Saturday, May 24, 2014

ለምን ከ6606 ኤርትራውን ባንዳዎቻቸው መካከል መቶ ወይም አንድ ሺህ የለም እኔ በጣሊያን አልገዛም ብሎ ከትግራይ ወንድሞቹ ጋር አልተቀላቀለም???

ለምን እነ ራስ መንገሻ ትግራይን አናስይዝም ብለው አምጸው ድረሱልን አሉ ??ይህ እንዳይደረገም ምኒልክ ከለከሉአቸው እንዴ??

ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ እንዲሉ ....

ዛሬ የባንደዎቹ ልጆችና የልጅ ልጆች በምኒልክ የሚያመካኙት እነርሱስ በጣሊያን አንገዛም ብለው ያመፁበት አጋጣሚ ነበርን፣ አለ የሚል ካለ እስቲ በማስረጃ የተደገፈ፣ ገጽ ጠቅሶ ይቅርብና እንወያይ ....


An excerpt from the book "The collusion on Eritrea" 

by Bocresion Haile (an Eritrean)

- As part of the Italian colonial military, almost 4000 Eritrean Askaris were constantly kept in Libya, 800 in Somalia, 6606 Eritreans fought in Adwa against Ethiopia.

ከፍ ሲል ቦክረጽዮን በመጽሐፉ እንደገለጸው በድምሩ 11406 ኤርትራውያን ባንዳዎች በቅኝ ገዣቸው ሠልጥነው ከጣሊያን ጦር ጋር ሊቢያን፣ ሶማሊያንና ኢትዮጵያን እንዲወጉ ዘምተዋል፡፡ አፄ ምኒልክ አደዋ ያዘመቱት ጦር ብዛት 60 ሺህ ቢሆን ይህንን ጦር ለመውጋት በጣሊያን ሠልጥነው ወደ አደዋ የዘመቱት ባንዳ ኤርትራውያን ደግሞ 6066 ሲሆኑ ይህም ከኢትዮጵያ ጦር 10.1% ያህል የሚሆን ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚያስፈልገው አሁን ያዙን ልቀቁን የሚሉት የባንዳ ልጆች አባቶቻቸው ኢትዮጵያውያንን ለመውጋት ወደ አደዋ በመዝመታቸው አያፍሩም፡፡ ለምንስ በወራሪያችው ጣሊያን ላይ አላመጹም፣በጣም ያስደንቃል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም, ቦክረጽዮን በመቀጠልም እንዲህ ብሎናል 

-During the 1935 to 1936 war with Ethiopia, the Italians forced their Eritrean troops to bury dead Italians but not their own dead brothers. ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ እንዲሉ ዛሬ የባንደዎቹ ልጆችና የልጅ ልጆች በምኒልክ የሚያመካኙት እነርሱስ በጣሊያን አንገዛም ብለው ያመፁበት አጋጣሚ ነበርን፣ አለ የሚል ካለ እስቲ በማስረጃ የተደገፈ፣ ገጽ ጠቅሶ ይቅርብና እንወያይ፡፡ Wekipedia, the free Encyclopedia, Italian Eriteria ብሎ የጻፈውን እንመልከት፡፡

The Italian-Eritrean community then grew from around 4,000 during World War I to nearly 100,000 at the beginning of World War II. …. By the early 1940s, Catholicism was the declared religion of around 28% of the colony's population.
Source: Bandini, Franco. Gli italiani in Africa, storia delle guerre coloniali 
1882-1943, "Eritrea". Template:It-icon
"Italian emigration to Eritrea". Template:It-icon

ልብ በሉ እንግዲህ፣ ኤርትራውን ለጣሊዮኖች ምን ያህል ምቹ ተገዥ እንደነበሩና የጣሊያኖችም ቁጥር ከ4ሺ በአጭር ጊዜ 100ሺህ እንደደረሰ፡፡ የምኒልክ ጦር ወደ ኤርትራ ያልዘመተበት በቂ ምክንያት እንደነበረው በብዙ ምሁራን ተጽፎ ይገኛል፡፡ ተላላኪያቸው ወያኔና ተከታዮቹ ግን ዘወትር ምኒልክን እንደወቀሱ ነው፡፡ ባለቤት ካልጮኸ እኮ ጎረቤት አይደርስም፡፡ ለምን እነ ራስ መንገሻ ትግራይን አናስይዝም ብለው አምጸው ድረሱልን አሉ፡፡ አዲስ አበባስ እሩቅ ነው እንበል፣ ለምን ከ6606 ባንዳዎቻቸው መካከል መቶ ወይም አንድ ሺህ የለም እኔ በጣሊያን አልገዛም ብሎ ከትግራይ ወንድሞቹ ጋር አልተቀላቀለም፡፡ ይህ እንዳይደረገም ምኒልክ ከለከሉአቸው እንዴ

 Shame on Bandits and their children, who are trying to steal antiquity. History will be more kinder to mperor Menelik than the Woyanes, who betray Ethiopia and the people. 

የአረና አመራሮች በአዳራሽ ውስጥ ታግተዋል

አረና አመራሮች በአዳራሽ ውስጥ ታግተዋል – ፍኖተ ነጻነት አረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በሀውዜን ከተማ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንዳለ ከመቀሌ የመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ደርሰው እኛ ሰላማዊ ሰልፍ ስለምናደርግ ስብሰባ የሚባል ነገር የለም በማለት ወደ አዳራሹ የሚመጣውን ሰው ድንጋይ በመወርወር ስብሰባው እንዳይካሄድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስብሰባውን እንዲታደም ሲቀሰቅሱ የነበሩ አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ሁለት አባላት ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች በመግጨት አደጋ አድርሰውባቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አዳራሹ ውስጥ ተዘግቶብን ዙሪያውን ተከበናል ፖሊስ መቆጣጠር ስላልቻለ ተጨማሪ ኃይል ጠይቋል ሲሉ የአረና አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገልጸዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ስፍራ ወላይታ ከተማ በተደራጁ ሰዎች ዝርፊያና ታርጋ በሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ ለማድረስ መሞከራቸውን ፍኖተ ነፃነት መዘገቧ የሚታወስ ነው፡፡

TPLF and the Ethiopian Flag



Listen carefully how everything is about Amhara.
Amahra this and Amhara that.
This was a discussion on whether to change the Ethiopian flag or not.
Listen to the amount of hate and suggestions they all throw.
Listen to how all of them talk in the same manner.


Wednesday, May 21, 2014

ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!! ከጥላዬ ታረቀኝ አለማየሁ

ለመረጃ ያህል አሁን እየተሰሙ ያሉ ነገሮች በጣም አስፈሪና አሳዛኝ ናቸው:: ለመሆኑም ይህንን በዝምታ ማለፍ አይቻልም፤ በጥቂቱም ቢሆን እየተሳካለት የሚገኘውን ህዋህት/ኢህዴግ ከመነሻው ጀምሮ ለሀገር ማሰቡ የሚባል ነገር ወደ ጎን በመተው የስልጣን ማርዘሚያ ዘዴዎችን በመቀየስ ይህው 23 ዓመት ሀገሪቱን በጎሳ፤ በጎጥ፤ በብሔር፤ በሀይማኖት ሲከፋፍል ከርሞአል። በመጀመሪያ እሱ በቀደደው ቁምጣ የቡሄር ብሔረሰቦች መብት፤ በማለት ሰራ ግን ከጭፈራ ያልዘለለ መብት ሰጠሁ ብሎ የተወሰኑ በጥቅም በሞቱ አንድ ብሔር እንወክላለን የሚሉ ግን ደግሞ ስራቸው የማይታወቅም ኢትዮጵያን ለመበታተን የተነሱ አካላት ጋር በመደገፍ የህዋህት አሽከር ሆነው ስንመለከት ወይ ሰው ብለን ብዙ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፤ ለምሳሌ በ1997 ምርጫ ውጤት ከታወቀ በኋላ የትግራይን ህዝብ ለመለየት መሠረቱ እስካሁን የማይታወቅ ህዝብ ከህዝቡ የሚያጋጭ ንግግር ሰምተናል ”እቃ ወደ ቀበሌ ትግሬ ወደ መቀሌ” የሚል በመቀጠል ወጣቶችን በማደራጀት አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ በማለት ማህበር አቋቁሞ፤ እዚህ ላይ እና መሰል የተዘሩ የተንኮል ዘሮች ቀናቸውን ጠብቀው አቆጥቁጦ ከማቆጥቆጥም አልፈው ለምልመው ይህው ሀገሪቱ ባለ ብዙ ባንዲራ ባለ ብዙ ሀገር ሆነች። ሁሉም የራሱን ጥግ በመያዝ አንዱ አንዱን ሲጠበቅ ገዥው መደብ ሀገር ሲበዘበዝ ደስ ካለው ከህግ አግባቢ ውጭ ሲገድል ሲያስር ተመልክተናል፤ የፀረ ሽብር ህግ ብሎ አውጥቶ ንፁሃንን በእስር ቤት የሚታገሉ አካላትን እራሱ ሲያሸብር ተመልክተን፤ በፈለገው መጠን ባይባልም በጣም ብዙ ግን የብሔርተኝቶ አስተሳሰብ ያላቸው አፈራ፤ እነሱንም በየኃላፊነት ቦታ ላይ በማስቀመጥ የልቡን አደረሷል፤ በተመቸው ሁሉ ህዝቡ ወደ አንድነት እንዳይመጣ ታግሏ። 
ለምሳሌ በሀይማኖት ለማጋደል ጀሀዳዊ አረካት ብሎ ተጋድሎ ዓይነት መልከት አዘል ዶክመንተሪ ፊልም አስኮመኮመን ብዙም አየው እኔ ግን በጣም የገረመኝ በዘንድሮ የጥቅምት በአል ጥር 11 ቀን 2006 ዓ.ም ማታ የታየው ዶክመንተሪ ፊልም ሰው በማግስቱ ይገኛል ብዬ አልጠበኩም ነበር፤ ግን ህዝቡ የተዋለደ እና በወንድማማችነት የተቆራኘ በመሆኑ ኢቲቪን ታዝቦ ዝም አለ፤ አልተሳካም በቅርቡ ደግሞ ባህር ዳር እስታዲየም ላይ በተነሳው የሁለት ወንድማማቾች ግጭት ከማን የመጣ እቅዱ ነው? ይህን አውግዘን ሳንጨርስ በገዛ ሀገራቸው አማራዎችን ይውጡልን የሚሉ አካላት ተገኙ ግን ጥያቄው ይህ የኦሮሚያ ወንድሞቻችን ጥያቄ ነው? ሌላው ብዙ ነው ጎራ ፈርዳ ቤንሻንጉል ላይ የተደረጉት ድርጊቶች ስንመለከት ሀገሪቱ ምን እንሆነች ነው ብለን ቆዝመናል ጭራሽ ይባስ ብሎ ወንድማቶችን የሚጨርስ የሚያጋድል መሠት የሌለው ታሪክ በዚህ ዘመን የማይታሰቢ ኢትዮጵያ ሊበታትን የሚችል ማስታወሻ ይህን መነሻ ስራ ይሁን ሴራ በማይታወቅ መልኩ የአንድ ብሔር ንጉስ ጡት ቆርጠዋል ብለው ሀውልት ገነባ፤ በአኖሌ ሀውልት ችግሩ መገንባቱ አይደለም የሚዘው ያዘለው መልዕክ ምንድነው? የሚለውን ማጤን ያስፈልጋል የሚያስቡ መንግስት ነኝ የሚል አካል ይህን እኩይ ተግባር ሲፈጽም ለሀገሩ ነው ለስልጣኑ ነው የቆመው ብለን ማጤን ይጠብቀናል ብቻ መርጋቱ ዋጋ አለው ባይ ነን። ሰሞንኑ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል ማስተር ኘላን ይጠቃለል፤ አይጠቀላል የሚለው ውዝግብ በጣም በርካታ የኦሮሚያ ተወላጅ የሆኑ ወንድሞቼ ተምረን ያልፍልናል ብለው ዮኒቨርስቲ ገበታው ሳለ ቤተሰቡ በጉጉት ነገ ልጄ ትልቅ ደረጃ ይደርሳል፤ እያለ በጉጉት በሚጠበቅበት ወቅት ህጉ በማይፈቅደው መልኩ ከህግ ውጭ የመመረቂያ ወረቀት በመስጠት ፈንታ በጥይት ግንባር ግንገሩን በማለት ለቤተሰቡ ሬሳ የላከው መንግስታችን የዛችት 1997ቱ ሳይቀንስ አንድ ነገር አሻሽሎ ብቅ አ። የተከበሩ አቶ አባዱላ ገመዳ ትንሽ ተሳስተናል ግን ባንክ ሲዝረፍ ነው የተገደሉት አሉን ሰው ሲስተም አንኳን አይቀይርም ተቀበሉና አቶ ኩማ ደመቅሳ ከበስተጀርባቸው የሆነ ሀይል አለ አሉ እረ የጉድ ሀገር ስለዚህ በዚህ ብጥብጥ መሀል የብሔር ግጭት እንዲኖር ካድሬዎች እየሰሩ ነው ብሎ ኢሳት ቲቪ ነገሩ ወደሌላ አቅጣጫ እንዳያመራ ጥንቃቄ ይደረግ ሲል እያስጠነቀቀ፤ ይህንን ግን ችላ በማለት የአማራ ተወላጅ ነህ እየተባለ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የስንቱ ቤት ሲደበደቡ የዕሪታ ድምፅ ሰማን። አሁን ልብ ብለን ማጤን ያለብን ነገር እንዴት የሁለቱ ብሔሮች ግጭት ተከሰተ? በዚህ ውስጥ እነማን ተሳተፉ? የሚለውን አንጥረን ማውጣት ካልቻልን እና በዚህ ከቀጠለ በመላው ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተዋለደ አማራ በመላው አማራ የተዋለዱ ኦሮሞ በምን መነጠል ይቻላል? ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ ብሔራቸው ኦሮሞ ግን ደግሞ ጀግና ኢትዮጵያዊ ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር በብሔር አለማመናቸው ባለቤታቸው አማራ ተወላጅ ነበረች፤ እሳቸው ሁለቱን ብሔር እንዴት አድርጎ መለየት ይቻላል? ብለው ታግለዋል። ትግላቸውም አሸናፊ ሆኖ ሁለቱን ብሔር ማስማማት ችለዋል። እኔም በአካል ሄጄ ስለአንድነታቸው ያላቸውን ስሰማ ያ ትውልዱ ያስብላል በአሁን ሰዓት ያለውን የተመለከቱ በመሆኑም እንድ አዋቂ በቀልድም ሆነ በምር መልክ እንዳዋቂ መልዕክት ያስተላልፉ ወገኖች አለጥፉም። ለምሳሌ ታማኝ በየነ ክልል ስንወጣ በምንም መልኩ ፓስፖርት እንዳንጠየቅ ያለበት አጋጣሚ አይረሳኝም፤ በጣም ሊታሰብበት ወያኔ የአህአዲግ በሚመቸው መልኩ ማስተር ኘላን ብሎ ያወጣው እቅዱ ሳይሳካለት ሲቀር የሁለት ብሔር ግጭት ለማስመሰል ከፍተኛ እንቅስቃሴ አያደርግም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። የኛ ጥያቄ የብሔር አይደለም የኢትዮጵያዊነት ነው ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት የኢህደግ ሴራ በሚመቸው መልኩ ጉዳዩን እያስኬዱ ያሉ የህዋህት ታማኝ ካድሬ መሆናቸውን ብዙ ማረጋገጫ አለ በመሆኑም የመብት ጥያቄን ወደብሔር በመቀየር በማተራመስ ላይ በመሆኑ ልክ እንደ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ጀግና የሚያስፈልግበት ወቅት ነው ስለዚህ በጣም ይታሰብበት፡፡

ዘር ማጥራት ወይስ ኢህአዴግን ማፍረስ ? (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ )

Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editorኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች… ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም፡፡ እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው፡፡
አርባ አራት ዓመት ወደኋላ…
በኢትዮጵያ የዘውግ ጥያቄ ለአደባባይ የበቃው በ60ዎቹ መጀመሪያ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከዘመነኞቹ የተማሪ እንቅስቃሴ መሪዎች ይህንን ጥያቄ አለቅጥ ለጥጦና አጋንኖ በማቅረብ ግንባር ቀደሙ ዋለልኝ መኮንን ነው፡፡ በ1962 ዓ.ም በአራት ገፅ ቀንብቦ ባዘጋጀው ታሪካዊ ጽሑፉ አማካኝነት “የብሔሮች ጥያቄ” ይፋ ሆኖ ለውይይት ከመቅረቡ በፊት፣ የተማሪው ዋነኛ የመታገያ አጀንዳ የመሬት ጉዳይ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ (በደብዛዛውም ቢሆን ይንፀባረቅ የነበረውን መደብ ተኮር መንፈስ ሳንረሳ)፡፡ ዋለልኝ የሀገሪቱን መንግስታዊ አወቃቀርም ሆነ ባሕልን በአማራና በትግሬ ተፅእኖ ስር ስለመውደቁ በተቸበት በዚያ “ዝነኛ” ጽሑፉ ላይ እንዲህ ይላል፡-
“…ማንንም ሰው የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ሙዚቃ የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የኢትዮጵያውያን ባሕል የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ ብሔራዊ ልብሳችሁ የቱ ነው ብላችሁ ጠይቁ፤ የአማራ ወይም የትግሬ ይላችኋል፡፡”
ይህ ሀቲት በወቅቱ በአብዛኛው ተማሪ ዘንድ ቁጣ ከመቀስቀሱም በላይ ዋለልኝን በ‹ፀረ-አማራና ትግሬነት› አስፈርጆ ለውግዘት ዳርጎት ነበር፡፡ እራሱም ቢሆን በአንድ የዩንቨርስቲው መድረክ ላይ የተሰነዘረበት ከባድ ተቃውሞ በፈጠረበት ብስጭት ‹‹እኔም አማራ ነኝ፤ ያውም ከአማራ ሳይንት-ቦረና›› ማለቱ ይታወሳል (ቦረና በተለምዶ አማራ መጥቶበታል የሚባለው አካባቢ መሆኑን ልብ ይሏል)፡፡ ግና፣ ዋናው ጥያቄ የእርሱ አማራ መሆን ያለመሆን አይደለም፤ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰበት ምክንያት ከተጨባጩ እውነታ ጋ ምን ያህል ይዛመዳል? የሚል ነው፡፡ ሌላው ነገር ደግሞ ከዚህ ጽሑፍ በፊት ብሔር ተኮር ጎዳዮችን አንስቶ ካለማወቁም በዘለለ፣ ሌሎች ሲያነሱ ፅንፈኛ ተቃዋሚ ስለነበረ ነው፡፡ ለምሳሌ ተማሪ ኢብሳ ጉተማ (ኋላ ላይ የኦነግ መስራችና አመራር የሆነው) ‹‹ኢትዮጵያዊ ማነው?›› በሚል ርዕስ ባቀረበው ግጥም እጅግ ተናድዶ ‹‹እንዴት እንዲህ አይነት ግጥም ታቀርባለህ? ዘረኛ ነህ፤ ኢትዮጵያውያንን የመከፋፍል ዓላማ ነው ያለህ?›› በማለት እስከመቃወም መድረሱ የክርክሩ አንዱ ጭብጥ ነው፡፡

ታዲያ ዋለልኝ መኮንን ድንገት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው ከምን የተነሳ ይሆን? በርግጥ ለዚህ ድንገቴ የአቋም ለውጥ ሶስት መላ-ምቶች ሲነገሩ ቆይተዋል፡፡ የመጀመሪያው ‹በአፄው ሥርዓት ላይ አሴረዋል› ተብለው ከተከሰሱትና ‹ኦሮሞ እየተጨቆነ ነው› የሚል እምነት ከነበራቸው ጄነራል ታደሰ ብሩ ጋር በታሰረበት ወቅት፣ በጄነራሉ ስብከት አመለካከቱ ተቀይሮ ሊሆን ይችላል የሚለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ‹‹መገንጠልን መደገፍ በመጨረሻ የማትገነጠል ሀገር እንድትኖር ያደርጋል›› በማለት ከተከራከረበት ከራሱ አቋም ጋር የሚያያዝ ነው፤ ሶስተኛው ‹የሻዕቢያ (ኤርትራውያን ተማሪዎች) አሊያም የአሜሪካኑ የስለላ ተቋም (ሲ.አይ.ኤ) መጠቀሚያ ሆኖ ነው› የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ይሁንና ከዋለልኝ ጀርባ ‹ስውር እጅ›ን ለመፈለግ ያስገደደው በጊዜው ብዙሁ ተማሪ ለሀገሪቱ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ‹የንጉሣዊው አስተዳደር ኋላቀርነት እና ስግብግበነት ነው› ብሎ ከማመኑም ባለፈ፣ ከፌዴራላዊ ይልቅ የቻይና ኮሙኒስታዊ ሥርዓት አድናቂ የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የተማሪውን እንቅስቃሴ በመምራት በዘመኑ ከዋለልኝ የላቀ ተሰሚነት የነበረው ጥላሁን ግዛው ‹‹ጎሰኝነትን›› በአደባባይ አጥብቆ ይቃወም እንደነበረ፣ በ1968 እ.ኤ.አ የታተመው ‹‹Struggle›› ቅፅ 3፣ ቁጥር 1 መጽሔት ጋር ያደረገውን ቃለ-መጠይቅ መጥቀስ ይቻላል፡-
‹‹በመጀመሪያ ደረጃ በጎሰኝነትና በሶሻሊዝም መካከል ያለውን ልዩነት ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ጎሠኝነት በተወሰነ አካባቢ ብቻ የሚቀርና አካባቢ ቀመስ ነው፡፡ ሶሻሊዝም ግን ዓለም ዓቀፋዊ ነው፡፡ …እንደ ዩንቨርስቲ ተማሪነታችንና እንደ እጩ ምሁርነታችን የሕብረተሰባችንን አቋም ከመደብ አንፃር መተንተን እንጂ በጎሣ መከፋፈል አይገባም›› ማለቱ ይታወሳልና፡፡
የህወሓት-ውልደት
ዋለልኝ መኮንንን ‹‹የብሔር ጭቆና›› ትንተናን መሰረት ያደረጉ ጥቂት የማይባሉ የፋኖ ድርጅቶች መመስረታቸው አይካድም፡፡ ከእነዚህም መንግስታዊውን ሥልጣን ለመጨበጥ የበቃው ህወሓት አንዱ ነው፡፡ የአማራና ትግሬ ጨቋኝነትን የሚያውጀው ጽሑፍ በተሰራጨ በአምስተኛው ዓመት የትግርኛ ተናጋሪውን ብሔራዊ ጭቆና ለማስረገጥ ጽሑፉን እንደ ሰነድ ማስረጃ ቆጥረው ‹‹ትግራይን ነፃ እናወጣለን!›› ያሉ ፋኖዎች ነፍጥ አንግበው በረሃ ቢወርዱም፣ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት አካባቢ ‹‹እንታገልለታለን›› በሚሉት ዘውግ ተወላጆች ሳይቀር መናፍቅ ተደርገው መወገዛቸው ይታወሳል፡፡ ደራሲና ገጣሚ አስማማው ኃይሉም ‹‹ኢህአሠ›› በተባለው መጽሐፉ እንዲህ ይለናል፡-
‹‹በ1969 ዓ.ም አጋማሽ አካባቢ በእምባ ሰገንይቲ ወረዳ ነበለት አካባቢ ሽምዕጭ ተብሎ በሚጠራው መንደር የህወሓትና የኢሕአሠ አባላት ሕዝብን ለመቀስቀስ ተገኝተው ነበር፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የድርጅታቸውን ዓላማ ካስረዱ በኋላ ያካባቢው አዛውንት ማሳረጊያውን ንግግር አደረጉ፡፡ አዛውንቱ መሔድ የሚሳናቸው ስለነበሩ ሰዎች ደግፈው ወደ በቅሏቸው እንዲያወጧቸው ከጠየቁ በኋላ የሚከተለውን ንግግር አደረጉ፡፡ ወደ ህወሓት አባላት እጃቸውን ዘርግተው ‹እናንተ ከሆዳችን የወጣችሁ ልጆቻችን ናችሁ›፤ ወደ ኢሕአሠ አባላትም ፊታቸውን አዙረው ‹እናንተ ደግሞ ከሁሉም የኢትዮጵያ ግዛት መጥታችሁ ለእኛ ስትሉ ነው የምትታገሉት፡፡ የሆነው ሆኖ እኛ የትግራይ ሰዎች ሆነን ስንቀር ኢትዮጵያ ከማን ጋር ልትቀር ነው? ስለሆነም እኛ ኢትዮጵያዊ ከሚል ጋር ነው የምንወግነው› ሲሉ ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡›› (ገፅ 235)
ህወሓት በትግራይም ሆነ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን አገዛዛዊ ጭቆና፣ የብሔር አስመስሎ እስከ መገንጠል ቢንደረደርም፣ የገጠመው ተቃውሞ ፕሮግራሙን ለመከለስ አስገድዶታል፡፡ ዘግይቶ ላገኘው ድጋፍም ቢሆን ከዘውግ ተኮሩ ተረት-ተረት ይልቅ አምባ-ገነናዊው የደርግ አስተዳደር የወለደው ሽብርና ጭፍጨፋ የተሻለ ጠቅሞታል፡፡ ለዚህም በዛሬይቷ ትግራይ ከሶስት ያላነሱ ፀረ-ህወሓት ድርጅቶች መኖራቸው ማሳያ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡
በሌላ በኩል ከህወሓት ምስረታ አንድና ሁለት ዓመት አስቀድሞ ወደ አደባባይ የመጡት ኢህአፓና መኢሶን የትግል አጀንዳቸው የመደብ ቅራኔ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ ይህ ግን በወቅቱ ከህወሓትም በከረረ መልኩ ‹‹የብሔር ጥያቄ በመገንጠል ብቻ ነው የሚፈታው›› የሚል እምነት ተከታዩ ኦነግን ህልውና አያስክድም፡፡ እዚህ ጋ የምንመለከተው ሌላኛው ግራ አጋቢ ጉዳይ የመጀመሪያው የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን የ‹‹መሬት ላራሹ››ን ሠልፍ (በ1957 ዓ.ም) አስተባብሮ የሕግ-መወሰኛው ምክር ቤት ድረስ የመራው ባሮ ቱምሳም (በአብዮቱ ሰሞን የኢጭአት የአመራር አባል ነበር) ሆነ፤ የመኢሶኑ ቁልፍ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ኃይሌ ፊዳን የመሳሰሉ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ልሂቆች፣ ከኦነግ በተቃራኒው ከብሔር ይልቅ የመደብ ጥያቄ አቀንቃኝ የነበሩ መሆኑን ነው፡፡ በነገራችን ላይ በግሌ ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ብያኔ እነዋለልኝ የለጠጡትንና ያጎኑትን ያህል እንኳ ባይሆንም እንደገና መከለስ እንደሚያስፈልገው አምናለሁ፡፡
የሆነው ሆኖ ህወሓት መንግስታዊውን ሥልጣን በጨበጠ ማግስት ‹የሰነበተውን የብሔር ቅራኔ በማያዳግም ሁኔታ የሚፈታ› ሲል ያንቆለጳጰሰውን ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝም ቢተገብርም፤ ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን የመግታት አቅም እንደሌለው ለማረጋገጥ የአንድ እጅ ጣቶች ያህል ዓመታት እንኳን አልፈጀም፡፡ በደቡብ በጉጂ እና ጌዲዮ፣ በጉጂ እና ቡርጂ፤ በጋምቤላ በአኝዋክ እና ኑዌር፤ በቤንሻንጉል በጉምዝ እና በርታ መካከል የተከሰቱት የይገባኛል ግጭቶች በማሳያነት ይጠቀሳል፡፡
የፌዴራሊዝሙ ቀዳዳዎች
ዘውግ ተኮር ፌዴራሊዝሙ፣ ገና ከጠዋቱ ለከፋ ዕልቂት ሊዳርግ እንደሚችል በማስታወስ ይሰሙ የነበሩ የተራዘሙ ጩኸቶችን ችላ ብሎ ዛሬ ላይ ቢደርስም፤ ለፕሮፓጋንዳ በሸነቆራቸው ቀዳዳዎች እየገባ ያለው ከባድ ንፋስ ከራሱ አልፎ ሀገሪቷንም ከበታኝ አደጋ ፊት አቁሟታል፡፡ ለዚህም አገዛዙ የፈጠራ ትርክቱን ለማስረፅ የሄደበት የኑፋቄ መንገድ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ በፓርቲው ካድሬዎች በኩል በየዕለቱ የሚዘራው የጥላቻ ፖለቲካ፣ ሐውልት ማነፅ፣ ከፋፍሎ ማቆም እና መሰል ስልቱ በተጨማሪ ሜጋ በሚያሳትማቸው መጻሕፍት እልቂት ጠሪ ዘውግ ተኮር ቅስቀሳዎችን እስከማሰራጨት መድረሱን ተመልክተናል፡፡ ለአብነትም የሚከተለውን ግጥም ልጥቀስ፡-

“ነፍጠኞች እቤታቸው በክብር ይጎለታሉ፣
እኛን በኃይል አስገድደው ያሰራሉ፣
ቁጥቋጦ እንደምትመነጥረው መንጥራቸው
ወደመጡበት ወደ ሸዋ አባራቸው፡፡”
 (“ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ቅፅ 3፤ ገፅ 145)
ግና ‹‹ሸዋ›› ሱዳን ወይም ግብፅ አይደለምና ዛሬ ከጉራፈርዳ እስከ ደንቢዶሎና ጊምቢ ለተተገበረው የማባረር ዘመቻ ዋነኛው ተጠያቂ የሥርዓቱ ኤጲስ ቆጶሳት መሆናቸውን ግጥሙ ያስረግጣል፡፡ በግልባጩ እነዚህ ሰዎች በ97ቱ ምርጫ ዋዜማ፣ ሚያዚያ 30 ቀን መስቀል አደባባይ ቅንጅት በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ፣ አቶ በድሩ አደም ‹‹ወደመጡበት እንመልሳቸዋለን›› ማለታቸውን፣ ወደ ዘውግ ጥላቻ ከመቀየራቸውም በላይ፣ የቅንጅቱን አመራሮች ለቅመው ካሰሩ በኋላ የሰውየውን ንግግር ‹‹የዘር ማጥፋት ሙከራ!›› ሲሉ ለመሰረቱባቸው ክስ በማስረጃነት ማቅረባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ በዚያው ሰሞን አቦይ ስብሃት ነጋም የብአዴን ጓዶቻቸውን ‹‹እኛ ወደመቀሌ ስንባረር፤ እናንተን መንዝ ላይ አራግፈን ነው የምንሄደው!!›› አሉ መባሉም ጉዳዩ በራስ ላይ ሲደርስ ምን ያህል አሳማሚ እና ለበቀል እንደሚያነሳሳ ሁነኛ ጥቁምታ ቢሰጥም፣ ገዥዎቻችን ትምህርት ሊወስዱበት አለመቻላቸው ያስቆጫል፡፡ እንዲያውም ከምርጫ 97 በኋላ በዩንቨርስቲዎች ግቢ የሚነሱ ተቃውሞዎች ዘውግ-ተኮር ወደመሆን ነበር የተሸጋገሩት፡፡ ኢህአዴግም ቢሆን በዩንቨርስቲዎች በተናጠል (በህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴን) ስር ማደራጀት የጀመረው ከዚሁ ምርጫ በኋላ እንደነበረ አይዘነጋም፤ ለእንዲህ አይነቱ የፓርቲው ተልዕኮ ደግሞ እንደ ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ አይነት የገዥው-ፓርቲ መንፈስ የሰረፀበት ‹‹ምሁር›› ጠቀሜታን ለመረዳት አሁን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ያለበትን ሁኔታ መቃኘቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ በርግጥ ባለፉት ሁለት አስርታት የህወሓት አባልና ደጋፊ ተማሪዎች የግቢውን መንፈስ አይመረምሩም (አይሰልሉም) ነበር እያልኩ አይደለም፤ በግላጭ የጓደኞቻቸውን እንቅስቃሴ እየተከታተሉ ሪፖርት ያደርጉ ነበርና፡፡ በአናቱም የዘውግ ተኮር ፖለቲካው መተግበር በጀመረበት ወቅት ወደ ትምህርት ቤት የተላኩ ልጆች፣ ዛሬ ለዩንቨርስቲ መብቃታቸው፣ አጀንዳው በቅፅበት ሊፈፀም የመቻሉን እውነታ በኦሮሚያ ሰሞኑን የተመለከትነው ቀውስ በቂ ማሳያ ይሆናል፡፡
የተጭበረበረው አጀንዳ
‹የብሔር ጥያቄ ዋነኛው የቅራኔ ቅርፅ ነው› የሚለው ህወሓት ይህን ጥያቄ መፍታት ሥርዓታዊ ግብ እንደሆነ እስኪሰለቸን ቢደሰኩርም፤ አጀንዳውን ከማጭበርበሪያነት የዘለለ ዋጋ አልሰጠውም፡፡ እናም ታሪክ ቢያንስ በዚህ በኩል በበጎ እንደማያስታውሰው ለመናገርም ብዙ ማስረገጫዎችን መጥቀስ አይገድም፡፡ አሁንም ኢትዮጵያን እየናጣት ያለው፤ ጥያቄያችን አልተመለሰም› የሚሉ ብሔርተኛ ቡድኖች መበርከት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በስያሜ ደረጃ እንኳን (መሬት ላይ ያላቸውን ጉልበት ትተን) ከአስራ አንድ የማያንሱ ተገንጣይ ንቅናቄዎች መኖራቸው እውነት ነው፡፡ የእነዚህን ከኦጋዴን እስከ ጋምቤላ፤ ከቤንሻንጉል እስከ አፋር ድረስ ያሉ አማፅያን እንቅስቃሴን የጥቂት ልሂቃን ቅብጠት አድርጎ መውሰድ ርትዕ አይሆንም (ስለምን ቢሉ ደርግም ህወሓትን የሚያስበው እንዲያ ነበርና)፡፡ እናም ከትልቁ ኦሮሞ ጥያቄ መጠለፍ ጀምሮ፤ እነዚህ ጉዳዮች አስቀድሞ ግንባሩ የብሔር ጥያቄን ለሥልጣን መወጣጫ ብቻ ለመጠቀም ማስላቱን ይጠቁሙናል፡፡
ሌላኛው ጭብጥ አሁንም ድረስ ማንነት ተኮር ጥያቄዎች አለመቆማቸው ነው፡፡ ከቅማንት እስከ ወለኔ እና ቁጫ ድረስ ያሉት ‹‹ማንነታችን ታውቆ ዞን ይሰጠን›› ጩኸቶች ማቆሚያቸው የቱ ጋ እንደሆነ ራሱ ኢህአዴግም የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ በግልባጩ ለእነዚህ ሶስት የማህበረሰብ ክፍሎች ጥያቄ በቅርቡ የሠጠው ምላሽ ጭፍለቃ መሆኑን ስናስተውል፤ ‹ተነሳሁለት› ከሚለው የብሔር ጭቆናን ማጥፋት አኳያ የሚነግረን ሀቅ ሥርዓቱ የሄደበትን ቁልቁለት ብቻ ነው፡፡
በሶስተኛነት ከዚሁ ጋር አያይዘን ልናነሳው የምንችለው ርዕሰ ጉዳይ የመገንጠል መብት ነው፡፡ ከዋለልኝ እስከ ጥላሁን ታከለ እና ቱሞቱ ሌንጮ (ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ) ድረስ የነበሩ የዘመኑ ትውልድ መንፈስ ተርጓሚዎች መገንጠልን ሕብረ-ሱታፌ (ሶሻሊስታዊ) ሥርዓት ለመገንባት መዳረሻ መንገድ አድርገው ቢያቀርቡትም፤ ጥራዝ ነጠቆቹ ህወሓቶች ሕገ-መንግስቱ ውስጥ ቀርቅረውታል፡፡ ለዚህም እንደምክንያት ‹‹መገንጠልን ለመከላከል ነው›› ቢሉም፤ ከፌደራሊዝሙ አወቃቀር አኳያ ‹የማይተገበር መብት› ስለመሆኑ ብዙ ተብሏል፡፡ ይህንን ለማስረገጥ በዋናነት ሁለት ነጥቦች ይነሳሉ፤ ‹እንደ ስታሊኒስቷ ሩሲያ ሁሉ መብቱ በሕገ-መንግስቱ ውስጥ ቢካተትም፣ የማዕከላዊ መንግስቱ ሥልጣን ፍፁማዊ መሆን እንዳይተገበር ያደርገዋል› የሚለው የመጀመሪያው ነጥብ ነው፡፡ ሁለተኛው የመብት አፈፃፀሙ ራሱ በተለያዩ አስገዳጅ ተዋረዳዊ ትግበራዎች መጠላለፉ ነው፡፡ በተለይም ሁለትና ከዚያ በላይ ዘውጎችን ያቀፉ ክልሎች የመገንጠል ጥያቄ ቢያነሱ ተፈፃሚነት እንደማይኖረው ለመረዳት የክልሎቹን አወቃቀር መመልከቱ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡ ከእነዚህ ሁለት ነጥቦች ስንነሳ የመገንጠል ግብ ያላቸው እንቅስቃሴዎች በትጥቅ ትግል አገዛዙን ካላስወገዱት በቀር በሕገ-መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ሊተገበሩ አለመቻላቸውን እንገነዘባለን፡፡ ይህ ሁነትም ሥርዓቱ ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ያነበረው ከፋፍሎ ለመግዛት እንጂ፤ እስክንደነቁር በጩኸት ስለሚነግረን ‹‹ጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች›› መብት ደንታ ኖሮት እንዳልሆነ ያስረግጥልናል ብዬ አስባለሁ፡፡

ግን እስከመቼ?
በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአፄ ኃይለስላሴ ቀጥሎ ረዘም ላለ ዓመታት ሀገሪቱን የመምራት ዕድል ያገኘው ኢህአዴግ የተሻለች ሀገር የመገንባት በርካታ ዕድሎችን አምክኗል፡፡ ወደሥልጣን በመጣ ማግስት ዘውገኝነትን የመንግስታዊ መዋቅሩ ብቸኛ ገፅ ሲያደርገው፣ ከብዙ ጫፎች ከተነሳበት ከባባድ ተቃውሞዎች መሀል፡- ቋንቋ ተኮር ፌዴራሊዝሙ ማሕበረ-ባሕላዊ መሰረቱ በጣም የተሳሳተ መሆኑን እና የዘውግ ማንነትን ብቸኛው የክልሎች ድንበር አሰማመር መነሻ ማድረግ ለእርስ በእርስ የዜጎች ትንቅንቅ ያጋልጣል የሚሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ ሥርዓቱ ይህን ጆሮ ሰጥቶ ከማዳመጥ ይልቅ ቢያፈገፍግም፣ ያሳለፍናቸው ሃያ ሶስት ዓመታት በሞቶችና በመከራዎች የተፃፉ ኩነቶችን አሳይተውናል፡፡ ‹‹ባለሥልጣን›› እና ‹‹ሥልጣን የለሽ›› (ባለቤትና መጤ) በሚል ጨዋታ፣ በየክልሎቹ የሚገኙ የሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከክልሉ የሥራ ቋንቋ ውጪ በመናገራቸው ብቻ፣ አንዳችም ተቋማዊ ውክልና እንዳያገኙ ማድረጉ፣ ከየአካባቢዎቹ በግፍ ለተፈናቀሉት የማሕበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው መነሻ ሆኗል፡፡ አዲሱን የአዲስ አበባ የማስፋፊያ ዕቅድ ተከትሎ የተነሳው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞም ሌላ ቅርፅ ወደመያዝ መሻገሩ አንዱ ሰሞነኛ ማሳያ ነው፡፡ በምዕራብ ወለጋ ለረዥም ጊዜ ኑሯቸውን መስርተው የነበሩት የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸው የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ፣ የአማራ ክልልን ጨምሮ የየክልሎቹ ዘውጎች ‹‹መጤ›› ያሏቸውን ማባረር ላለመጀመራቸው እርግጠኛ መሆን የምንችልበት ምንም አይነት ዋስትና የለንም፡፡ እናሳ! ይህ አይነቱ ክልልን ከ‹‹መጤ›› ዘውግ የማንፃት ሂደት ማቆሚያው የቱ ጋ እንደሆነ ማን ሊገምት ይቻለዋል? ዘግናኝ ደም መፋሰስስ ሳያስከትል ይህንን ክፉ ድርጊት መሻገር የምንችለው እንዴት ነው?
እንግዲህ ይህ ሁሉ የፍርሰት መርዶ እየተሰማ ያለው፣ የሥርዓቱ ሰዎችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ለዚህ ከፍታ የበቁበትን ሃያ ሶስተኛ የድል ዓመት በፌሽታ ለማክበር ደፋ ቀና በሚሉበት ዋዜማ ላይ ቆመን ቢሆንም ‹‹ጊዜው ከቶም ቢዘገይ አልረፈደም›› እንዲሉ፤ ተገፍቶ ገደል ጠርዝ የተንጠለጠለውን የኢትዮጵያን ህልውና በደለደለ መሰረት አፅንተን ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር አንዳች እርምጃ መውሰዱ ብቸኛ አማራጭ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለዚህ ዘመን ለጣለው ትውልዳዊ የማንነት ዕዳ ክንውን ቀዳሚው ተግባር ኢህአዴግን ‹‹በቃህ!›› ብሎ ማስቆም እንደሆነም መቀበል የሚያስቸግር አይመስለኝም፡፡ ግና፣ ይህ ሳይሆን በወታደራዊ ጡንቻ ካሳለፍናቸው ዓመታት ጥቂቱን እንኳ እንዲሰነብት ከፈቀድንለት፣ የደም ባሕር ሲያጥለቀልቀን ቆመን ለመመልከት ተስማምተናል ማለት ነው፡፡
Source Ethiomedia

በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአብዛኛዎቹ ዘርፎች እንደማይሳካ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡

May 21/2014

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም ሊከናወን የታቀደው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከፋይናንስ አቅም ፣ከሰለጠነ የሰው ኃይል እና ከመሠረተ ልማት አለመሟላትና ከመሳሰሉ ጉዳዮች  ጋር በተያያዘ ፈተናዎች ገጥመውታል፡፡

በዕቅዱ ዓመታት  11 በመቶና ከዚያ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የታሰበ ቢሆንም ባለፉት ሶስት የዕቅዱ ዓመታት የተመዘገበው እድገት 10 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ከኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ አንጻር በሚጠበቀው አቅጣጫ እና በጎላ መልኩ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን መረጃው ይጠቅሳል፡፡

በተለይ ባለፉት ሶስት ኣመታት ካጋጠሙ ፈተናዎች መካከል በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት የተከሰተው የዋጋ ንረት፣ የግብርና ዘርፍ ምርታማነት ዕድገት አርኪ አለመሆን፣ ኤክስፖርት የገቢ ድርሻ ማሽቆልቆል ፣ የኢምፖርት ድርሻ በከፍተኛ ደረጃ ማደግ፣ የግብርና ዘርፍ የምርታማነት ዕድገት የተፈለገውን ያህል አለመሆን፣ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከመነሻው መሠረተ ጠባብ መሆን፣ የግል ባለሃብቱ ተሳትፎ ማሽቆልቆል ፣ ከምንም በላይ የማስፈጸም አቅም ማነስ እና በየደረጃው የሙስናና ብልሹ አሰራር ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮች መንሰራፋት ይጠቀሳሉ፡፡

የመካከለኛና ትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ልማት በውጪ ንግድ የሚመራ፣ የውጪ ምንዛሪ እጥረትን የመቅረፍና ለግብርና ልማት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ከተቀመጡ ኣላማዎች አኳያ ባለፉት ሶስት የዕድገትና የትራንስፎርሜሸን ዕቅድ የትግበራ ዓመታት ክንውን ወደኃላ የቀረ መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ይጠቅሳል፡፡

በፕሮጀክቶችም ደረጃ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት በመንግሥት መረጃ መጠናቀቅ የቻለው 30 በመቶ ያህል ብቻ ሲሆን በባቡር ፤ በስኳር፣ በማዳበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ የተያዙ ዕቅዶች ቀጣዩ የእቅዱ መጨረሻ ኣመት ድረስ የሚሳኩ አይደሉም፡፡

በዚህም ምክንያት ለመጪው ዓመት ምርጫ ድረስ የአዲስአበባ ቀላል ባቡርን ስራ ለማስጀመር ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት የቻይና ኩባንያዎችን ጥብቅ መመሪያ የሰጠ ሲሆን ይህ ዓይነቱ የጥድፊያ አካሄድ በግንባታው ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ባለሙያዎች ከወዲሁ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው፡፡

የአዲስአበባ ቀላል ባቡር ግንባታ በዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ውስጥ የሌለና በእነአቶ መለስ ዜናዊ ደንገተኛ ውሳኔ የተጸነሰ ዕቅድ ሲሆን ግንባታው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸውን የመንገድ መሰረተ ልማቶች፣ ሕንጻዎች እያፈራረስ ከመምጣቱም ባሻገር የባቡሩ መስመር ዝርጋታ ለእግረኞችና ለተሸከርካሪዎች ማቋረጫ ግምት ውስጥ ባላስገባ መልኩ እየተከናወነ መሆኑ በባለሙያዎች ጭምር ጠንካራ ትችትን አስከትሎአል፡፡

የመንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ እጅግ የተለጠጠ እና በፋይናንስና በሰውኃይል አቅም ሊተገበር እንደማይችል በተለይ በአገር ውስጥ በሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቶዎችና በውጪ አገር በሚገኙ ኢትጽያዊያን ባለሙያዎች በሰፊው ሲተች የቆየ ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት ይህ የኒዮሊበራሊስቶች አፍራሽ አስተሳሰብ ነው በሚል ሲያጣጥለው ከመቆየቱም በላይ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር በፓርላማ ተቃዋሚዎችን በኃላ ዕቅዱ ሲሳካ እንዳታፍሩ እስከማለት መድረሳቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ዘረኝነት -በኢትዮጵያ እግር ኳስ! የጋምበላ ምርጥ "ቶክ" አንገቱን ደፋ

ዘረኝነት -በኢትዮጵያ እግር ኳስ!
የጋምበላ ምርጥ "ቶክ" አንገቱን ደፋ
የኢትዮጵያው ቡናው እና የኢትዮጰያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ የጋምበላ ምርጥ ውጤት ቶክ ጀምስ ይርጋለም ላይ በአንዳንድ ደጋፊዎች በዝንጀሮ ድምፅ በቆዳ ከለር ተሰድቧል።
በቦታው የነበሩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊው ቶክ በድንጋጤ ከሜዳው ወጥቶ የተቀያሪ ወንበር ላይ አንገቱን አቀርቅሮም ታይቷል። በአዲስ አበባ ስታዴየም የግለሰቦች ስም እየጠሩ የሚሳደቡ እንዳሉ ይታወቃል።
ይህ ጉዳይ ጥንቃቄ ሊወሰድበት የሚገባ ነው።