳያ በተገቢው መንገድ ተወጥተዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከዚህ ውጭ በግላቸውም በተለይ አካባቢንና ተፈጥሮን ከመንከባከብ አኳያ የጀመሩት ስራ በጥሩ ሁኔታ ተከናውኗል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የእኛ አገር አካሄድ በአብዛኛው ፓርላሜንታሪ ነው፡፡ በፓላሜንታሪ አገር ደግሞ ብዙውን ስራና ሀላፊነት የሚጥለው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ስለሆነ ባልተሰጣቸው ሀላፊነት ስራ አልሰሩም ተብሎ የሚወቀሱበት ሁኔታ ያለ አይመስለኝም። ህገ መንግስቱ የፈቀደላቸውን ግን በአግባቡ ተወጥተዋል ባይ ነኝ፡፡ ይቅርታ በማድረግ፣ አምባሳደሮችን በመሾም እና በመሰል ጉዳዮች ላይ ሰርተዋል ወይ ከተባለ፣ አዎ ሰርተዋል። ሹመቶቹንም ቢሆን ቀጥታ መሾም ሳይሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ነው የሚሾሙት፣ ስለዚህ ስራቸውን ተወጥተዋል፡፡ ስለወደፊቱ ፕሬዚዳንት አመራረጥ መነሻው ህገ-መንግስቱ ነው፡፡
በህገ መንግስቱ መሰረት ለገዢው ፓርቲ የተሰጠ ስልጣን አለ፡፡ ገዢው ፓርቲ ነው ፕሬዚዳንቱን የሚያቀርበው፣ ስለዚህ ስለ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ከዚህ በላይ ማለት አልችልም፡፡ “ፕሬዚዳንት ግርማ ስኬታማም እድለኛም መሪ ናቸው” “የቀጣዩን ፕሬዚዳንት ማንነት መተንበይ አልችልም” አቶ አሰፋ ከሲቶ የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የፕሬዚዳንት ግርማ ዋናው ስኬት ለሁለት ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመረጣቸው መሆኑ ነው፡፡ ከዴሞክራሲ ሂደቱ አንፃር ይሄ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ በራሳቸው ለህዝብ አርአያ የሚሆን በርካታ ስራዎችን ላለፉት 12 ዓመታት ሲያከናውኑ ነው የቆዩት፡፡ የህዝብ አገልጋይነትን ስሜት ይዘው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ህዝብ ማገልገል መቻላቸው በጣም አስደሳች ነው፡፡ ለምሳሌ የተቸገረ ሰው ወደ እርሳው አቤቱታ ባቀረበ ጊዜ ችግሩ እንዲፈታ ያደርጋሉ፡፡ የቅርብ አማካሪ እንደመሆኔ የእርሳቸውን ውሳኔና ድጋፍ ሊያገኝ የመጣ ሰው የእርሳቸውን ድጋፍና ምክር አግኝቶ የሚሄድበት ሁኔታ እንደነበር አውቃለሁ በአጠቃላይ ዜጐችን የማገልገል እምነታቸውና ፍላጐታቸው ጠንካራ መሆኑን ለማስተዋል ችያለሁ፡፡ በሌላ በኩል እውቀታቸው ከምንምና ከማንም ጋር ተወዳዳሪነት የሌለው ነው።
ለምሳሌ የቋንቋ ችሎታቸው በጣም ሰፊ በመሆኑ ከማንኛውም አገር መሪና ኤምባሲዎች ጋር በመገናኘት በፈለጉት ቋንቋ ሀሳባቸውን የመግለፅ ብቃታቸው ወደር የለውም፡፡ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳኛ፣ ጣሊያንኛና ሌሎችንም ቋንቋዎች አቀላጥፈው መናገር የሚችሉ በመሆናቸው ስለ አገሪቱ ጠቅላላ ሁኔታ በእድገት ጉዞና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአገርን ገፅታ ግንባታ በመስበክ ስኬታማ መሪ ናቸው፡፡ በጣም አንባቢ ናቸው፡፡ የማስታወስ ችሎታቸው ፍፁም የሚደነቅና ወደር የለሽ ነው፡፡ በዚህ ለሌሎች አርአያ መሆን የሚችሉ ናቸው፡፡ ሌላው ማረሚያ ቤት ገብተው የታረሙ ሰዎች ይቅርታ አግኝተው እንዲወጡ ከፍተኛ ክትትል ያደርጋሉ። አንድ ሰው ወንጀል ፈፅሞ በፍ/ቤት ፍርድ ተሰጥቶ ማረሚያ ቤት የገባ ሰው መታረሙ ከተረጋገጠ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ አይፈልጉም፡፡ ታራሚው ከማረሚያ ከወጣ በኋላ ችግር የማይፈጥር መሆኑን እንደ ይቅርታ መስፈርት ይወስዱታል፡፡ እንደውም በአንድ ወቅት የነገሩኝን ባነሳ ደስ ይለኛል፡፡ በ1950ዎቹ ኢሉባቡር ጐሬ ውስጥ ለስራ በሄዱ ጊዜ 15 ሰዎች መንገድ ላይ ቆመው ያገኛሉ። ከመኪና ወርደው “ምንድናችሁ?” ብለው ሲጠይቁ፣ እስረኞች እንደሆኑ መለሱላቸው ከመሀላቸው አንዱ ጠብመንጃ ይዟል፡፡
“አንተስ ጠብመንጃ የያዝከው ምንድነህ?” ብለው ይጠይቁታል፡፡ “ወደ መቱ አጅቦን የሚሄደው ፖሊስ ሊፀዳዳ ወደ ጫካ ገብቶ ጠብመንጃውን ያዝ ብሎኝ ነው” አላቸው፡፡ እርሳቸውም በጣም ተገርመው በወቅቱ መቱ ጠቅላይ ግዛት ሀላፊ ለነበሩት ሰው ደብዳቤ ፅፈው እንዲፈቱ አድርገው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አጫውተውኛል፡፡ እናም የታረሙ ሰዎች እስር ቤት እንዲቆዩ አይፈልጉም፡፡ እድለኛ ናቸው የምለው ደግሞ በእርሳቸው ዘመን ታላቁ የህዳሴ ግድብ በመጀመሩ ነው፡፡ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድም ውጤታማ በሆነ መንገድ ተፈፃሚ እየሆነ ያለበት ወቅት በመሆኑም ስኬታማም እድለኛም ናቸው እላለሁ፡፡ እስካሁን እንደ ርዕሰ ብሄርነታቸው በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 11 መሰረት የተሰጣቸውን ስልጣንና ተግባር ሙሉ ለሙሉ በአግባቡ እንደተወጡ አምናለሁ፡፡ በአስፈፃሚ አካል ስልጣንና ሃላፊነት ጣልቃ አይገቡም፡፡ ጠንካራና ታታሪ ሰራተኛ ናቸው፡፡ ለምሳ የማይወጡበትቅ ጊዜ ይበዛል፡፡ ሀላፊነታቸውንና ተግባራቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል፡፡ እርሳቸውን ተክቶ የሚሰራውን ሰው መገመት አልችልም፡፡ በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረት ቀጣዩ ፕሬዚዳንትም በህዝብ በተወካዮች ም/ቤት እና በፌዴሬሽን ም/ቤት ስብሰባ ተደርጐ በውይይት ተመርጦ ነው የሚቀርበው፡፡ በመሆኑም የቀጣዩን ፕሬዚዳንት ማንነት መተንበይ አልችልም፡፡ የማውቀውም ነገር
እኛን ለማዳከም የታሰበ ስራ ቢሆንም ትግላችንን እንቀጥላለን” ሰማያዊ ፓርቲ
እኛን ለማዳከም የታሰበ ስራ ቢሆንም ትግላችንን እንቀጥላለን” ሰማያዊ ፓርቲ
Minilik Salsawi
"መስቀል አደባባይ ለተቃዋሚዎች አይፈቀድም::" ኢህአዴግ
“እኛን ለማዳከም የታሰበ ስራ ቢሆንም ትግላችንን እንቀጥላለን” ሰማያዊ ፓርቲ
ሰማያዊ ፓርቲ ነገ እሁድ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እንቅፋት እንዳጋጠመው የተናገሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ ቦታው ለተቃዋሚዎች አይፈቀድም እንደተባሉ ገለፁ፡፡ በአዲስ አበባ መስተዳድር፣ የስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ሃላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ በበኩላቸው፤ ስፍራው ለልማት የታጠረ በመሆኑ የትኛውም አካል በስፍራው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሂድ አይፈቀድለትም ብለዋል፡፡
ሰላማዊ ሰልፉን በጃንሜዳ እንዲያካሂዱ ሃሳብ አቅርበንላቸዋል ይሉት አቶ ማርቆስ፤ “በዚህ ካልተስማሙ አማራጭ ቦታ እንዲያቀርቡ በደብዳቤ አሳውቀናቸዋል” ብለዋል፡፡ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደምናካሂድ ለመስተዳድሩ በደብዳቤ ያሳወቅነው ከ10 ቀን በፊት ነው የሚሉት ኢ/ር ይልቃል በበኩላቸው፤ መስተዳድሩ ቅሬታውን በ12 ሰዓት ውስጥ ካልገለፀ እንደተስማማ ስለሚቆጠር ፅሁፎችን አትመን ስናሰራጭ፣ በሚዲያ በይፋ ስናስተዋውቅ ቆይተናል፤ ስለዚህ በዚያው እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
...
ጃንሜዳ በክረምቱ ዝናብ በሙጃና በጭቃ ስለተሸፈነ ለሰላማዊ ሰልፍ አያመችም ይላሉ፡፡ ቦታው ለተቃዋሚዎች አይፈቀድም ተብለናል የሚሉት ኢ/ር ይልቃል፤ ለልማት ታጥሯል መባሉም ተቀባይነት እንደሌለው ሲናገሩ፤ ቦታው ከጥቂት ቀናት በኋላ የደመራ በዓል ይካሄድበታል፤ ክልከላው “እኛን ለማዳከም የታሰበ ስራ ቢሆንም ትግላችንን እንቀጥላለን” ብለዋል፡፡
የመስቀል በዓልን አከባበር በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ማርቆስ፣ “የመስቀል በዓል ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓል በመሆኑ፣ እኛ መፍቀድም መከልከልም አንችልም” ብለዋል፡፡ ኢህአዴግስ ሠልፍ በስፍራው ማካሄድ ይችላል ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ጉዳዩ የገዢ ፓርቲ ወይም የተቃዋሚ ፓርቲ የሚል አይደለም፤ ስፍራው በከፍተኛ በጀት በውጭ ኮንትራክተሮች እየለማ ስለሆነ፣ የትኛውም አካል ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ አይችልም” ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲም ጃንሜዳ አይመቸኝም የሚል ከሆነ አማራጭ ቦታ ያቅርብና አስተዳደሩ ተወያይቶ ይወሰናል በሚል ሃሳባችንን በደብዳቤ ገልፀናል ብለዋል - አቶ ማርቆስ፡፡
Subscribe to:
Comments (Atom)




