Wednesday, June 4, 2014

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተላለፈ ጋዜጣዊ መግለጫ “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት”


ለአለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት የሕዝብን መብት በመቀማትና አፍኖ በሥልጣን ላይ የሚገኘው የህወሃት/የኢህአዴግ መንግሥት ዜጐች በአገራቸው ውስጥ በመዘዋወር ሰርተው እንዳይኖሩ ያገደ ብቻ ሳይሆን በተወለዱበትና እየኖሩበት በአለው ቀያቸውም የገዠው ፓርቲ አባል ካልሆኑ ወይም ደግፈው ካልቆሙ ይሰደዳሉ፣ ይበታሰራሉ፣ ይደበደባሉ፤ በተለያዩ ምክንያቶችም ንብረታቸውን ይቀማሉ፡፡ የተቀዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባል ከሆነ ደግሞ ጫናው ምን ያህል እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ በዚሁ መመሪያቸው መሠረትም በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡ ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከልም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህልም፡-
1. በደቡብ ክልል በሰሜንአሪ ወረዳ በጉዛ ዚፍቲ ቀበሌያት የሚኖር ሕዝብ ሕገ-መንግሥታዊ መብቻውን ተጠቅመው በመኢአድ ጥላ ሥር ስለተደራጀና ጽ/ቤት ስለከፈቱ ብቻ ሦስት (3) አመራሮቻቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ፍትህም ተከልክለው ሰሚ አካል ሊያገኙም አልቻሉም፡፡
2. በጐፋ ልዩ ዞን የሚገኙ የመኢአድ አመራሮችና አባላት ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ስለተደራጁ ብቻ ከፍተኛ ድብደባና እስር ደርሶባቸዋል፤ የፓርቲው መታወቂያቸውንም እንዲነጠቁ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜም አስራ ሁለት (12) የመኢአድ አባላት በሳውላ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
3. በደቡብ ክልል በደራሼ ልዩ ወረዳ የመኢአድ የወጣቶች የአመራር አባል በጩቤ ተወግተው ለፍትህ አካላት አቤት ቢሉም መልስ አጥተው በችግር ላይ ይገኛሉ፡፡
4. በአማራ ክልላዊ መንግስት በአንካሻ ወረዳ የሚገኙ የመኢአድ አመራር በኢህአዴግ ካድሬዎች ተደብድበው በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከትናንት በስቲያ ማለትም ሚያዚያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በጐንደር ከተማ በመንግሥት ታጣቂዎችና በሕዝቡ መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የብዙ ዜጎች ሕይወት እንዲጠፋ ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ዜጎችም ከቤታቸው እየታፈኑ ወደ አልታወቀ ቦታ እንዲወሰዱ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
5. በተለያዩ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በመማር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር በአደረጉት ግጭት ምክንያት ብዙ ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተው፤ ብዙ ንብረትም ወድሟል፡፡
ይህ የሚያሳየን የህወሃት/ኢህአዴግ መንግሥት የማስተዳደር ስልት ችግሩን በዘዴ በመፍታትና በማግባባት ሳይሆን ኃይልን በመጠቀም ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን ነው፡፡
በአጠቃላይ እንደዚህ ያሉ የከፉ የሰብአዊ መብት ረገጣ አገር ተረካቢውን ወጣት ምሁር ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል፡፡
ስለዚህ የመላው ኢትዮጰያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመቃወምና ከተበዳዮች ጐን የቆመ መሆኑን ለማሳየት “ሕዝባዊ አንድነት ለነፃነት” በሚል መሪ መፈክር በመላ አገሪቱ ሕዝባዊ ንቅናቄ ለመፍጠር ከዜጎች ጐን የቆመ ድርጅት መሆኑን ለማሳየት ሰላማዊ ሰልፎችን አዘጋጅቷል፡፡ በዚሁ መሠረትም እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም በጐፋ ልዩ ዞን በሳውላ ከተማ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አድርጓል፡፡
ስለዚህም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት ሲል ከጐናችን እንዲሰለፍ ታላቅ ሕዝባዊ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ከሱዳን ካርቱም የደረሰኝ መረጃ]በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመባቸው ነው

በሱዳን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ቀጥሏል:: በየጊዜው ለስራ ፍለካ ምክንያትና በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ሀገራቸውን እየለቀቁ ወደ ሱዳን የሚገቡ ኢትዮጵያኖችን ብዙ ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያኖች ወደ ሱዳን ከገቡ በኋላ ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል :: በተለይም በሱዳን በሚኖሩ ኢትዮጵያን ዜጎቻችን ላይ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ኢሰብዓዊ ድብደባ እየተፈጸመባቸውና በሀገሪቱ ፖሊስ እና በሱዳን ማህበረሰብ ዘግናኝ ግፍና በደል እየደረሰባቸው እንዳለ ለማወቅ ተችሏል :: በዛው በሱዳን ካርቱም ነዋሪ ከሆነ ግለሰበ እንዳገኘውት ምንጭ ከሆን በኢትዮጵያኖች ላይ ፖሊስ የተለያያ ድብደባና ጥቃት የሚያደርስባቸው ሲሆን በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ሴቶች በእነዚህ ፖሊሶች እና በወጣት ሱዳን ወንዶች በግሩፕ በየቦታው እየተደፈሩ ሲሆን በፖሊሶችና በሱዳን ወጣት ወንዶች ወሲባዊ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል::
እነዚህ በሱዳን የሚኖሩኢትዮጵያውያኖች የድረሱን ጥሪ አያቀረቡ ሲሆን ነገር ግን ማንም ሊደርስላቸው እንዳልቻለና በሱዳን ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት ጥረት እያደረገላቸው አይደለም:: ኢምባሲው ወገኖቻችን ችግር ሲደርስባቸው ፈጥኖ ደርሶ የዜጓቹን ችግር ከመፍታት ይልቅ በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የማፍያዎች ስብስብ ሆኖል ስለ ዜጋ የሚቆረቆርና ሀላፊነት የሚሰማው አንድም ሰው የለም ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛ የሆኑ ለሕዝብ የሚያገለግሉና ሀላፊነት የሚሰማቸው ሰዎች እንዳይደሉ ::ነገር ግን እዛ ቁጭ ብለው ምንም ስራ እንደማይሰሩ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ስም ብቻ በሙስና ሀብት ማካበት ብቻ እንደሆነ የደረሱኝ መረጃዎቹ ይጠቁማሉ ::
በነዚህ ሁለት ወራት ውስጥ በጣም አሳዛኝ ነገር ከመቼውም ጊዜ በተለየ ለየት ያለ ኢትዮጵያዊያንን የማጥቃት ዘመቻ በካርቱም ተጦጥፎ ይገኛል:: ካርቱም ያሉ አራቱም ወህኒ ቤቶች ኩበር፣ሶባ፣ኦምዱራምሃ፣ሀል ሁዳ የተባሉ እስር ቤቱች በእስረኛ ተጨናንቀዋል በተለየ ኢትዮጵያኖች ከአስር እስከ ሃያ አመት ፍርደኛ ናቸው:: አንዲትም ቀን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሂዶ ጠይቋቸውም አያውቅም በአሁኑ ሰአት ደግሞ ህገ ወጥ ስደተኛ ተብለው ከሶስት መቶ በላይ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች በሆዳ እስር ቤት ይገኛሉ እንደዚሁ ህገ ወጥ ስደተኛ ተብለው ሆዳ እስር ቤት የታጎሩ ሰዎች ባለፈው 21/5/2014 ሶስት ኢትዮጵያውያን ሞተዋል:: ምክንያቱም ለሰባት ቀን ያህል በር ተዘግቶባቸው ያለ ምግብና ውሃ በመቆየታቸው ሰውነታቸው ተዳክሞ ሲሆን ሌሎች 30 ሰዎች በወህኒ ቤቱ ግቢ ህክምና ተደርጎላቸው አስራ ሁለቱ ከተወሰነ ሰአት በኋላ ሲመለሱ አስራ ስምንቱ በአንድ የፖሊስ ሆስፒታል በዝግ አይሱዚ መኪና ተወስደዋል:: በወቅቱ ጉዳዩን መቀመጫው ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ አማባሳደር አቶ አብዲ ዘሙ ተደውሎ ተነግሯቸው የነበረ ሲሆን እሳቸው ግን ችግሩን ችላ በማለት ጅብ ከሄድ ውሻ ጮኸ እንደሚባለው በነጋታው ሰው በማስላክ አይተዋቸዋል ::ከዛ እንደለመደው በመዋሸት ምንም የሞተ ሰው የለም በማለት አወራ::ምክንያቱም ጉዳዩን ካርቱም ያለ አብዛኛው አበሻ ስለሰማ ለመሸፋፈን ቢሆንም ነገር ግን ሆስፒታል የነበሩ የተቀሩት ሐበሾች ወዲያውኑ ከተመለሱ ጉዱ ስለሚገለጥ ፍርዳቸውን ሳይጨርሱ የት እንደሚወስዶቸው አልታወቀም ፈተው ወደ ሀገር ቤት እባረዋቸው ይሆን ወይም እነሱም የሶሰት ወንድሞቻቸው እጣ ፈንታ ደርሶቸው ይሆን ምንም የታወቀ ነገር የለም::
ሌላው በጣም የሚገርመው ነገር በዛው ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ባሉት አረመኔዎች እህቶቻችን ወሲባዊ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል::አቶ መሀመድ ቱፋ የሚባል የኢምባሲው ሰራተኛ የሆነ ከኢትዮጵያ ጫት እያስመጣ የሚነግድ አደገኛ የጫት ነገዴ እንደሆ ነው የሚነገርለት::ሌላው ደግሞ ሌባ የኢምባሲው ሰራተኛ አቶ በላቸው ገብረ መስቀል ይባላል ከአሁን በፊት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በካርቱም ብር ዘርፎ ሀገር ቤት ሄዶ ነበር ተመልሰው አምጥተውት ከፍ ያለ ስልጣን ተሰቶት ካርቱም በኢትዮጵያ ኢምባሲ እየሰራ ነው:: ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ባጠቃላይ የህገ ወጡች ስብስብ ሆኖል::

 ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና

አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ “የኢህአዴግ በርዕዮተዓለም መበላላት ይፋ እየሆነ ነው”


አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል።
በቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳና በአቶ ድሪባ ላይ ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገር ጥለው እንዳይወጡ በሚል ነው። ጎልጉል በቅርቡ ካገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ውሳኔው የተላለፈው ሰሞኑን የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ለመተግበር የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካተታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው። ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከፍተኛ የክልልና የዞን የኦህዴድ አመራሮችም በደህንነት ቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ተሰምቷል። ካገር መውጣት የማይችሉም አሉ።
አባ ዱላ /ጃርሳው/
ሙክታር
ሙክታር
አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲረከቡ በማክረር አካሄድ የሚታወቁት አቶ ጁነዲን ያዋቀሩትን ካቢኔ በመበተን ሥራቸውን አንድ ብለው ጀመሩ። አዲስ ካቢኔ ሲገነቡ የመረጡት አዲስ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችንና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቀናቃኝ (የተቃዋሚ) ፓርቲ አባላትን በማስኮብለል ነበር። ህወሃት ለሁለት በተበረገደበት ወቅት ለአቶ መለስ ቡድን ድጋፍ በመስጠት ቅድሚያ የያዙት አባ ዱላ ባስቀመጡት ውለታ መሰረት ኦሮሚያ ላይ ያሻቸውን እንዲያደርጉ የሟቹ መለስ ድጋፍ ነበራቸው። በዚህም ድጋፍ ሳቢያ ኦሮሚያ ላይ የሚፈልጉትን ሲያደርጉ ከተባረሩት መካከል የአሁኑ ፕሬዚዳንት ሙክታር ከዲር ይገኙበታል።
“አትደግፉን ነገር ግን የክልሉን ልማት አታደናቅፉ” በማለት አዲስ የመለመሏቸው የተለያየ አመለካከት ያላቸው አዳዲስ የኦህአዴድ አባላት ኦሮሚያን ከአባ ዱላ እጅ ተረከቡ። አባ ዱላ ፍጹም ነጻነት ይሰጡ ስለነበር ካድሬው ወደዳቸው። ስማቸው ተቀይሮ መለያ ተሰጣቸው፤ “ብራንድ” ሆኑ – “ጃርሳው” ተባሉ። በካቢኔያቸውና በሳቸው መካከል የነበረው ፍቅር በነደደበት ወቅት አባ ዱላ ክልሉን እንደሚለቁ ተሰማ። ባለፈው ምርጫ አባ ዱላ ለፌዴራል እንጂ ለክልል እንደማይወዳደሩ ይፋ ሲደረግ ካድሬው ገነፈለ። “የኢህአዴግ ምክር ቤትን ውሳኔ አንቀበልም” በማለት ተቃወመ። ከአንዴም ሁለት ጊዜ ስብሰባ ቢካሄድም ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተበተነ። በመጨረሻም ራሳቸው አባ ዱላ በመሩት ስብሳባ ካድሬውን ተማጽነው ነገሩ ረገበ። ይሁን እንጂ ቅርሾ ግን ነበር። ይህንኑ አስመልክቶ “ኦህዴድ/ኢህአዴግ በመደብ ትግል መተላለቅ ጀመረ” በማለት ዘግበን ነበር።
አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲመሩ ቆይተው ሲመሻሸ “ይህንን ቤት ይዤ ለመታገል አይመቸኝም” በማለት ቦሌ ያስገነቡትን አስገራሚ ህንጻ ለኦህዴድ አስረከቡ። በከፍተኛ ሙስና ይታሙ ስለነበር ተናዘውና ገብረው ታለፉ። ለፌዴራል ተወዳድረው አፈ ጉባኤ ለመሆን በቁ። በወቅቱ የወ/ሮ አዜብ ድጋፍ ቢኖራቸውም የሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን የቀኝ እጅ የሆኑ ባለስልጣኖች ግን ጠምደዋቸው ነበር። ሙክታር አህመድ አንዱና ዋናው ነበሩ። ከላይ በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ አባ ዱላን ከሚቃወሙ መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚቀመጡ ናቸው።
በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ አልፈው እዚህ የደረሱት አባ ዱላ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች ህይወት የቀጠፈውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አስመልክቶ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ተማሪዎችን ከወ/ሮ አስቴር ማሞ ጋር በመሆን አነጋግረው ነበር። በወቅቱ የተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሃዊ እንደሆነ ሲመሰክሩ፣ ይህንኑ ምስክርነታቸውን ለተለያዩ የአገር ውስጥና የውጪ አገር ሚዲያዎች አሳውቀውም ነበር። አያይዘውም ነፍስ ያለ አግባብ ያጠፉ እንደሚጠየቁ ቃል ገቡ።abadulla
የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት አባ ዱላ ይህንን ከተናገሩ በኋላ ከፍተኛ ወቀሳ ተሰንዝሮባቸዋል። “ረብሻውን ያስነሱት ራሳቸው የኦህዴድ ካድሬዎች ናቸው” ከሚል ድምዳሜ የደረሰው ኢህአዴግ ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ ሰፊ የስለላ ስራ አከናውኗል። “ጥፋተኞቹን ለህግ እናቀርባለን” በማለት መግለጫ ያወጣው ኢህአዴግ በቀጣይ የሚያስራቸውና የሚከሳቸው ባለስልጣኖች አሉ። ምንጮቹ በተለይ አባዱላና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ ላይ ስለሚወሰደው ርምጃ ያሉት ነገር ግን የለም። ክስ ከተመሰረተባቸውና ምርመራው በሰንሰለት ታች ድረስ ከዘለቀ የኦህአዴድ የታችኛው መዋቅር ሊናጋ እንደሚችል ግን ግምታቸውን አኑረዋል። ለምሳሌ ያነሱት ሽፈራው ሽጉጤን ነው። ሽፈራው ሽጉጤ በሙስና እንዲከሰሱ ከተወሰነ በኋላ የታለፉት “የሲዳማ ብሔረሰብ ይነሳል” በሚል እንደሆነ ያወሱት ምንጮች “ክስ ተመስርቶ ምርመራው ቢካሄድባቸው ወ/ሮ አዜብም አሉበት ሲሉ አስቀድመው በምክር ቤት ይፋ በማድረጋቸው ዝምታ ተመርጧል”።
ኦህዴድን ወደ ታች ማዘዝ እንደ ቀድሞው አይቀልም
አዲስ አበባን የሚያሰፋው አዲሱ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን ሀሳብ ሲቀርብ ድፍን የኦህዴድ ምክር ቤትና ካቢኔ ተቃውሞ አሰምቷል። በክልሉ ምክር ቤት ደረጃም የተያዘው አቋም ተመሳሳይ ነው። ይህንን እውነት የሚያነሱ ክፍሎች ኢህአዴግ/ህወሃት ስንቱን አስሮና ለፍርድ አቅርቦ ይችለዋል ሲሉ ጥያቄ ይሰነዝራሉ” ቀደም ሲል በምርኮኞች ስብስብ የተቋቋመው ኦህዴድና አሁን ያለው ኦህዴድ የተለያዩ መሆናቸውን ኢህዴግ ችግር ሊገጥመው እንደሚችልም ግምታቸውን ያስቀድማሉ።
አሁን ያለው ኦህአዴድ ከምርኮ አስተሳሰብ የተላቀቀ። አዲስ ትውልድ የተካተተበት፣ በጎሳ አስተሳሰብ የተቃኙ፣ ህወሃት በሚፈልገው መጠን ከመታዘዝ በላይ ወደ ራሳቸው ደምና ጎሳ የተሳቡ፣ ይህንኑ አስተሳሰብ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ የተከሉ በመሆናቸው የተወሰኑ የበላይ አመራሮችን በማሰር ችገሩ ሊፈታ እንደማይችል ሰፊ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ለዚህም ይመስላል ኢህአዴግ በመደብ መተላላቅ መጀመሩ ይፋ እየሆነ የመጣው።
የመጨረሻው መጀመሪያ
ለጊዜው ይፋ ሆኑ መረጃዎች እንደሚያመክቱት አባዱላና አቶ ድሪባ ኩማ ካገር መውጣት አይችሉም። የተጀመረው ግምገማ ተጠናቆ የሚሆነው ሳይታወቅ በቅርብ ክትትል ስር ናቸው። የጎልጉል ምንጮች እንደጠቆሙት የዞንና ወረዳ መዋቅሮች ላይ ርምጃ ለመውሰድ  ስጋት አለ። ካድሬው ዘንድም መደናገጥ ተፈጥሯል። ህወሃት ውስጥም የአቋም መለያየት ተከስቷል፡፡ በአንድ ወገን ካድሬው እንዳይሸፍትና በቀጣዩ ምርጫ ኢህአዴግን አሳልፎ እንዳይሰጠው ርምጃው የተለሳለሰ መሆን አለበት እየተባለ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ግለ ሂስ በማካሄድ ነገሩን የማርገብና ምርጫውን የማለፍ ስልታዊ አካሄድ አለ። ይሁን እንጂ ኦህዴድ እየተለማመደ ያለው አካሄድ ሌሎችን ትምህርት በሚሰጥ መልኩ ካልታረመ ወደ ፊት ችግሩን ያገዝፈዋል የሚል አቋም የሚያራምዱ መኖራቸው ታውቋል። ህወሃት በዚህ ደረጃ አቋም ለመያዝ አለመቻሉና በርዕዮተ ዓለም መከፋፈል መጀመሩ ለዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የዘራው መርዝ መልሶ ራሱን ሊያጠፋው አፉን መክፈቱ የሚጠቁም ነው፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት “ኢህአዴግ በርዕዮተ ዓለም መበላላት መጀመሩ ይፋ እየሆነ ነው” የሚለው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚነሳ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል፡፡
ምንጭ www.goolgule.com

Monday, May 26, 2014

Ethiopia: Crimes Against University Students and Humanity

Ethiopia: Crimes Against University Students and Humanity
May 26, 2014
On May 2, 2014, BBC reported that the security forces of the regime in Ethiopia had massacred at least 47 university and high school students in the town of  Ambo 80 miles west of the capital Addis Ababa. The regime dismissed the massacre and tried to sweep it under the rug claiming that a “few anti-peace forces incited and coordinated the violence”.  There has been little international coverage or outrage over the massacre.
Human Rights Watch (HRW) issued a statement condemning the “shooting at and beating [of] peaceful protesters in Ambo, Nekemte, Jimma, and other towns”. According to HRW, the student “protests erupted over the release of the proposed Addis Ababa Integrated Development Master Plan” which would “expand Addis Ababa’s municipal boundary to include more than 15 communities in Oromia” and displace Oromo farmers and residents.HRW demanded an immediate end to theexcessive use of force by the regime’s security forces against peaceful student demonstrators.The massacre of Ambo University and high school students
I am outraged beyond my ability to express my outrage in words. I grieve and ache for the students cut down by hails of bullets in the prime of their lives. They had an undeniable constitutional right to peacefully petition for grievances; because they exercised that right, we must now all grieve for them. I grieve for Ethiopia for it has lost its best and brightest children. I extend my deepest condolences to the families and friends of the victims of the massacre.
I abhor massacres. I got involved in Ethiopian and African human rights advocacy following the post-2005 election massacres of unarmed protesters in Ethiopia. Prior to that time, I had virtually no involvement in Ethiopian politics. I did not know the name Meles Zenawi “from Adam’s off ox”.
When troops under the personal control and command of the late Meles Zenawi massacred some 200 unarmed demonstrators and shot and wounded nearly 800 more (the actual figure is documented to be much more than that), I was hopping mad as hell. I just could not let Meles and his criminal gang get away with mass murder. For the past eight years, I have been advocating and promoting human rights in Ethiopia and Africa every single Monday without missing a single week.
I am hopping mad as hell today over the massacre of the dozens of unarmed university and high school students in Ambo and elsewhere as I was in 2005 when hundreds of unarmed protesters were slaughtered. I am hopping mad as hell that no one is ever held accountable for massacring innocent people in Ethiopia. There is a long and shameful culture of impunity in Ethiopia. Mengistu Hailemariam committed mass murder and has not been held accountable. That mass murderer said he “did not hurt a fly” while he was in power. He did kill tens of thousands of innocent people. He is comfortably living out his twilight years in Zimbabwe writing fiction and fables about his time in office.
Meles Zenawi received divine justice. His surviving disciples and comrades today thumb their noses at justice. The perpetrators of the massacres of 2005 today roam the streets free. Yet we know the names of each and every “federal police” thug who participated in the massacres. In a report entitled “Modernizing Internal Security in Ethiopia” counterterrorism expert Col. Michael Dewar, British Army (Rtd.) revealed that the Director General of the Ethiopian Federal Police Werkneh Gebeyehu told him that “as a direct result of the 2005 riots, he [had] sacked 237 policemen.” Not a single one of these  criminals who committed the massacres or the criminal bosses who ordered the massacres have been brought to justice.  Meles’s own Inquiry Commission in 2007 damned Meles for the use of deadly force and absolved the peaceful unarmed protesters of any criminal or civil liability.
In December 2003, Meles Zenawi’s troops in a series of attacks in Gambella killed 400 Anuaks and destroyed over 1000 homes. The Meles regime subsequently issued a statement “apologizing for not acting proactively and promised to stand on the side of the victims to see that justice is done.” At the time, the regime claimed to have identified dozens of suspects in the Anuak massacres. No soldier, police or security official has ever been prosecuted, held accountable or sanctioned for those crimes against humanity in Gambella.
Beginning in October 2007, Meles Zenawi launched a crackdown against insurgents in the Ogaden region which quickly expanded into a program of collective punishment for Ogadeni civilians. Meles’ troops destroyed  entire villages and committed rape, murder and pillage. They hanged and beheaded suspects to terrorize the population. A Human Rights Watch told the U.S. House Foreign Affairs Subcommittee on Africa and Global Health that “the Ogaden is not Darfur. But the situation in Ogaden follows a frighteningly familiar pattern”. Retired general and formed U.S. Secretary of State Colin Powell declared genocide had occurred in Darfur. By the same token, in 2007-08 a “mini-genocide” occurred in the Ogaden. No one has been brought to justice for the Ogaden massacres. The catalogue of massacres by the regime in Ethiopia is voluminous.
I have no illusions that those who committed the “Black Tuesday” massacres at Ambo University and other institutions and towns will ever be brought to justice under the current regime. Not only will there be no prosecution, there will not even be an investigation. The best that could be expected is a kangaroo police investigation if the public could bring sustained pressure on the regime. Of course, the outcome will be a surefire whitewash. The final report of that kangaroo investigation will conclude that a “few anti-peace forces incited and coordinated the violence.”
Opposition leaders inside the country and in the Ethiopian Diaspora must speak in one voice in demanding a swift and independent investigation into the massacres in Ambo and elsewhere. We have to go beyond moral condemnations and demand legal action in local kangaroo courts and international tribunals. We should put the kangaroo courts on trial in the court of international public opinion. We must take advantage of remedies available in international bodies and political institutions in donor states.
I am calling on the regime to launch an independent investigation into the massacres of Ambo University students and other peaceful protesters in Nekemte, Jimma and other locations. I am under no delusion or illusion that the regime will heed my call. I know they do not give a rat’s behind about anything I say.
I am calling for an independent investigation for a different reason. I want to name and shame the Obama Administration, the Cameron Government in the U.K., the European Union, the World Bank, the International Monetary Fund and the rest (except China for whom a single death is a tragedy and thousands of deaths a statistic) who provide billions of dollars annually to a regime that massacres its best and brightest youth. I want to call attention to the fact that American, British and European taxpayers are bankrolling child killers in Ethiopia. I want to call attention to the fact that the silence of the West in the face of such horrific crimes against schoolchildren and university students cries out to their complicity in crimes against children, crimes against the most vulnerable members of humanity.
Only the Western donors and loaners have the financial muscle to demand and insist on an independent investigation so that the police and security officials who committed the killings of the Ambo schoolchildren and university students and those who authorized or condoned it could be brought to justice. I also know for a fact that the Western bankrollers of the regime will never call for an investigation because they don’t give a  s _ _t about Ethiopia’s children. I am calling them out though!!!
In my call for an investigation, I accuse the Obama Administration, the Cameron Government, the European Union, the World Bank and the International Monetary Fund as the silent aiders and abettors before and after the fact in the commission of crimes against humanity in Ethiopia. They know in their own laws that those who aid and abet directly or indirectly in the commission of a crime are just as guilty as those who actually committed the crime.  George Bush said, “We will make no distinction between the terrorists who committed these acts and those who harbor them.”  Well said.
I have a personal confession to make. Perhaps it will help my reader understand why I am hopping mad about the massacre of Ambo University and high school students and others. The Ambo massacres are not mere issues of human rights advocacy. They are personal.  As I imagine things, I tell myself that in a different place and in a different time, the massacred students could have been MY students taking my courses. They could have been in my lecture classes or sitting in my advanced special topics seminars.  I would have known each one of them by name. I would have read their papers and graded their exams. I would have stopped them on campus and asked them why they missed class and enjoy watching them squirm trying to come up with excuses. I would have challenged them to achieve academic excellence. They could have been my advisees. I could have mentored them for a career in the legal profession or other areas of public policy. I could have written them recommendation letters. I may even have been able to help place the most able ones at some of the best graduate and professional schools in the world. They could have been MY students!!!
I would have been very proud to have them as MY students.  I would have challenged them to think critically. I would have challenged them not to think outside the box but to make their own thought boxes. I would have taught them to challenge the orthodoxy of ideas and always be skeptical of dogma and ideologies. I would have taught them to be open and independent-minded and act on evidence instead of hunches and emotions.  Above all, I would have taught them to stand up for their beliefs and never, never back down from speaking truth to tyranny. How I would have been proud to be their teacher and mentor!
Just as I believe Ethiopia’s youth are Ethiopia’s future, I also believe America’s youth are America’s future. American college and university students have been the tip of the spear in social and political change. So have Ethiopian university students. From the days of the Freedom Rides to the Free Speech Movement at UC Berkeley to the anti-war movement in the 1960s, American university students remained in the vanguard of social and political change. So were Ethiopian university students from the days of imperial rule.
Things changed on American campuses on May 4, 1970 at Kent State University in Ohio when Ohio National Guardsmen opened fire on unarmed college students firing 67 rounds over a period of 13 seconds. Those students were protesting President Nixon’s expansion of the Vietnam War into Cambodia. The Kent State massacres were the only time in American history that tens of millions of American university and high school students went on strike and closed down their institutions. The Kent State killings were the straw that broke the camel’s back. By 1973, the Vietnam War had effectively ended as the U.S. began withdrawing its combat units.
For the past 44 years, the U.S. government has refused to acknowledge responsibility for the Kent State killings. That has not stopped patriotic Americans from seeking accountability for the massacre, including efforts to hold the U.S. government accountable before the United Nations Human Rights Committee. The Kent State killers may never be brought to justice, but the ongoing efforts on their behalf sends a clear message to the U.S. government that it cannot use its armed forces (or its drones) to kill citizens for expressing their dissenting political beliefs.
The Ambo University and high school students and others at least deserve as much as the Kent State University students. We must never stop demanding justice for them before domestic courts or international tribunals.  I call for an investigation not only to name and shame the regime’s international supporters but also because I believe, as did James Russell Lowell, that “Truth (will not) forever (remain) on the scaffold, (nor) Wrong (remain) forever on the throne.” I believe that “behind the dim unknown, Standeth God within the shadow, keeping watch above his own.”
Speak up and demand justice for the massacred Ambo University and high school students and others!
When Ambo University students were massacred, not all of Addis Ababa University students came out. Many remained silent. Mekele University students did not protest. They stayed put and remained silent. Students at Bahr Dar, Gondar, Dire Dawa and other universities also remained silent.
Silence in the face of crimes against humanity – my silence, your silence, the silence of the Obama Administration, the Cameron Government, the European Union, the World Bank, the IMF and the African Union — is the real criminal as we have learned from Martin Neimoller, the German anti-Nazi theologian and Lutheran pastor:
When the Nazis came for the communists,
I remained silent;
I was not a communist.
When they locked up the social democrats,
I remained silent;
I was not a social democrat.
When they came for the trade unionists,
I did not speak out;
I was not a trade unionist.
When they came for the Jews,
I remained silent;
I wasn’t a Jew.
When they came for me,
there was no one left to speak out.
I feel the same way as Nimoller.
When they came for the Amharas “sefaris from North Gojam” in Bench Maji,
When they ethnically cleansed the Amharas in Benishangul,
I remained silent;
I was not an Amhara.
When they hunted down and killed the Anuaks in Gambella,
I remained silent;
I was not an Anuak.
When they strafed and bombed the Ogadenis and burned their villages,
I remained silent;
I was not an Ogadeni.
When they built dams and damned the Omotic peoples,
I remained silent;
I was not Mursi, Suri, Nyangatom, Dizi or Me’en.
When they massacred Oromo students in Ambo,
I remained silent;
I was not an Oromo student.
When they came for me,
there was no one left to speak out.
For me, it does not matter if you are an Oromo, a Tigrean, an Anuak, a Gurage, an Amhara, an Ogadeni, a Mursi… For me, you are an Ethiopian. I love you just as you are! I will NEVER, NEVER remain silent when you are victimized by human wrongs and deprived of your human rights!
Lately, I have been cross with Barack Obama. In as much as I was his staunchest supporter in 2008, I am his staunchest critic in 2014 on his human rights (wrongs) policy in Africa. Regardless, I will always agree with his fundamental values about America. “There is not a liberal America and a conservative America—there is the United States of America. There is not a Black America and a White America and Latino America and Asian America—there’s the United States of America.”
For me there is not an Oromo, a Tigrean, an Amhara, a Gambellan, an Ogadeni, a Mursi, a Gurage… Ethiopian – there is only an Ethiopian. For me, our humanity in our Ethiopianity is infinitely more important than our identity in our ethnicity. This is my simple creed!!!
Professor Alemayehu G. Mariam teaches political science at California State University, San Bernardino and is a practicing defense lawyer.
posted by Metasebia Tadesse

Sunday, May 25, 2014

ከአያት መገናኛ የተነጠፈው የባቡር ሐዲድ እየተቀየረ ነው

Rails in the Ayat-Megenagna Section are being Replaced .....
ከአያት መገናኛ የተነጠፈው የባቡር ሐዲድ እየተቀየረ ነው
በአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር መስመር ዝርጋታ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ በሚገኘው የአያት መገናኛ መስመር ላይ የተነጠፈው 
ሐዲድ፣ ከመሥፈርቱ ውጪ በመሆኑ ምክንያት በሌላ ሐዲድ በመቀየር ላይ ነው፡፡ ከሳምንት በፊት የተጀመረው ቀደም ሲል የተዘረጋውን ሐዲድ የመቀየር ሥራ በአሁኑ ወቅት ከአያት ወደ ሲኤምሲ አካባቢ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር የሆነውን ቻይና ሬልዌይ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንና የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ የሆነውን ስዌድሮድ የተባለ የስዊድን ኩባንያ ሪፖርተር ለማነጋገር ቢሞክርም፣ በኮንትራት ስምምነቱ መሠረት ለሚዲያ መግለጫ መስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ግን የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር የመጀመሪያውን ሐዲድ የማንጠፍ ሥራ ሲጀምር፣ በኮንትራት ስምምነቱ ላይ በተቀመጡት መሥፈርቶች መሠረት እንዲሠራ ተነግሮት ነበር ብለዋል፡፡ በኮንትራት ስምምነቱ ላይ የተቀመጠው መሥፈርት አንዱ ባለ 25 ሜትር ሐዲድ ከሌላኛው ጋር የሚገናኘው በኦክስጅን ብየዳ እንደሆነ ቢገልጽም፣ ኮንትራክተሩ ግን የተቀመጠውን መሥፈርት እያወቀና በተቆጣጣሪ (አማካሪ) ድርጅቱ በተደጋጋሚ እየተነገረው ሐዲዱን መዘርጋት እንደቀጠለበት ምንጮች አስረድተዋል፡፡
አማካሪ ድርጅቱ ባለበት ኃላፊነት መሠረት ጉዳዩን ከማሳሰብ ባለፈ ለተዘረጋው ሐዲድ የሚቀርብ የክፍያ ጥያቄን እንደማያጸድቅ ግልጽ በማድረጉና በሌሎችም ምክንያቶች፣ ኮንትራክተሩ የስምምነት መሥፈርቱን ለማክበር እንደተገደደ ያስረዳሉ፡፡ ከአያት መገናኛ ባለው መስመር ላይ ተነጥፈው የነበሩት ሐዲዶች ብዛት 960 ሲሆኑ፣ እያንዳንዳቸው 25 ሜትር ርዝመት እንዳላቸው የሚያስረዱት ምንጮች፣ እየተነሱ ያሉት በመሥፈርቱ መሠረት መበየድ የማይችሉ ሆነው ስለተገኙ እንደሆነ ገምተዋል፡፡

‹‹ሙሉ በሙሉ መቀየር አለባቸው፡፡ ይህ ማለት ግን አገልግሎት አይሰጡም ማለት አይደለም፡፡ ምናልባት ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ለሚዘረጋው የባቡር መስመር ሊያገለግሉ ይችላሉ፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ አሁን ለተፈጠረው ችግር ምክንያቱ ኮንትራክተሩ እንደሆነ፣ ወጪውም ሙሉ በሙሉ የራሱ እንደሚሆን የሚያስረዱት ምንጮች፣ በዚህ ምክንያት የፕሮጀክቱ ጊዜ ተስተጓጉሏል ማለት እንደማይቻል ይገልጻሉ፡፡ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ሐዲድ ማንጠፍ በዚህ ፕሮጀክት ላይ ቀላሉ የሥራ ዓይነት መሆኑን፣ በአጠቃላይ 34 ኪሎ ሜትሩ ላይ ሐዲድ የማንጠፍ ሥራ በአንድ ወር ማጠናቀቅ የሚቻል መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር በኃይሉ ስንታየሁ ተጠይቀው፣ የተነጠፈውን የሐዲድ መስመር የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ አፅድቆ እንዳልተረከበ ተናግረዋል፡፡ የኮንትራት ስምምነቱ የሐዲድ መስመሩ ‹‹ኮንቲኒየስሊ ዌልድድ›› ወይም አንድ የሐዲድ ብረት ከሌላኛው ጋር ያለምንም ክፍተት ተበይዶ መያያዝ እንዳለበት ያመለክታል ብለዋል፡፡ በመገናኛ አያት መስመር ላይ የተዘረጋው በዚህ መሠረት ሳይሆን ብሎን በማያያዝ በመሆኑና ይህ ደግሞ መሥፈርቱን የማያሟላ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሪፖርተር በሥፍራው ተዘዋውሮ እንደተመለከተውና በፎቶግራፉ ላይም እንደሚታየው ቀደም ሲል የተነጠፉት ሐዲዶች እየተነሱ ነበሩ፡፡ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር በኃይሉ ግን፣ ‹‹እየተነሱ ያሉትን በማሳሰብና በማጠጋጋት ለመበየድ ነው እንጂ የሐዲድ ብረቶቹ እየተቀየሩ አይደሉም፤›› በማለት ያስተባብላሉ፡፡
የሐዲድ ማንጠፍ ሥራው ከመጀመሪያውኑ በመሥፈርቱ መሠረት ለምን በብየዳ አልተሠራም በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹መጀመሪያና መጨረሻ የሚባል ነገር በአሁኑ ወቅት የለም፡፡ እኛ ገና አልተረከብናቸውም፡፡ ምክንያቱም ገና ሒደት ላይ ነው ብለዋል፤›› ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል የተነጠፉትን ሐዲዶች በሌላ የመቀየር፣ እርስ በርስ የመበየድና የማያያዝ ተግባር በጐተራ መስመር ላይም መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህ ላይም የተጠየቁት ኢንጂነር በኃይሉ፣ የተነጠፉት ሐዲዶች እርስ በርስ ባልተበየዱባቸው ወይም በብሎን ብቻ በተያያዙባቸው ቦታዎች ላይ ሁሉ የመበየዱ ሥራ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ፕሮጀክት 34 ኪሎ ሜትር ሲሸፍን፣ ከምሥራቅ ምዕራብ እንዲሁም ከሰሜን ደቡብ የሚዘረጋ ነው፡፡ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ 475 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ሲጠበቅ፣ ከጠቅላላ ወጪው 85 በመቶ የተገኘው ከቻይና መንግሥት በብድር ነው፡፡
Rails in the Ayat-Megenagna Section are being Replaced Rails that have...
DIRETUBE.COM

Saturday, May 24, 2014

የዛሬው የመድረክ ፓርቲ ሰልፍ ለጉድ ነው !!!!

The demo is underway in Addis. " Stop eviction of farmers in the name of development".

በ10 ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ የተሳተፈበት ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባን አጥለቅልቋታል።
ስላማዊ ሰልፉን የጠራው በፕሮፌሰር መራራ ጉድና የሚመራው መድረክ ፓርቲ ነው።
ሃሳባችንን በነጻነት መግለጽ እንፈልጋለን ! ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችን ይከበር!!!
ተቃውሞ ባሰም የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እናወግዛለን !!!
መድረክ ለኦሮሞ ተማሪዎች ያለውን አጋርነት ይገልጻል !! ቪቫ መድረክ !!!
መድረክ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ከሚጠበቀው በላይ በድምቀት እየተካሄደ መሆኑን ከስፍራው የደረሱን መርጃዎች ይጠቁማሉ።
ግምቱ በ10ሺዎች የሚገመት የአዲሳበባ እና አዋሳኝ ከተሞች ህዝብ ዋና ከትማዋን በሰልፍ አጥለቅልቋታል የዛሪው ሰላማዊ ሰልፍ ድንቅ ነው በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በእንግሊዘኛ መፈክሮች ያነገቡ ከአዛውንት እስከ ወጣት እና ሴቶች ሰልፈኞች አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምትዋል።
"Stop the massacre!. Bring culprits to justice! Free all political prisoners! Stop the land grab!" Well done Medrek!
Like ·  · 

በኮልፌ ቤቱ የፈረሰበት አባወራ በጅብ ሲበላ አንዲት ወላድ በድንጋጤ ህይወቷ አለፈ

news‹‹ቪዛ ይሰጠንና ወደ ሱማሌያ ቢሆንም እንሂድ›› ቤታቸው የፈረሰባቸው

በኮልፌ ቀራኒዮ አለም ባንክ አካባቢ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በማድረግ ቤቶችን ሰርታችኋል የተባሉ ዜጎች ቤቶቻቸው በላያቸው ላይ በሀይል ፈርሶ ንብረታቸው መወረሱን አመለከቱ፡፡ 
ከ15.000 የሚልቁ ነዋሪዎች በሚገኙበት አለም ባንክ አካባቢ ሰዎቹ አነስተኛ መጠለያ ያረፉባቸውን ቤቶች ከገበሬዎች ላይ በመግዛት መኖር ከጀመሩ አመታት መቆጠሩን ያስረዳሉ፡፡ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ልከውና ወደ ስራ በተሰማሩበት ቅጽበት ከጸጥታ ሰራተኞች ጋር አካባቢውን የወረሩት አፍራሽ ግብረ ሃይሎች መኖሪያ ቤቶቹን ማፍረሳቸውን በሀዘን ተውጠው ገልጸዋል፡፡ 
ቤቶቹ በድንገት መፍረሳቸውን በመቃወም ድምጻቸውን ያሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊሶች ክፉኛ መደብደባቸውንና መወሰዳቸውን የአይን እማኞች አስረድተዋል፡፡ቤቷ ሲፈርስ የደነገጠች እመጫት ወዲያኑ ህይወቷ ሲያልፍ ቤቱ በመፍረሱ መሄጃ ያጣ አባወራ ላስቲክ ዘርግቶ በተኛበት ጅብ ጎትቶት ወስዶት በልቶታል፡፡በጅብ የተበላው አባወራ ስርዓተ ቀብርም ዛሬ መፈጸሙ ታውቋል፡፡ ቤታቸው ፈርሶ ለጎዳና እንደተዳረጉ የሚናገሩ ሰዎች‹‹ኢትዮጵያዊነታችን ተሰርዟል፣ቪዛ ይሰጠንና ሌላው ቢቀር ወደ ሶማሊያ እንድንሄድ ይደረግ ›› ብለዋል፡፡
source justiceethio.wordpress.